Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
646 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
እንደ ሀገር ፕሮጀክቶች ጀምሮ በፍጥነት ማጠናቀቅ በትምህርት ቤቶችም ባህል እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ።
------------------------------------------

(ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በሲዳማ ክልል ያለውን የትምህርት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚሁ ጊዜ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በትምህርት ቤቶቹ ተገኝተው ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።

በተለይም በወንዶ ገነት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው የመማሪያ ህንፃ በ8 ወር ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን ተመልክተዋል።

ይህም እንደ ሀገር ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የሚለው ባህል እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ያሉ ሲሆን ሌሎች ክልሎችም ከዚህ ልምድ ሊወስዱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የሲዳማ ተሃድሶ በሚል የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተሠሩ ሥራዎችን አብራርተዋል።

በተለይም እንደ ክልል ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት ተመሳሳይ ስታንዳርድ ያላቸው 78 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአዲስ መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።

የጉብኝቱ ዓላማም በክልሎች መካከል ልምድ መለዋወጥ መሆኑም ተገልጿል።
በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገራዊ ምክክር መድረክ የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት ውጤት አመላካች መለኪያዎች ላይ የጋራ ስምምነት በመፈራረም ተጠናቋል።

----------------------------------------------

(ነሐሴ 16/2017 ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ሲያካሄድ የነበረው የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገራዊ የምክክር ከሁሉም የክልልና ከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት ውጤት አመላካቾችን የስምምነት ሰነድ በመፈራረም አጠናቋል።

መድረኩ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የተመከረበትና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከመግባባት የተደረሰበት መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የትምህርት ተሳትፎ፣ ጥራትና ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ረገድ በ2017 የትምህርት ዘመን የተገኙ ስኬቶችን በማስፋትና በማስቀጠል በመጭው አመት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መድረኩ በመምከር አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በዘርፉ የአፈጻጸም ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶች በመሻገር በ2018 የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረትም እንዲሁ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የተመከረበት እንደሆነም ክብርት ሚንስትር ዴኤታዋ አያይዘው ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1UQesBy5es/
በ2017 የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ እቅድ አፈጻጸም መሳካት መምህራን ለነበራቸው ሚና እውቅና ተሠጠ።
--------------------------------------------
(ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም) በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ2017 የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም መሳካት የኢትዮጵያ መምህራን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ስጥቷል።

ለሁለት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ በነበረው የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ማጠናቀቂያ ላይ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በዘርፉ የ2017 የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም ሂደት ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ተመስግነዋል።

በመማር ማስተማር፣ በትምህርት ለትውልድ፣ በትምህርት ቤት ምገባ እንዲሁም በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ ስራዎች የተሳኩ እንዲሆኑ ከመምህራን በተጨማሪ የተማሪ ወላጆች ህብረትም ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስቴሩ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን በመጪው አመት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል ሁሉም የዘርፉ ተዋንያኖች ሚናቸውን በተጠናከረ መልኩ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት አሁን ላይ በትምህርቱ ዘርፍ የምንሰራቸው ስራዎች ትክክለኛነት የመጪው ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወስኑ በመሆናቸው ሀላፊነታችንን መወጣት ይገባልም ብለዋል።

በማያያዝም የበለጸገችና ያደገች ሀገር ለመፍጠር ሁሉም የትምህርት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ባለድርሻ አካል በሚፈለገው ልክ መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል።
ማስታዋቂያ
በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉ ተመሳሳይ ጾታ መንትዮች፣ የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም የተለያዩ የጤና ዕክል ያለባቸው ተማሪዎች የ 2017 ዓ.ም 12ኛ መልቀቂያ ፈተና ውጤት እስኪገለጽ ድረስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።
የሚያስፈልጉ ሰነዶች
1. ለተመሳሳይ ጾታ መንትያ አመልካቾች
1.1. የሁለቱም አመልካቾች የልደት ካርድ
1.2. ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ

2. የሚያጠቡ እናት አመልካቾች
2.1. ስድስት (6) ወር ያልሞላው የህጻኑ/ኗ የክትባት ካርድ
2.2. ከተማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3. የተለያዩ የጤና ዕክል ያለባቸው አመልካቾች
3.1. ከመንግስት ሆስፒታሎች የቦርድ ወሳኔ የተሰጠበት የህክምና የምስክር ወረቀት
3.2. ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ የመያስፈልጉ መሆኑን እንገልጻለን።
የትምህርት አገልግሎትን ከትርፍ ጋር ብቻ አያይዞ መሥራት ሀገርን እንደሚጎዳ ተገለጻ፡፡
---------------------------------------------
(ነሃሴ 20/2017 ዓ.ም) የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላይ አገልግሎት እየሰጡ ባሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባካሄደው የዳግም ምዝገባ አፈጻጸም ዙሪያ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት አገልግሎትን ከትርፍ ጋር ብቻ አያይዞ መሥራት ሀገርን እንደሚጎዳ ገልጸዋል፡፡

መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተጠናው ጥናት መሠረት በተካሄደውና በቀጣይ በሚካሄደው ምዘና ዝቅተኛ የምዘና መስፈርቶችን የማያሟሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሥርዓቱ እንዲወጡ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከሀገር ወቅታዊና የወደፊት ፍላጎት እንዲሁም ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር በመቃኘት መምራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም ይህ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የተጀመረው የብቃት ምዘና ሥራ ያለ ምንም ማዳላት በተመሳሳይ መልኩ በመንግሥት ተቋማት ላይም ተግባራዊ እንደሚሆንም ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19fvNZn2Q7/
ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ለተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የፕሮግራም ኮዲንግና አልጎሪዝም ስልጠና ተሰጠ፤

-------------------------------------------------

(ነሃሴ 20/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል ዕወቀት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት አለሙ እንደገለጹት ስልጠናው የተሰጠው ከሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ለተውጣጡ አንድ መቶ ሃያ አንድ ከ9ኛ-11ኛ ክፍል ላሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ከአዲስ ኮደር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው አገር አቀፍ የክረምት ስልጠና መርሃ ግብር ተማሪዎቹ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግና አልጎሪዝም ፕሮግራሞች ዙሪያ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ እውቀት እንዲጨብጡ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ መርሃ ግብር አጋዥ መሆኑን ኃላፊዋ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ኮደር ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጂላኔ ኔልሰን በበኩላቸው በአልጎሪዝምና ፕሮግራሚንግ ላይ አተኩሮ ለአራት ሳምንታት በተሰጠው ስልጠና ከመላ አገሪቱ የተመለመሉና ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1DxmMJYaD5/