Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በማስፈን ለተማሪዎች ውጤትና ሥነ-ምግባር መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ።
----------------------------- // -----------------------------
(ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም) ትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ አግባብነት ካላቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የከፈቱት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ ደንቡ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በማስፈን ለተማሪዎች ውጤትና ሥነ-ምግባር መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያውኩ ጉዳዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመምጣታቸው ይህንን ለማስተካከል ረቂቅ ደንቡ መዘጋጀቱን ጠቅሰው ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ዜጋ ማፍራት የደንቡ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/17DbLErLnk/
ለተማሪዎች ውጤታማነት እና ሥነ-ምግባር መሻሻል የትምህርት ቤቶች ወላጅ፣ ተማሪ፣ መምህር ህብረት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፤
--------------------------- // ----------------------
(ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማሻሻል ከኢትዮጵያ የተማሪ ወላጆች ማህበር እና ከየክልሉ የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች ከተመረጡ የትምህርት ቤት ወላጅ፣ ተማሪ፣ መምህር ህብረት ሰብሳቢዎች ጋር ምክክር አካሄደ።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በምክክር መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ለተማሪዎች ውጤታማነት እና ሥነ-ምግባር መሻሻል ሀገር አቀፍ፣ክልልና ከተማ አቀፍ የተማሪ ወላጆች ማህበር እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ወላጅ፣ ተማሪ፣ መምህር ህብረት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ቤት ከባቢን የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በየደረጃው ያሉ የተማሪ ወላጆች ህብረት ህብረተሰቡን የማንቀሳቀስ ቁልፍ ሚናቸውን መወጣት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አሳስበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17ftzWjxcJ/
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፉን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ያነሷቸውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦

👉🏾ትምህርት ላይ ዋናው ሥራ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው።

👉🏾በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ክ43 ሚሊየን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መጽሃፍትን በማሳተም ለተማሪዎች አንድ ለአንድ ማድረስ ተችሏል።

👉🏾ለመምህራን ጥራት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በማዘጋጀት በየደረጃው እየተሰጠ ይገኛል።

👉🏾የትምህርት ቤት መገባ ፕሮግራም ወላጆች ሳይጨነቁ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ በእጅጉ አግዟል።

👉🏾በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብረው አስደናቂ ተግባር እየፈጸሙ ነው።

👉🏾መንግስት እያካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን በማስወገድ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጻኦ አበርክቷል፣

👉🏾ልጆቻችን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረግን የምንመኛትን ኢትዮጵያ መፍጠር አንችልም በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ማስታወቂያ
የRemedial ፕሮግራም ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች
1. Website: https://student.ethernet.edu.et
2. Telegram bot: @moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎት/ አካቶ ትምህርት ማስፈጸሚያ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል።
በመሆኑም ሰነዱን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ይህንን ሊንክ ( https://forms.gle/P1QYEtgch5nsQ932A) ይጫኑ፣
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት እንዲሰጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፤
የ2016 ምሩቃን የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ከተያዘው ጥቅምት እስከ መጪው ሚያዚያ ወር እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

--------------------------- // ------------------------
(ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

በመደረኩ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የከፍተኛ ትምህርት ተማራቂዎች የመዳረሻ ጥናት የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ፕሮግራሞቻቸውን የመዳረሻ ጥናት ካላካሄዱ ምን እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ እንደሚቸገሩና በገበያው የማይፈለግ የሰው ሀብት ሊያሰለጥኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት በመስጠት በትምህርት ፕሮግራም ደረጃ ወጥ በሆነ መንገድ ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1BkZbJ5BBp/