Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
646 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም ያለችበትን ሁኔታ የተገነዘቡ፤ ሀገርን ከችግር ሊያወጡ የሚችሉ ጥናትና ምርምሮች በማድረግ እውነትና እውቀትን መሠረት ያደረገ ሀሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

-----------------------------------------------

(ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው በስተላለፉት መልዕክት አሁን ካለንበት የትምህርት ጥራት ችግር ለመውጣት ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ሪፎርሞች ተቀርፀው በትምህርት ሴክተሩ እየተተገበሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም ያለችበትን ሁኔታ የተገነዘቡ፤ ሀገርን ከችግር ሊያወጡ የሚችሉ ጥናትና ምርምሮች በማድረግ እውነትና እውቀትን መሠረት ያደረገ ነፃ ሀሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።

እንደ ህብረተሰብ እንዳንጠፋ ከፈለግን ይህንን የሚቋቋም ትውልድ ለመፍጠር በመሰረታዊነት በመናበብ ከላይ እስከ ታች እነዚህን ሪፎርሞች መተግበር ይገባናል ብለዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲኖረን እንፈልጋለን ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚኖር ውድድር በሚሰጡት የትምህርት ጥራት እና በሚሰሯቸው ጥናትና ምርምሮች ብቻ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/fdremoe/posts/pfbid02k8jk7CsNVMc8HpEDcxfLgkXK8Naic96xxsdpAn59kkgjXV6gfTm3WtWcWRSXcic2l
የአካቶ ትምህርት ማዕከላትን በማስፋትና በማጎልበት ረገድ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑ ተመላከተ።
--------------------------------------------
(ሀምሌ 30/ 2017 ዓ.ም) የአካቶ ትምህርት በስፋትና በትኩረት የሚተገበር ጉዳይ መሆኑን በአዲሱ የትምህርት ፓሊሲ ላይ ተመላክቷል።

በፓሊሲው የተቀመጠውን የአካቶ ትምህርት ትግበራ ከግብ ለማድረስ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በመከናወን ላይ ያሉ ጅምር ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዩሀንስ ወጋሶ ገልጸዋል ።

ትግበራውን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የተባባሪና አጋር ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚው አያይዘው ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፊንላንድ መንግስት ጋር በመተባበር "አካታችና ጥራት ያለው የመምህራን ስልጠና" (Teacher Education for Inclusion and Quality (TEFIQ) ፕሮጀክት ትግበራ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራን አቅም ለማጎልበትና የአካቶ ትምህርት ትግበራ ማዕከላትን ለማስፋትና ለማጎልበት በሚከናወኑ ተግባራት ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አመላክተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1QtomLxryH/
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን እንደ አንድ የሀገር ልጆች የሚቀበልበት የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮግራም ለጎንደር ብቻ ሳይሆን ለሀገሩም ምሳሌ የሚሆን መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ፤

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ እና ማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷ።

-------------------------------------------------------

(ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም) በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህ ክብረ በዓል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለጎንደርና ለአካባቢው ህዝብ ያለውን ፋይዳ እንዲሁም ህዝቡ ለተቋሙ ያለውን አክብሮት ያየንበት ነው ብለዋል።

በዓሉ ከዩኒቨርሲቲውና ከሆስፒታሉ ምስረታ በላይ በተለይ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የጎንደርን ህዝብ ጥልቅ የሆነ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያንፀባረቀበትም እንደነበር አንስተዋል።

በተለይም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን እንደ አንድ የሀገር ልጆች የሚቀበልበት “የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮግራም” ለጎንደር ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንዲያደርጉ የምንፈልገው የመንደር ሳይሆኑ የሀገር ሀብት እንዲሆኑ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፤

በተለይ አሁን ዋና ሪፎርም ዩኒቨርሲቲዎች ራሳቸውን እንዲችሉ በነፃነት የሚሰሩ፣ በነፃነት የሚያስቡ እውነትንና እውቀትን የሚፈልጉ ሰዎች የተሰባሰቡባቸው ሰላማዊ ቦታ እንዲሆኑ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1D3gaudqWn/
በህጻናት ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች ሥር እየሰደዱ መምጣታቸው አሳሳቢ መሆኑ ተገለጻ።
========================
(ነሃሴ 2/2017 ዓ.ም) በህጻናት ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ለመከላከል ከመላ ሀገሪቱ ከተውጣቱ የተማሪ ወላጅ ህብረት አመራሮችና አባላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደጥናት ተካሂዷል።


በአውደ ጥናቱ መከፈቻ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን የኤችኣይቪ ሥርጭት፣ያልታቀደ እርግዝና፣ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና የህጻናት ጋብቻ ችግሮች በበርካታ አካባቢዎች ሥር እየሰደዱ መምጣቸው ጥናቶች እንደሚያመላክቱ ገልጸው ይህም አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።


አክለውም ተሳታፊዎች ከዚህ ስልጠና እንደተመለሱ ወደ ስራ ለመግባት የድርጊት መርሃ-ግብር ማዘጋጀታቸውን ጠቅሰው በዚህም ማህበረሰቡ ለልጆቹ ደህንነትና ትምህርት ትኩረት በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ ቀጣይነት ያለው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤https://www.facebook.com/share/p/1B45SQpyi1/
ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ባስገነባቸው ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍልን ካጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል አወዳድሮ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ከነሐሴ 05/2017 እስከ ነሐሴ 15/2017 ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለመመዝገን ይህንን ሊንክ መጠቀም ትችላላችሁ።
https://sbs.moe.gov.et/apply