የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ከሚገኘውን የአለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርኡ ዌንድሊን ክብዌ ከተመራ ቡድን ጋር ውይይት አካሄዱ።
-----------------------//---------------------
(ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ዘርፉ በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚሰሩ እና በቀጣይ በሚኖሩ ግንኙነቶች ዙሪያ ከኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሩ ጋር ተወያይተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የትምህርት ተደራሽነት ለማስፋፋት በሰፊው ቢሰራም ከፍተኛ የጥራት ችግር የነበረበት መሆኑን በመጥቀስ ይህንን ለመለወጥ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ዘርፈ ብዙ የትምህርት ዘርፍ ሪፎርሞች ለዳይሬክተሩ አብራርተውላቸዋል።
በተለይም ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት እና ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ ከትምህርት ጥራት ጋር የተያያዙ ሪፎርሞችን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚረዱ የትምህርት ልማት አጋር ድርጅቶች ጎን ለጎን የአለም ባንክ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
የዓለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርኡ ዌንድሊን ክብዌ በበኩላቸው ትምህርት የዓለም ባንክ የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዩ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉን ለመቀየርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚሰራውን ሥራ በአድናቆት እንደሚመለከቱት ገልጸዋል።
አክለውም በቅርቡ በሚዘጋጀው የ5 ዓመት እና የ10 ዓመት የኢትዮጵያ እና የአለም ባንክ የትብብር ስትራቴጂ ላይ በተለይም የትምህርት ዘርፉን በሚመለከት ክቡር ሚኒስትሩ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ
----------------------------------------------------
(ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር) በአገር አቀፍ ደረጃ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና መጠናቀቁን ተገልጿል።
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም በመላ አገሪቱ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
ከዝግጅት ጀምሮ በፈተናው ወቅት በየደረጃው የሚገኙ በፈተናው ስራ የተሳተፉ ባለሙያዎች ፣ አመራሮችና ባለድርሻዎች በፈተናው ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ፈተናው በሰላም ተጠናቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የፈተናው ስራ እንዲሳካ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለተወጡ ኃላፊዎች፣ አስተባባሪዎች፣ ፈታኞች፣ የጸጥታ አስከባሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻዎች ላበረከቱት አስዋጽኦ ምስጋና ያቀርባል፡፡
ተፈታኞችም ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ላሳዩት በጎ ስነ ምግባር አያመሰገነ መልካም እድል እንዲገጥማቸው ትምህርት ሚኒስቴር ምኞቱን ይገልጻል፡፡
የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ(12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ በወረቀትና በበይነ መረብ በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከባለፉት ሶስት አመታት በተሻለ መልኩ በሠላም እና በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ።
----------------------------------------------
(ሐምሌ 9/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የታለመለትን ግብ በመምታት በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
ሚንስትሩ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት ሶስት አመታት በተወሰነ መልኩ ያጋጥሙ የነበሩ የጸጥታ ችግሮች፣ የፈተና ስርቆት ሙከራዎች፣ የፈተና ስርዓትና አስተዳደር የዲሲፒሊን ግድፈቶች በዘንድሮው አመት ቀንሰው መገኘታቸውን አብራርተዋል።
ለዚህም የበይነ መረብ የፈተና ሽፋን በአንድ አመት ውስጥ በአራት እጥፍ ማደጉ፤የፈተና ግብረ ሀይሉ ያልተቆጠበ ጥረት፤ እንዲሁም ተማሪዎች ሰርቶ ውጤት ማምጣት አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን መገንዘባቸውና መሰል ለውጦች ችግሮች ጎልተው እንዳይስተዋሉ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Ap4FMbaWM/

