Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
646 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር ከቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር አለም አቀፍ የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ ማዕከል ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሠነድ ተፈራረመ።

(ነሃሴ 23/2017 ዓ.ም)ትምህርት ሚኒስቴር ከቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር አለም አቀፍ የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ ማዕከል ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሠነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የተቋም ለተቋም ግንኙነትን በማጠናከር የሁለቱ ሀገራት የእውቀትና ክህሎት ሽግግርን ለማሳለጥ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ስምምነቱን በፈረሙበት ወቅት የቻይና መንግስት በኢትዬጵያ የትምህርት ልማት ዘርፍ ውስጥ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል

ሚኒስትር ድኤታው በማያያዝም ስምምነቱ ሀገራዊ ፍላጎት ላይ መሠረት በማድረግ በተለይም በማደግና በመስፋፋት ላይ ያሉ የዲጂታል፣ ሠው ሠራሽ አስተውሎ ፣ ሳይበር ሴኪዩሪቲና መሠል ትብብሮች ላይ የቻይና ባለሙያዎችንና ተቋማትን ድጋፍ እንደሚሹ አስገንዝበዋል።

መሠል ትብብሮች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን በማጠናከርና ቅርርቦሽን በመፍጠር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አጋርነትና ትብብር በበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ሚንስትር ድኤታው በማያያዝ ገልጸዋል።

የቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር አለም አቀፍ የህዝብ ለህዝብ ማዕከል ሀላፊ ዩ ቻንግሺዩ በበኩላቸው ቻይና አሁን ለደረሠችበት የእድገት ደረጃ የአለም አቀፍ ትብብር ያለው ሚና ወሳኝ መሆኑን ትገነዘባለች ያሉ ሲሆን በትምህርትና ተያያዥ ልውውጦች ከኢትዮጵያ ጋር ተባብሮ ለመስራት ፍላጎት ያላት መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/17D1bheXY5/
የምርምርና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደገበያ የማስገባት ተግባር የሪፎርም አካል ተደርጎ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑ ተገለጸ።

-----------------------------------------------

(ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም) ለዩኒቨርሲቲ እንዱስትሪ ትስስር ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተሮችና የኢንኩቤሽን ማዕከላት አስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ፣ የምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰራዊት ሃንዲሶ (ዶ/ር) በስልጠናው ላይ እንደገለጹት የምርምርና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደገበያ የማስገባት ሥራ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደዋና ዕቅድ ተይዞ እየተሰራበት ይገኛል።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙ 27 የኢንኩቤሽን ማዕከላትን የማጠናከርና ያላቋቋሙትም እንዲያቋቁሙ እየተደረገ መሆኑንም ዶ/ር ሠራዊት ተናግረዋል።

የኢንኩቤሽን ማዕከላት ማቋቋም የሥራ አጥነትን ችግር በማቃለል፣ የተግባር ልምምድ ለማድረግ በተለይም ክህሎትና ሥራ ፈጠራ ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚያስችልም መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማስፋፋት በተለያዩ የትምህርት መስኮች መካከል ሊኖር የሚችለውን መስተጋብርና ቅንጅት የተሻለ በማድረግ ፈጠራና የሳይንስ ዕውቀት እንዲዳብር ለማድረግ እንደሚያግዝም ዶ/ር ሠራዊት ጨምረው አስረድተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19okrrfmXY/
ማስታወቂያ
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን አወዳድረን ለመቅጠር የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል።
ነገር ግን የዘንድሮ የክረምት ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና የተጠናቀቀው በቅርቡ በመሆኑ ምዝገባውን ማራዘም አስፈልጓል። በመሆኑም ምዝገባው እስከ ጳጉሜን 05/2017 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑንን እየገለጽን ለማመልከት ፍላጎቱ ያላችሁ መምህራን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እድትመዘገቡ በድጋሚ እንገልጻለን ። ለመመዝገብ https://sbs.moe.gov.et/career/teacher ይጠቀሙ
በትምህርት ሚኒስትሩ የተመራ የልዑካን ቡድን በቺሊ ሳንቲያጎ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተሳትፏል።

--------------------------------------------------

(ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም) ይህ አለም አቀፍ ጉባኤ በቺሊ ፕሬዚዳንት ገብርኤል ቦሪቼ እና በዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ አማካኝነት የተመራ ሲሆን በሀገራት ደረጃ የኤሰ ዲ ጂ 4 እድገትን ለማፋጠን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ አፍሪካን በመወከል የኢትዮጵያ እና የኮትዲቫር የትምህርት ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት በ2030 የትምህርት ዘላቂ ግብን ለማሳካት በሁሉም ሀገራት በተለይም በታዳጊ ሀገራት በርካታ ሥራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

