Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፉን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ያነሷቸውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦

👉🏾ትምህርት ላይ ዋናው ሥራ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው።

👉🏾በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ክ43 ሚሊየን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መጽሃፍትን በማሳተም ለተማሪዎች አንድ ለአንድ ማድረስ ተችሏል።

👉🏾ለመምህራን ጥራት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በማዘጋጀት በየደረጃው እየተሰጠ ይገኛል።

👉🏾የትምህርት ቤት መገባ ፕሮግራም ወላጆች ሳይጨነቁ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ በእጅጉ አግዟል።

👉🏾በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብረው አስደናቂ ተግባር እየፈጸሙ ነው።

👉🏾መንግስት እያካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን በማስወገድ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጻኦ አበርክቷል፣

👉🏾ልጆቻችን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረግን የምንመኛትን ኢትዮጵያ መፍጠር አንችልም በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ማስታወቂያ
የRemedial ፕሮግራም ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች
1. Website: https://student.ethernet.edu.et
2. Telegram bot: @moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎት/ አካቶ ትምህርት ማስፈጸሚያ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል።
በመሆኑም ሰነዱን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ይህንን ሊንክ ( https://forms.gle/P1QYEtgch5nsQ932A) ይጫኑ፣
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት እንዲሰጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፤
የ2016 ምሩቃን የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ከተያዘው ጥቅምት እስከ መጪው ሚያዚያ ወር እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

--------------------------- // ------------------------
(ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

በመደረኩ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የከፍተኛ ትምህርት ተማራቂዎች የመዳረሻ ጥናት የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ፕሮግራሞቻቸውን የመዳረሻ ጥናት ካላካሄዱ ምን እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ እንደሚቸገሩና በገበያው የማይፈለግ የሰው ሀብት ሊያሰለጥኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት በመስጠት በትምህርት ፕሮግራም ደረጃ ወጥ በሆነ መንገድ ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1BkZbJ5BBp/
በመምህራን የትምህርት ዝግጅትና ልማት ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

------------------------- // ------------------------

(ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም) “Educators shaping futures" በሚል መሪ ቃል በመምህራን የትምህርት ዝግጅትና ልማት ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከአለም ባንክና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ ባዘጋጀው በዚህ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የበርካታ ሀገራት የትምህርት ባለሙያዎችና ስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ለትምህርት ጥራት መሳካት መምህራን ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ መምህራንን ማብቃትና መደገፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና መሆኑን አመላክተው በዚህም የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1Bp5nJvbFi/
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥርዓተ ትምህርት ውጤት ተኮር እንዲሆን ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ተገለጸ፤

‌‎የሚከለሰው ስርዓተ ትምህርትም በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

------------------------ // ------------------------

‌(ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም) የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተልዕኮ መሰረት ባደረገ መልኩ ስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የዩኒቨርስቲዎቹን ስርዓተ ትምህርት ውጤት ተኮር አድርጎ መከለስ ያስፈለገው የቀድሞዎቹ ስርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ያልዋጁና ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር በአግባቡ ያልተቃኙ በመሆናቸው ነው።
‎አዲሱ የውጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት ተመራቂዎች በትምህርት ፕሮግራሞቹ መጨረሻ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት በአግባቡ የፈተሸ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡


‌‎የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ነገዎ በበኩላቸው ውጤት ተኮር የሆነው ስርዓተ ትምህርት ሙያና ተግባር ተኮር መሆኑን ጠቅሰው ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ምሩቃንን ማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።‎ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1GoVkDSoBU/