Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
አመታዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይና ውድድር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፤
------------------------------- // ------------------------------

(ህዳር 04/ 2018 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር እና ተባባሪ አካላት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው 10ኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይና ውድድር ተጠናቋል።

በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ መርሃ-ግብሩ ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ሀሳባቸውን ለሌሎች አካፍለው ድጋፍና ግብዓት በማሰባሰብ ወደ ውጤታማ ምርትና አገልግሎት ለመቀየር የሚጥሩበት አውድ በመሆኑ በሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሀገራት መካከል ለተፈጠረው የዕድገት ልዩነት መሰረታዊውና ዋነኛው ምክንያት ለቴክኖሎጂና ፈጠራ ስራዎች የተሰጠው ትኩረትና በዚህ ረገድ የተሰሩ ሥራዎች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴታው አክለውም በአካባቢያቸው ያሉ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ሥራ ዝንባሌና ተሰጣኦ ያላቸው ተማሪዎችን የመደገፍና የማብቃት ሥራ ለዩኒቨርሲቲዎች ከተሰጡት ቁልፍ ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/16VyKcrspR/
የክብር ዶክትሬት የተሠጣቸውን ግለሰቦች በመጠሪያነት መጠቀም የማይቻል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ።

--------------------------- // ----------------------------

(ሕዳር 05/2017 ዓ.ም) በዛሬው እለት የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቷል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በተመለከተ ችግር የነበረበት በመሆኑ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/17ogQjrnLd/
በትምህርት ቤቶች የጓሮ እርሻ ሥራን ከመደበኛ ትምህርት ጋር በማቀናጀት ተማሪዎች ጽንሰ ሀሳቦችን እንዲተገብሩና የህይወት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ
‎
‎(ሕዳር 08/2018 ዓ.ም) ለተመረጡ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና የግብርና ባለሙያዎች በትምህርት ቤቶች የጓሮ እርሻ ልማት ላይ ያተኮረ ስልጠናና ትምህርታዊ ጉብኝት ተደርጓል።
‎
‎የትምህርት ፕሮግራሞቾና ጥራት መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሐንስ ወጋሶ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በትምህርት ቤቶች የጓሮ እርሻ ሥራን በማስፋፋት ተማሪዎች የህይወት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እየተሰራ ነው።
‎
‎ በትምህርት ቤቶች የጓሮ እርሻዎች መስፋፋት አመጋገብና ሥነ ምግብን በማሻሻል፣ የምገባ ወጪን በመቀነስ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሥራ እድል ፈጠራና በሌሎችም ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ዶ/ር ዩሐንስ ተናግረዋል።
‎
‎ትምህርት ቤቶች የመማማሪያና የማህበረሰብ ሽግግር የሚደረግባቸው ማዕከላት በመሆናቸው ምርታማነታቸው በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
‎
‎
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ በ2 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ ደንብ ሊንክ = https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6
2. የተማሪዎች የሥነ-ምግባር መመሪያ (የመጀመሪያ ረቂቅ) ሊንክ =
https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6

በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂቅ መመሪያ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅና የመምህራንን ብቃት በማሳደግ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገልጸ።

።።።።።።።።።።።።።።።።

(ሕዳር 9/2018 ትምህርት ሚኒስቴር) የመምህራንን ብቃት ለማሳደግ የሚረዳ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የአሠልጣኞች ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል።

በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የመምህራንና ት/ቤት አመራሮች ልማት ዴስክ ሀላፊ ወ/ሮ አሰገድ መሬሳ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ እየወሰዳቸው ካሉ እርምጃዎች አንዱ የመምህራንን ብቃት ማሳደግ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የመምህራንንና ትምህርት አስተዳደር ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ዋነኛ የትኩረት መስክ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አሁን ላይ የሚሠጡ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ስልጠና ቀደም ሲል ከነበረው ተለምዶዓዊ የአሠለጣጠን ስርዓት በማላቀቅ የትምህርት አመራሩና መምህሩ ሁለንተናዊ ስብእና የተላበሠ፤ በእውቀትና ክህሎት የተገነባ እንዲሆን የሚያስችሉ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም መምህራን ከማስተማር ሥራ ጎን ለጎን አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት የሥራ ላይ ተግባራዊ ስልጠና ተዘጋጅቶ በመላ ሀገሪቱ ይሰጣል ብለዋል።

በተያዘው አመት መጨረሻ ድረስ የሚሠጠው ይህ ስልጠና 70% መምህራኑና የትምህርት አመራሩ በስራ ገበታቸው ላይ ሆነው የስራ ላይ የተግባር ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን 20% ከሌሎች ልምድና ተሞክሮ የሚቀስሙበት እንዲሁም ቀሪው 10% የገጽ ለገጽ ስልጠና እንደሚወስዱ ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን በሚያካሂዱት የጓሮ እርሻ ሥራ የተማሪዎችን ምገባ በማገዝ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ።
‎
(ሕዳር 9/2018 ትምህርት ሚኒስቴር) ከተለያዩ ክልሎች የተወጣቱ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች በአዳማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ከመማር ማስተማሩ ሥራ ጎነ ለጎን በጓሮ እርሻ ልማት ትምህርት ቤቱ እየሰራቸው ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረ በመመልከት ልምድ ቀሰመዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሁሴን በሪሶ የትምህርት ቤቱን የጓሮ እርሻ ሥራ ባስጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት ትምህርት ቤቱ ከመማር ማስተማር ሥራው ጎነ ለጎን በጓሮ እርሻ ስራ ራሱንና የአካባቢውን ማህበረሰብ መጥቀም መቻሉን ተናግረዋል።
‎
‎ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባሉት ክፍት ቦታዎች በመጠቀም በወተት እና እንቁላል ምርት ፣ በንብ ማነብና እንደ ፓፓዬ ፣ብርቱካንና ማንጎ ያሉ ፍራፍሬዎችን በማልማትና ኮምፖስት ማዳበሪያ በማዘጋጀት ውጤት ማግኘቱን አቶ ሁሴን ገልጸዋል። ሙሉ ዜናውን https://web.facebook.com/share/p/14TNARMUovG/

‎ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