Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ሴት ተመራማሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ሴቶች በምርምርና ፈጠራ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፤
---------------------------------------------------------
‎(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራንና ተመራማሪዎች የተካተቱበት የኢትዮጵያ ሴት ተመራማሪዎች ማህበር ምስረታ እውን ሆኗል።
‎
‎በምስረታው ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ባስተላለፉት መልዕክት ሴት ተመራማሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ሴቶች በምርምርና ፈጠራ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ሚናቸውን በሚገባው ልክ መወጣ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።፡
‎
ማህበሩ ሴት ተመራማሪዎች አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት መልካም አጋጣሚዎችን እንዲጠቀሙና ተተኪ ሴት አመራሮችን ለማፍራትና እርስ በርስ ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና የሚረዳዱበትን እድል እንደሚፈጥር ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ ገልጸዋል፡፡
‎
‎ ሴት ምሁራንና ተመራማሪዎች ያካበቱትን ልምድና እውቀት የህጻናት ትምህርትን ፣ ድህነትን ፣የሴቶች ተሳታፎና ተጠቃሚነትን የሚገድቡ ችግሮችን በጥናትና ምርምር ስራዎች በመደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/1Bt1LWd7xP/
ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ዙሪያ ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ተፈራረመ ፤
-------------------------- // --------------------
(መስከረም 30/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት (Performance contract) የዩኒቨርሲቲዎቹ የቦርድ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን መሠረት በማድረግ ቆጥረው የወሰዱትን ተግባራት አፈጻጸም ጥራትና ተዓማኒት ባለው መረጃ አስደግፈው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበረ ያለው የመስክ ልየታ ፕሮግራም የአካባቢያቸውን ጸጋ እና በሂደት ያካበቱትን እምቅ አቅም አስተውለው በመለየት የየራሳቸው ተፈላጊነትና ተወዳዳሪነት እንዲኖሯቸው የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው ተቋማቱ በተማሪዎች ዘንድ ተመራጭ ለመሆኑ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Fc6nSzWLq/
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትረው ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
-------------------------- // ----------------------------
(ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም) የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር፣የማህበረሰብ ጉድኝትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ጊዜ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ምርምሮች ወደ ገበያ ሲገቡ commercialization ተኮር ከመሆን በተጨማሪ መነሻና መዳረሻቸው ህብረተሰቡና ኢንዱስትሪው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡

አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ፈጠራና ተቋማቱ በቅንጅትና በትብብር መሥራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የየራሳቸውን የንግድ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ማበልጸጊያ (incubation centers) ማዕከላት ያላቋቋሙ ተቋማት በአፋጣኝ አቋቁመው ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1DfgngLVJp/
የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ፡፡
=======================

(ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበሰውን ብሄራዊ የሠንደቅ አላማ ቀንን አክብረዋል፡፡

በክበረ-በዓሉ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያና መሠባሠቢያ መሆኑ አንስተዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሀገራችንን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ከፍታ አስጠብቀን ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ አደራ በዚህ ትውልድ ላይ የተጣለ መሆኑን አመላክተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘይ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17CNpuNiDc/