የትምህርት ሚኒስቴር የሚያስገነባቸውን የፌዴራል አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ2018 የትምህርት ዘመን ስራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
--------------------//-------------------
(ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም) በአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር እያስገነባቸው ካሉ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የተወሰኑት በመጪው የትምህርት ዘመን ስራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞ በሰጡት ማብራሪያ እንዳስታወቁት በሳይንስና በቴክኖሎጂ የበቁ የነገ የዚች ሀገር መሪ መሆን የሚችሉ ዜጎችን ለማፍራት የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም አካባበዎች የሚመጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው፣ አብሮ መኖርና ማደግን የሚለምዱባቸውና የአገሪቱ የወደፊት መሪዎችን የምናፈራባቸው ቦታዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡
በዚህም መነሻ የትምህርት ሚኒስቴር በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች እያስገነባቸው ካሉ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የተወሰኑትን በመጪው የትምህርት ዘመን ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/15vewLAG6N/

ኢትዮጵያውያንና የባለድርሻ አካላት ከብሄራዊ ዩኔስኮ ጎን በመቆም አገራችን ከዩኔስኮ የምታገኘውን ጥቅም እንዲያሳድጉ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ።
----------------------------------------------
(ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም) የብሄራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሃፊ አቶ አለሙ ጌታሁን ብሄራዊ ዩኔስኮ እና የዩኔስኮ በአፍሪካ የመምህራን አቅም ግንባታ ተቋም (IICBA) በጋራ ባዘጋጁት አውደ ጥናት ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኢትዮጵያውያንና የባለድርሻ አካላት ከብሄራዊ ዩኔስኮ ጎን በመቆም አገራችን ከዩኔስኮ የሚታገኘውን ጥቅም እንዲያሳድጉ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ አለሙ ከዩኔስኮ የሚገኘውን ብሄራዊ ጥቅም ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ ከሶስቱ የአፍሪካ አገራት ማለትም ከኬንያ፣ናይጄሪያና ኡጋንዳ ተሞክሮ መውሰድ ዋነኛው የአው ደጥናቱ አላማ መሆኑን አንሰተዋል፡፡
አውደ ጥናቱ ለተሳታፊዎች ግልጽነት ከመፍጠርና ልምድ ከማለዋወጥ በተጨማሪ ተደጋግፈው፣ተቀናጅተውና በመተማመን መርህ ላይ ተመስርተው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አቶ አለሙ አክለውም አውደጥናቱ በፓናል ውይይት ታግዞ ቀጣይ ዋና ዋና ተግባራትና የአቅም ግንባታ እቅዶች የሚታቀዱበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የዩኔስኮ በአፍሪካ የመምህራን አቅም ግንባታ ተቋም (IICBA) ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ኮንታን ውዶን አውደጥናቱ ብሄራዊ ዩኒስኮን እንደተቋም የማጠናከር፣ የዩኒስኮ ፕሮግራሞችን ከሚተገብሩ ሴክተሮች፣ተቋማት፣ከዩኔስኮ የአቅም ግንባታ ማዕከላትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር የለውን ግንኙነት የማጠናከርና የማስተሳሰር ፋይዳ ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ የሀገር ወስጥና የሀገር ውጭ ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።

"ለትውልድ ስንል አረንጎዴ አሻራችንን ያለልዩነት እናስቀምጣለን" የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ
-------------------------------------------
(ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ አካሄዱ።
"በመትከል ማንሠራራት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የአረንጎዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ለትውልድ ስንል አረንጓዴ አሻራችንን ያለልዩነት እናስቀምጣለን ብለዋል።
ሚንስትሩ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ባስተላለፉት መልእክት ሀገርና ትውልድን በሚጠቅሙ ጉዳዬች ላይ ሁሉም ዜጋ ያለልዩነት የበኩሉን አስተዋጾ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተከናወነው የችግኝ ተከላ ከስራና ሙያ ጋር የተያዘና ለተማሪዎች አርያ ለመሆን ታስቦ መሆኑን የገለጹትት ሚንስትሩ ሁሉም ዜጋ ባለው የሙያም ይሁን ማህበራዊ ትስስር ሁሌም አረንጓዴ አሻራውን ማኖር አለበት ብለዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19zQMUr4iN/