Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የትምህርት ሚኒስትሩ የ Foreign, Commonwealth & Development Office (FCDO) የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተርን በጽ/ቤታቸው ተቀበለው አነጋገሩ።
------------------------//-------------------
(መስከረም 07/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በእንግሊዝ መንግስት የFCDO የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተመደቡትን Amanda McLoughlin በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በኢትዮጵያ በሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ የሪፎርም ተግባራትን እየተገበረች መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራት የበለጠ እንዲሳኩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቅድሚያ ትኩረት በሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19djC3coFz/
የትውልዱን ስኬታማነት ለማረጋገጥ በኤችኣይቪ ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

---------------------------- // ------------------------

(መስከረም 8/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቷ ለሚገኙ የመምህራን ኮሌጆች የተለያዩ ክበብ ተጠሪ መምህራን ጋር ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ልማት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰግድ መሬሳ የወጣቱን ትውልድ ሁለንተናዊ ስኬታማነት ለማረጋገጥ በኤችኣይቪ ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የትምህርት ሥርዓቱ ውጤታማነት የሚረጋገጠው በክፍል ውስጥ ከሚሰጠው መደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን በተጓዳኝ በሚሰጡ የህይወት ክህሎት ሥልጠናዎችና እውቀቶች መሆኑን ጠቅሰው የኮሌጅ መምህራን የተጓዳኝ ትምህርት ክበባት በሚገባ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የብሄራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሃፊ አቶ አለሙ ጌታሁን በበኩላቸው በህይወት ክህሎት ሥልጠና እጥረት ምክንያት የኤችአይቪ ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮች የወጣቱ ትውልድ ስጋት ሆነው መቀጠላቸውን ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ጠቅሰው የመምህራን ኮሌጆች ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አክለውም በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ክበባት በውጤታማነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ሥልት የሚቀመጥም መሆኑን ተናግረዋል።

የኮሌጅ መምህራኑም ወደየ መጡበት ሲመለሱ በኤች አይቪና ስነተዋልዶ የሚሰሩ ክበባትን እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የማጠናከር ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።
የትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤት መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ ከተባበርን የትምህርት ዘርፉን ማሳደግ እንደምንችል ያሳየ ነው፤ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥራት ያለው “ትምህርት ለአገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የ2018 የትምህርት ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

------------------------ // ----------------------

(መስከረም 08/2018 ዓ.ም )ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተጠናቀቀው የ 2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል።

በተለይ በክልሉ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ለ12ኛ ክፍል ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች 22 በመቶ የሚሆኑትን ማሳለፍ መቻሉ በክልሉ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ትምህርት አገራችንን ወደ ቀድሞ ታላቅነትና ገናናነት ክብር የሚያሻግር ነው ነው ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ በክልሉ የትምህርት ጥራት፣ተደራሽነትና ተሳትፎን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ስርዓቱ የነበሩ ስብራቶችን በመለየትና ስትራቴጂዎችን በማውጣት በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ መምጣቱን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1FUcpxaNbU/
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተማሪዎችን የማንበብ ክህሎትና ፍላጎትን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ።

አለም አቀፍ የንባብ ቀን "በቴክኖሎጂ ዘመን ንባብን ማዳበር" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ተከብሯል።

----------------------------// -----------------------------

(መስከረም 09/2018 ዓ.ም) በመድረኩ ላይ የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለመሄድ የተማሪዎችን የንባብ ክህሎትን በየጊዜ ማሳደግ እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ይጠበቃል፤ ለዚህም ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ትምህርትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች በጥራት ለማድረስ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆ እየተተገበረ ሲሆን በተለይም አዲስ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ፀድቆ ወደ ተግባር ገብቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የነገው ትውልድ እጣፈንታ የሚወሰነው ዛሬ መሠረቱ ላይ በሚሰራው ሥራ በመሆኑ የልጆችን የንባብ ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የልጆች የማንበብ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቶ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል የተባለ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት መሥራት ይጠበቃል።

በተለይም ቴክኖሎጂ የዚህ ዘመን ስጦታ ቢሆንም አጠቃቀሙን መግራትና እኛ በምንፈልገው መልኩ በመጠቀም የንባብ ባህላችን መመለስ የሁላችን ጉዳይ ሊሆን ይገባል ተብሏል።

በመድረኩም የኢትዮጵያ ቤተመፅሃፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት እና ኢትዮጵያ ታንብብ የተባለ ድርጅት የተማሪዎችን የንባብ ባህል ሊያዳብሩ የሚችሉ የተለያዩ መጽሐፍትን ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።

ይህ ባለፈው ሳምንት በአለም ለ58 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ የተከበረው የአለም የንባብ ቀን ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጋር በትብብር የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።
እየተቀየረ ያለውን የአለም ሁኔታ ሊሸከሙ የሚችሉ በሁሉም ዘርፍ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ተወዳዳሪ ልጆችን ማፍራት እንደሚገባ ተጠቆመ።

ትምህርት ሚኒስቴር በሀረሪ ክልል የሚያስገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚኒስቴሩና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።

------------------ // ------------------------

(መስከረም 09/2017 ዓ.ም) በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ሥርዓቱ መጪውን ዓለም መሸከም የሚችሉ እውቀትና ክህሎት ያላቸው በራሳቸው የሚተማመኑ ተወዳዳሪ የሆኑ ልጆችን ማፍራት ይገባል፤ ለዚህም የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በተለይም በትምህርት ያለው ኢፍትሃዊነትን በማስቀረት ዜጎች እኩል ትምህርት በማገኘት እኩል ተወዳድረው የሚማሩበትን ሥርዓት መፍጠር አለብን ብለዋል።

ለዚህም 50 ሞዴል እንዲሁም 13 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመገንባት ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

ይህም ሁሉም ዜጎች እኩል ተወዳድረው ውጤት የሚያገኙበትን ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ ይህ ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1777uVaWXV/
የቅጥር ማስታዎቂያ
የትምህርት ሚኒስቴር ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ት/ቤቶች የአሰተዳደርና ፋይናንስ ቡድን መሪ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ከላይ በቴምፕሌቱ የተጠቀሱ መስፈርቶችን የምታሟሉ በ https://sbs.moe.gov.et/career በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።