አክለውም የአፍሪካ ሀገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ የመጣውን የውጭ እርዳታ መተማመናቸውን በመተው ከችግሮቻቸው ለመውጣት ህብረተሰቡን በማስተባበር በራስ አቅም መንቀሳቀስ ዘላቂ ልማትና እድገት ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ እየሰራች ያለውን ሥራ ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ በተለይም በትምህርት ለትውልድ የትምህር ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ ፣ በቅድመ መደበኛ ትምህርት፣ በትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃግብር ረገድ የተገኙ ስኬቶችን በመድረኩ አብራርተዋል።

በዚህ አለም አቀፍ ጉባኤ የ28 ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ፣ ኤጀንሲዎች፣ የሼርፓ ቡድን ከፍተኛ የቴክኒክ ቡድን ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ክቡር ሚኒስትሩ ከጉባኤው በተጓዳኝ "በመምህራን ላይ የዓለም ጉባኤ" በሚል ርዕስ በተካሄደ መድረክ ላይም ተሳትፈዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከክፍል ከሚሰጠው እውቀት ባሻገር በክህሎትና በአመለካከት ስራ ፈጣሪ ሆነው መውጣት እንዳለባቸው ተጠቆመ፤

የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ስራና ስራ ፈጣሪነት ዙሪያ ተገቢውን ክህሎትና አመለካከት ይዘው መውጣት እንዲችሉ ማዕከላትን ማቋቋም (Center for Employment and Entrepreneurship Development) በሚቻልበት ሁኔታ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
====================
(ጳጉሜን 1/2017 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና ውይይቱን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሥራ ፈጣሪነት አመለካከትና ክህሎትን እንዲለበሱ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው ተቋማቱ ማዕከላቱን በበቂ ግብዓት ማደራጀት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎቻቸው እውቀት ብቻ ከማስተላለፍ አውድ ወጥተው ወደ ስራ ፈጠራ ስርዓተ-ምህዳር ለውጥ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመው ማዕከላቱ በቀጣይ የሚመጥናቸውን የሰው ሀይልና አደረጃጀት አንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑንም ተናገረዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የመምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ሀላፊ አቶ በየነ ተዘራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ያገኙትን እውቀት ከአለማችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እያገናዘቡ ወደ ተግባር መቀየርን የሚለማመዱበትና የሥራ ፈጠራ አመለካከትና ክህሎት የሚያሳድጉበትን ማዕከል እንደ አንድ ወሳኝ የመማር ማስተማሪያ ግብዓት በመቁጠር አቋቁመውና አጠናክረው መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1JfjQhpzkD/
የ2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ፤ትምህርት ሚኒስቴር
ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሞባይል ስልክ ፣ ታብሌትና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዞ ትምህርት ቤት መምጣት ተከልክሏል፡፡

----------------------------------------

(ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች አከፋፈት አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር ባደረገበት ወቅት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 5/ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል።

በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት ዓርብ መስከረም 2 / 2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበትና መስከረም 5/2018 ዓ.ም ደግሞ በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑንም ክብርት ወ/ሮ አየለች አስታውቀዋል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19VhCdzuyH/
ጳጉሜ 2 የህብር ቀን “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ቃል ተከበረ፤
የትምህርት ፣ የሠላም፣ የፍትህ እና የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር መ/ ቤቶች የህብር ቀንን '' ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ '' በሚል መሪ ቃል በጋራ አክብረዋል።

------------------------------------------------

(ጳጉሜን 2/ 2017 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ቀኑ በፓናል ውይይቱ በተከበረበት ወቅት እንደገለጹት ብዝሃነት የሀገራዊ ስኬቶቻችን መሠረት በመሆኑ የወል ትርክት ግንባታን ማጠናከር ከሁላችንም እንደሚጠበቅ ጠቁመው የብዝሃ ኢትዮጵያ ጌጦችን ማጽናትና በቀጣይም አዳዲስ ድሎችን በማስመዝገብ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ከዚህ ጋር አያይዘው ለጋራ ራዕያችን እውን መሆን ብዝሃነትን በማስተናገድ የተገነባ ጠንካራ አገራዊ አንድነት፣ መተሳሰብ፣ መቻቻል፣ ፍቅርን በይቅርታ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ክብርት ወ/ሮ አየለች አክለውም ትምህርት ቤቶች የብዝሃ ኢትዮጵያ መገለጫ በመሆናቸው በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ብዝሃነትን የሚቀበሉ፣ የሚከባበሩ፣ የሚተሳሰቡ ፣አብሮ ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑ ዜጎችን በመፍጠር የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከታችኛው እርከን ጀምሮ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17PZ4ahyrk/