Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
646 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ተደርጓል።
***//

የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ማጠናቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡

ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡

አድራሻዎቹ፡
1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot
3.  አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284
የ2018 ዓ.ም ትምህርት መማር ማስተማር ስራ በመላ ሀገሪቱ ተጀምሯል።

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሂደቱን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል።

-------------------------------- // ----------------------------

(መስከረም 05/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘዋውረው የ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመርን ምልከታ ባደረጉበት ወቅት በትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማሩን ስራ በማሻሻል ተማሪዎች በቂ እውቀት እና ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ውጤታማነታቸው እንዲሻሻል ሁሉም አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡

ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ተማሪዎችም ለትምህርታቸው ትኩረት በመስጠት ማጥናትና ጊዜያቸውን በፕሮግራም ለትምህርት ስራ ማዋል እንደሚጠበቅበቸው ተናግረዋል፡፡

መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችም በትምህርት ዘመኑ ለተማሪዎች የሚሰጡትን እውቀት በላቀ ደረጃ በማሳደግ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የተማሪዎች ስነ ምግባር ለትምህርት ስራ ወሳኝ በመሆኑ ተማሪዎች በሰነ ምግባር የታነጹ በአለባበሳቸውና በስነ ምግባራቸው ለሌሎች ምሳሌ ሊሆኑ እንደሚገባ ክብርት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል፡፡
ተቋማት ከተልዕኳቸው አንጻር ተገቢነት ባላቸው የትምህርት መስኮች ብቻ ላይ ትኩረት አድርገው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ፤

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ "በአዲስ ምዕራፍ ዋዜማ" በሚል መሪ ቃል ዩኒቨርሲቲውን በአዲስ የማደራጀት ሪፎርም ማስጀመሪያ ውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡


---------------------------- // ---------------------------

(መስከረም 5/2018 ዓ.ም) በመድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ሰቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰቡን ወቅታዊና የመጪውን ጊዜ ፍላጎት ማሟላት የሚችሉ ብቃትና ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ የህዝብ አገልጋዮችን ማፍራት እንዲችል ከተልዕኮው አንጻር ተገቢነት ባላቸው የትምህርት መስኮች ብቻ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እየተተገበረ ያለውን ሀገራዊ የሪፎርም ሥራ መሸከም የሚችል ተቋምና ሲቪል ሰርቫንት ለማፍራት በሚያስችል መልኩ እራሱን መልሶ ማደረጃት እንደሚገባው አንስተዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ኢትዮጵያ መድረስ በምትፈልገው የዕድገትና የስልጣኔ ደረጃ ላይ መድረስ የሚያስችል የመንግሥት አገልግሎት መሪዎችና ባለሙያዎችን ማፍራት የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር ሊከተል እንደሚገባም ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19sHior8sm/
የትምህርት ሚኒስትሩ የ Foreign, Commonwealth & Development Office (FCDO) የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተርን በጽ/ቤታቸው ተቀበለው አነጋገሩ።
------------------------//-------------------
(መስከረም 07/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በእንግሊዝ መንግስት የFCDO የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተመደቡትን Amanda McLoughlin በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በኢትዮጵያ በሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ የሪፎርም ተግባራትን እየተገበረች መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራት የበለጠ እንዲሳኩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቅድሚያ ትኩረት በሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19djC3coFz/
የትውልዱን ስኬታማነት ለማረጋገጥ በኤችኣይቪ ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

---------------------------- // ------------------------

(መስከረም 8/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቷ ለሚገኙ የመምህራን ኮሌጆች የተለያዩ ክበብ ተጠሪ መምህራን ጋር ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ልማት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰግድ መሬሳ የወጣቱን ትውልድ ሁለንተናዊ ስኬታማነት ለማረጋገጥ በኤችኣይቪ ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የትምህርት ሥርዓቱ ውጤታማነት የሚረጋገጠው በክፍል ውስጥ ከሚሰጠው መደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን በተጓዳኝ በሚሰጡ የህይወት ክህሎት ሥልጠናዎችና እውቀቶች መሆኑን ጠቅሰው የኮሌጅ መምህራን የተጓዳኝ ትምህርት ክበባት በሚገባ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የብሄራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሃፊ አቶ አለሙ ጌታሁን በበኩላቸው በህይወት ክህሎት ሥልጠና እጥረት ምክንያት የኤችአይቪ ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮች የወጣቱ ትውልድ ስጋት ሆነው መቀጠላቸውን ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ጠቅሰው የመምህራን ኮሌጆች ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አክለውም በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ክበባት በውጤታማነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ሥልት የሚቀመጥም መሆኑን ተናግረዋል።

የኮሌጅ መምህራኑም ወደየ መጡበት ሲመለሱ በኤች አይቪና ስነተዋልዶ የሚሰሩ ክበባትን እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የማጠናከር ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።
የትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤት መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ ከተባበርን የትምህርት ዘርፉን ማሳደግ እንደምንችል ያሳየ ነው፤ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥራት ያለው “ትምህርት ለአገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የ2018 የትምህርት ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

------------------------ // ----------------------

(መስከረም 08/2018 ዓ.ም )ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተጠናቀቀው የ 2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል።

በተለይ በክልሉ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ለ12ኛ ክፍል ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች 22 በመቶ የሚሆኑትን ማሳለፍ መቻሉ በክልሉ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ትምህርት አገራችንን ወደ ቀድሞ ታላቅነትና ገናናነት ክብር የሚያሻግር ነው ነው ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ በክልሉ የትምህርት ጥራት፣ተደራሽነትና ተሳትፎን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ስርዓቱ የነበሩ ስብራቶችን በመለየትና ስትራቴጂዎችን በማውጣት በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ መምጣቱን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1FUcpxaNbU/