Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
646 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተጠናቋል፤
ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን ወስደዋል፡፡

---------------------------- // ---------------------------

(ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም) የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና በተያዘለት ጊዜና አግባብ ተጠናቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱንም ዶክተር ኤባ ገልጸዋል፡፡

ፈተናውን በመንግስትና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመዝግበው ለመማር ፍላጎት ያላቸው 29ሺህ 491 አመልካቾች ተመዝግበው 96 በመቶ ያህሉ ፈተናውን መውሰዳቸውን መሪ ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1H4nonCZxk/
በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ሥልጠና ረቂቅ ደንብ ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

-------------------------- // ------------------------

(ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም) በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራም በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስያሜ ተሰጥቶት ሲተገበር መቆየቱን አንስተዋል።

ይህ ፕሮግራም ለዜጎች አማራጭ የትምህረትና ሥልጠና እድል በማቅረብ ረገድ አስተዋፅኦው የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ፕሮግራሙን በውጤታማነት ለመተግበር እንዲቻል የአጠቃላይ ትምህርት አዋጁን መነሻ በማድረግ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

ከዚህ አንጻር በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ የሚመለከታችው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ምክክር በማስፈለጉ እና ግብአት የሚሰበሰብበት ስለሆነ ይህ መድረክ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል ።

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮሴፍ አበራ(ዶ/ር) በበኩላቸው ከዚህ በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሴክተሮች ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ፕሮግራሙ በቅንጅት ሲተገበር መቆየቱን አንስተዋል።


ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ አዲስ ከተሾሙት የሀንጋሪ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።
---------------------------//--------------------------
(ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የሀንጋሪ አምባሳደር አቲላ ቶዝን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና ሀንጋሪ በትምህርቱ ዘርፍ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።

በተለይም በ2023 በትምህርት ሚኒስቴርና በሀንጋሪ ኢምባሲ በኩል የተፈረመውን የነጻ የትምህርት እድል ስምምነት በተመለከተ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት አንስተው ተወያይተዋል።

በዚሁ ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ ይህንን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ አስተካክሎ ለሀገራችን ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጠቃሚ በሆኑ የትኩረት መስኮች በተለይም በፔትሮ ኬሚካል፣ በኒውክለር ሳይንስ፣ በማዕድን ልማት ፣ በቱሪዝምና ባህል እንዲሁም በሀገራችን በማይሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ የነጻ የትምህርት እድል መስጠት በሚያስችል መልኩ ማሻሻልና መፈራረም እንደሚገባ ለአዲሱ አምባሳደር አብራርተውላቸዋል። ሙሉ መረጃውንይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
https://www.facebook.com/share/p/1QnZHqn2kq/
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

--------------------------- // -----------------------------

(ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጋምቤላ ክልል "የትምህርት ፍትሃዊነትና ጥራት ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል።

በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርት ዘርፉ በተተገበሩ የሪፎርም ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻሎች እየታዩ መምጣታቸው አብራርተዋል።

አክለውም እንደ ሀገር ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲረጋገጥ ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ በራሱ የሚተማመን ዜጋ መገንባት ያስፈልጋል፤ ለዚህም በትምህርት ዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/16vUj3Jeh8/
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ከአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ዋና ምክትል ኃላፊ ጋር ተወያዩ፤
--------------------------- // --------------------
(ጥቅምት o7/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ምክትል ኃላፊ ሙቲንታ ሀምባይን (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ አካላት በቀጣይ የኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በዚሁ ጊዜ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የኢትዮጵያ መንግሥት ለትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለመርሃ-ግብሩ የሚመድቡት በጀት አየጨመረ መምጣቱንና ህብረተሰቡም ለመርሃ-ግብሩ ውጤታማነት የሚያደርገው ተሳትፎ በየጊዜው እያደገ የመጣ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ሙቲንታ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር በአፍሪካ ትልቁና ቀዳሚ መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ በተካሄደው አለም አቀፍ የትምህርት ቤት ምገባ ጥምረት ስብሰባ ላይ እውቅና የተሰጠውና በአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ለትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር መተግበር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በጊዚያዊነት ለመቀበል እያደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ተዘዋውረው ተመለከቱ ።
-------------------------- // -------------------------

(ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚንስትሩ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን በጋምቤላ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ለመቀበል እያደረገ ያለውን ቅድመ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያስገነባቸው ባሉ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር ከመላ ሀገሪቱ አወዳድሮ የተቀበላቸውና በጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎች በጊዜያዊነት በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለማስተማር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ ተማሪዎች የመማር ማስተማር አገልግሎት ያዘጋጃቸውን የተማሪዎች ቤተ-መጽሐፍት፣ የኮምፒውተር ክፍል፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ እና የመኝታ ክፍሎች እና ሌሎችንም አይተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሚንስትሩ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙትን ስማርት እና ኮንፈረንስ ክፍሎች እንዲሁም የኬሚስትሪና የማይክሮ ባዮሎጂ ቤተ-ሙከራዎችን የጎበኙ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ጥሩ መሻሻሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርታቸው የላቁና ብቁ ተወዳሪ እንዲሁም ወደፊት የሀገር መሪ የሚሆኑ ልጆችን ለማፍራት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያስገነባ ሲሆን በአምስቱ በቅርቡ የመማር ማስተማር ሥራ የሚጀመር ይሆናል።