ተማሪዎችም በነጻነት ተምረው ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢያቸው ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃት ነጻ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
================================
(ሀምሌ 26/2017 ዓ.ም) ህብረተሰቡና የባለድርሻ አካላት በትምህርት ቤት ውስጥና አካባቢው የሚፈጽሙ ጾታዊ ጥቃቶችን ተረድተው እንዲከላከሉና ምላሽ መስጠት እንዲችሉ የሚረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና ከክሌሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሰቷል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በስልጠና መድረኩ ማስጀማሪያ መርሃ-ግብር ላይ እንደተናገሩት ወላጆች ያለስጋት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩና ተማሪዎችም በነጻነት ተምረው ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢያቸው ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃት ነጻ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ቤትና አካባቢው ማህበረሰብ ጾታዊ ጥቃቶችን ከነመንስኤዎቻቸውና አይነታቸው ለይተው እንዲከላከሉና ከዚህም አልፈው ሲከሰቱ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ አቅም መፍጠር የሥልጠናው ዋነኛ አላማ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/19dN8uosE4/

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ መምራት እንደሚባ ተመላከተ፤
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ የአሰራር ማኑዋልና የአፈጻጸም ግምገማ ዙሪያ ከተቋማቱ የስራ አመራር ቦርድ አመራሮች ጋር ምክክር ተደርጓል ፡፡
-----------------------------------------------------
(ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በምክክሩ ወቅት እንደገለጹት ለፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ በተደራጀና በተቀባጀ አግባብ መምራት እንደሚባ አመላክተዋል፡፡
የዩኒቨርስቲ የስራ አመራር ቦርድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተግባርና ኃላፊነቶቻቸውን ብሎም የሚተገብሯቸውን የሪፎርም ስራዎች በውጤታማነት መፈጸምና ማከናወን እንዲችሉ የስራ አመራር ቦርድ የአሰራር ማኑዋለል መዘጋጀቱን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ተቋማቱ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸውና ተጨማሪ አቅምና አደረጃጀት የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ክቡር አቶ ኮራ አስረድተዋል፡፡
የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) በበኩላቸው የስራ አመራር ማኑዋሉም ሆነ የአፈጻጸም ግምገማ መስፈርቶቹ የተፈጻሚነት ወሰን ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/16jKH5oQJs/

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ።
የኢትዮጵያ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት "የከፍተኛ ትምህርት ለላቀ ተፅዕኖ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።
-----------------------------------------------------
(ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም) በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ ይህ ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ተግባራት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምን ያህል ለውጥ ተመዘገበ ተብሎ የሚገመገምበትና የወደፊት አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን ገልፀዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወዳዳሪ፣ የበለፀገች፣ ሉዓላዊት፣ ዴሞክራሲያዊት እና ፍትሃዊ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሚናቸው የጎላ መሆኑንም አንስተዋል።
በዚህም "የትምህርት ጥራት የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በገቡት የቁልፍ ተግባራት መለኪያ ውል መሠረት ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩና ባልተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ለመመካከር እድል ይፈጥራል ብለዋል።
በተጨማሪም መድረኩ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ልምድ ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1HqM5HKsed/

በአገሪቱ በተመረጡ 30 ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና መሰጠት ጀመረ።
በስልጠናው ከ84 ሺ የሚበልጡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ይሳተፋሉ፡፡
-------------------------------------------
(ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም) ስልጠናውን መስጠት ከጀመሩ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዲን የቆየዓለም ደሴ (ዶ/ር) ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን በጥሩ ሁኔታ ለማሰልጠን የአሰልጣኝ መምህራን ፣ የስልጠና ክፍሎች፣ የተማሪዎች ማደሪያ ፣ የካፍቴሪያ እና የማሰልጠኛ ሞጁልና ምዝገባ አጠናቆ ስልጠና መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው መምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት ዓይነት ፣ በማስተማር ስነ ዘዴ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም በስነ ልቦናዊ ፣ ማህበራዊና የጤና ጉዳዮችን አካቶ የያዘና ሰፊ ክፍተትን የሚሞላ በመሆኑ ሰልጣኞች ተረጋግተው መሰልጠንና የመጡበትን አላማ ሳይረሱ ክፍል ውስጥም ሆነ ከሌሎች ጓደኞቻቸውና ከአሰልጣኝ መምህራን ጋር መነጋገር እና መማር እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
https://www.facebook.com/share/p/1B56YnWyGA/

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን በመሙላት አቅም የሚገነባበት መሆኑ ተጠቆመ፤
ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
-----------------------------------------------
(ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም) የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ የህይወት ዘመን ትምህርት ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር እዮኤል አባተ (ዶ/ር) ስልጠናው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ይቸገሩበታል ተብሎ በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአገራችን ትምህርትን ከተማሪዎች ሀይወት ጋር አገናኝቶና ተግባር ተኮር አድርጎ በመስጠት ተማሪዎች ትምህርቱን ወደውትና ለህይወታቸውም የሚጠቀሙበትን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ከማድረግ አንጻር ክፍተት መኖሩን ዶ/ር እዮኤል አመልክተዋል፡፡
ስልጠናው ተማሪዎች እውቀት ወይም ሀሳብ (concept) ወደ መሬት አውርደው ከራሳቸው ህይወት እና ተግባራዊ ሊሆን ከሚችል የማስተማር ስነ ዘዴ ወይም ፍልስፍና ጋር አቆራኝተው መስጠት እንዲችሉ አቅማቸውን የሚገነቡበት መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠናው በትምህርት ስርዓታችን ላይ አለ የሚባለውን ዋና እና መሰረታዊ ችግር ሊፈታ የሚችል የአቅም ማጎልበቻ ፕሮግራም በመሆኑ በአግባቡ መከታተልና ተገቢውን እወቀትና ክህሎት መጨበጥ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1YBEbroskD/