Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ስራዎች ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ሀገርን ለማሻገር ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገለጸ።

አስረኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይና ውድድር በይፋ ተከፍቷል።

-------------------------- // ------------------------

የትምህርት ሚኒስቴር ከሌሎች ተባባሪ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያዘጋጀው አመታዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይና ውድድር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ልዩ ዝንባሌና ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎችና መምህራን የሚያገናኘውን አመታዊ አውደ ርዕይና ውድድር የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በይፋ ከፍተውታል።

ሚንስትር ዴኤታዋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ሀገርን ለማሻገር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና የሌሎች ተባባሪ ተቋማት ስራ ሀላፊዎች ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።
34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀመረ፤

----------------------- // -------------------------

‎(ሕዳር 2/2017 ትምህርት ሚኒስቴር) ''ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም'' በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ጉባዔ የ2017 የትምህርት ልማት ዘርፍ አፈጻጸም ይገመገማል።
‎
‎ጉባዌው በ2018 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም የሚያግዙ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
‎
‎በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ ጉባዔ የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
‎
‎በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፣የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶችና አጋሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
‎
የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጠንካራ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትና ለየሞራል ግንባታ መሰረት የሆነ ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረ አድርጎ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ፤

‎34ኛው የትምህርት ጉባዔ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
----------------------- // ----------------------
‎(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጉባኤውን ሲከፍቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጠንካራ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትና ለየሞራል ግንባታ መሰረት የሆነ ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረ አድርጎ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
‎
‎የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር ጥራትና ፍትሃዊነትን የተረጋገጥ ትምህርት ከማቅረብ ባሻገር በጠንካራ ሞራል መሠረት ላይ የቆመ ዜጋ መፍጠር እንደሚገባም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጨምረው አስገንዝበዋል።
‎
‎የተማሩ ብቃትና ችሎታ ያላቸውን ዜጎች ለማፍራት ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥልቀት ያለው እውቀት መስጠት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1DW3caqN3o/
ትውልድን የመገንባት መንገዳችን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ስለሆነ ዘርፉን የሚያሻግሩ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አሳሰቡ፤

------------------------- // ------------------------

(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር) ትውልድን የመገንባት መንገዳችን ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ስለሆነ ዘርፉን የሚያሻግሩ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ አሳስበዋል።

በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ተግባራት ተነድፈው እየተተገበሩ መሆኑት የገለጹት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ባለፈው የትምህርት ዘመን ጸድቆ ወደትግብራ የገባውን የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ በሚገባ መተግበር ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም ለተማሪዎች ውጤታማነት የትምህርት ቤት ምገባ፣ የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን አንስተው በዚህ ዓመትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሰገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፣ https://www.facebook.com/share/p/1XT2JWBUGF/
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለታቀዱ የሪፎርም ተግባራት መሳካት ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ፤

------------------------ // -----------------------

‎(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በ34ኛው የትምህርት ጉባኤ ላይ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለታቀዱ የሪፎርም ተግባራት መሳካት ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

‎በዚህም የኢንዱስትሪዎችና የትምህርት ተቋማት ትብብር መሥራት ሁለቱንም አካላት የሚጠቅም ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።
‎
‎አያይዘውም የዩኒቨርስቲዎች በመማር ማስተማር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ገልጸው ከየዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ምገባ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ወስዶ የሚከታተል ተቋም ለማቋቋም እቅድ መኖሩንም ተናግረዋል።
‎
‎ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የዩኒቨርስቲዎች የትኩረት መስክ ልየታ በሂደት እየተሳካ የሚሄድ መሆኑን ገልጸው በዚህ ሂደት የሚፈጠሩ የመምህራንን እጥረትና ከምችት ለማሰተካከል አዘዋውሮ የማሰራት አቅጣጫ መኖሩንም ጠቁመዋል።
‎
‎የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በትኩረት ለመደገፍ የተለየ የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጨምረው አብራርተዋል።
የት/ቤት ምገባን በማጠናከር የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ማሳደግ ይገባል፤ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይዎት

--------------------- // ------------------
(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) በ34ኛው የትምህርት ጉባኤ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይዎት የት/ቤት ምገባን በማጠናከር የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

ፕ/ር ክንደያ አክለውም የትምህርት ማህበረሰቡ በ “ትምህርት ለትውልድ“ያሳየውን የላቀ ተሳትፎ በአዳሪ እና በሞዴል ት/ቤቶች ግንባታም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የሪፎርም ስራዎቻችንና አበይት ስራዎቻችንን በሚገባ ለይተን በዚህ የትምህርት ዘመን ውጤት ሊያመጡ በሚችል መልኩ መተግባር እንደሚገባም ተናገረዋል።
የትምህርት ስርዓቱን ከዓለም የአየር ንብረት ፣ የቴክኖሎጂ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቃኘት እንደሚገባ ተመላከተ።
‎
‎34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
--------------------------- // -----------------------
‎
‎(ሕዳር 02/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የትምህርቱን ሥራ ከአየር ንብረት ፣ ቴክኖሎጂና ከዓለም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቃኘትና መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎
‎ይህ ጊዜ ለውጦችን በመቋቋም ወደ እድል የሚቀይሩ ፣ አገራቸውን የሚወዱና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ዜጎችን ለማፍራት በትጋት የምንሰራበት ወቅት መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።
‎
በመሆኑም‎ በየደረጃው ያሉ መምምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት አይነት የበቁ ሆነው በመገኘት ሙያቸውን ሊያሳድጉና ሊያስከብሩ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
‎
በተጨማሪም ‎የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተቋቋሙበት አላማ ቅድሚያ በመስጠት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
‎
‎የአካል ጉዳተኞችን የመማር ማስተማር ከባቢ ምቹ ለማድረግ አገሪቱ ባላት አቅም ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክተዋል።
‎
‎በበኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፍትሃዊና “ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪቃል የተካሄደው 34ኛው የትምህርት ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣትም ተጠናቋል።