Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ልጆቻችንን በጥራት ካስተማርናቸው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመወዳደር ብቃትና ችሎታ አላቸው፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የሆጤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ ተመርቋል።
--------------------- // ----------------------
(መስከረም 28/2018 ዓ.ም) በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የሆጤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአማራ ክልል በሰሜኑ ጦርነት የተጎዱ 45 ትምህርት ቤቶች ግንባታ መጠናቃቸውንና ሰባት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ እየተገነቡ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ወደፊት ይችን ሀገር የሚመሩ ልጆችን ለማፍራት በትኩረት እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የአንድ ሀገር እድገት የሚረጋገጠው በትምህርት ላይ በሚሰራ ስራ በመሆኑ የትምህርት ስብራቱን ለማስተካል የተለያዩ የለውጥ እርምጃዎች እየተተገበሩ መሆኑን አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/17URKmXJcE/
ሴት ተመራማሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ሴቶች በምርምርና ፈጠራ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፤
---------------------------------------------------------
‎(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራንና ተመራማሪዎች የተካተቱበት የኢትዮጵያ ሴት ተመራማሪዎች ማህበር ምስረታ እውን ሆኗል።
‎
‎በምስረታው ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ባስተላለፉት መልዕክት ሴት ተመራማሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ሴቶች በምርምርና ፈጠራ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ሚናቸውን በሚገባው ልክ መወጣ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።፡
‎
ማህበሩ ሴት ተመራማሪዎች አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት መልካም አጋጣሚዎችን እንዲጠቀሙና ተተኪ ሴት አመራሮችን ለማፍራትና እርስ በርስ ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና የሚረዳዱበትን እድል እንደሚፈጥር ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ ገልጸዋል፡፡
‎
‎ ሴት ምሁራንና ተመራማሪዎች ያካበቱትን ልምድና እውቀት የህጻናት ትምህርትን ፣ ድህነትን ፣የሴቶች ተሳታፎና ተጠቃሚነትን የሚገድቡ ችግሮችን በጥናትና ምርምር ስራዎች በመደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/1Bt1LWd7xP/
ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ዙሪያ ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ተፈራረመ ፤
-------------------------- // --------------------
(መስከረም 30/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት (Performance contract) የዩኒቨርሲቲዎቹ የቦርድ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን መሠረት በማድረግ ቆጥረው የወሰዱትን ተግባራት አፈጻጸም ጥራትና ተዓማኒት ባለው መረጃ አስደግፈው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበረ ያለው የመስክ ልየታ ፕሮግራም የአካባቢያቸውን ጸጋ እና በሂደት ያካበቱትን እምቅ አቅም አስተውለው በመለየት የየራሳቸው ተፈላጊነትና ተወዳዳሪነት እንዲኖሯቸው የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው ተቋማቱ በተማሪዎች ዘንድ ተመራጭ ለመሆኑ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Fc6nSzWLq/
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትረው ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
-------------------------- // ----------------------------
(ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም) የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር፣የማህበረሰብ ጉድኝትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ጊዜ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች ወደ ገበያ ሲገቡ commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትሪው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡

አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ፈጠራና ተቋማቱ በቅንጅትና በትብብር መሥራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የየራሳቸውን የንግድ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ማበልጸጊያ (incubation centers) ማዕከላት ያላቋቋሙ ተቋማት በአፋጣኝ አቋቁመው ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1DfgngLVJp/