ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
የትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ በ2 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ ደንብ ሊንክ = https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6
2. የተማሪዎች የሥነ-ምግባር መመሪያ (የመጀመሪያ ረቂቅ) ሊንክ =
https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6
በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂቅ መመሪያ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር

Google Docs
በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችንለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ (2018) ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) ይጫኑ እና ያለዎትን አስተያየት…
የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅና የመምህራንን ብቃት በማሳደግ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገልጸ።
።።።።።።።።።።።።።።።።
(ሕዳር 9/2018 ትምህርት ሚኒስቴር) የመምህራንን ብቃት ለማሳደግ የሚረዳ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የአሠልጣኞች ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል።
በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የመምህራንና ት/ቤት አመራሮች ልማት ዴስክ ሀላፊ ወ/ሮ አሰገድ መሬሳ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ እየወሰዳቸው ካሉ እርምጃዎች አንዱ የመምህራንን ብቃት ማሳደግ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የመምህራንንና ትምህርት አስተዳደር ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ዋነኛ የትኩረት መስክ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አሁን ላይ የሚሠጡ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ስልጠና ቀደም ሲል ከነበረው ተለምዶዓዊ የአሠለጣጠን ስርዓት በማላቀቅ የትምህርት አመራሩና መምህሩ ሁለንተናዊ ስብእና የተላበሠ፤ በእውቀትና ክህሎት የተገነባ እንዲሆን የሚያስችሉ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም መምህራን ከማስተማር ሥራ ጎን ለጎን አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት የሥራ ላይ ተግባራዊ ስልጠና ተዘጋጅቶ በመላ ሀገሪቱ ይሰጣል ብለዋል።
በተያዘው አመት መጨረሻ ድረስ የሚሠጠው ይህ ስልጠና 70% መምህራኑና የትምህርት አመራሩ በስራ ገበታቸው ላይ ሆነው የስራ ላይ የተግባር ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን 20% ከሌሎች ልምድና ተሞክሮ የሚቀስሙበት እንዲሁም ቀሪው 10% የገጽ ለገጽ ስልጠና እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን በሚያካሂዱት የጓሮ እርሻ ሥራ የተማሪዎችን ምገባ በማገዝ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ።
(ሕዳር 9/2018 ትምህርት ሚኒስቴር) ከተለያዩ ክልሎች የተወጣቱ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች በአዳማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ከመማር ማስተማሩ ሥራ ጎነ ለጎን በጓሮ እርሻ ልማት ትምህርት ቤቱ እየሰራቸው ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረ በመመልከት ልምድ ቀሰመዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሁሴን በሪሶ የትምህርት ቤቱን የጓሮ እርሻ ሥራ ባስጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት ትምህርት ቤቱ ከመማር ማስተማር ሥራው ጎነ ለጎን በጓሮ እርሻ ስራ ራሱንና የአካባቢውን ማህበረሰብ መጥቀም መቻሉን ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባሉት ክፍት ቦታዎች በመጠቀም በወተት እና እንቁላል ምርት ፣ በንብ ማነብና እንደ ፓፓዬ ፣ብርቱካንና ማንጎ ያሉ ፍራፍሬዎችን በማልማትና ኮምፖስት ማዳበሪያ በማዘጋጀት ውጤት ማግኘቱን አቶ ሁሴን ገልጸዋል። ሙሉ ዜናውን https://web.facebook.com/share/p/14TNARMUovG/
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
ህዳር 10/2018 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ) በበይነ መረብ የተደገፈ የአውቶሜሽን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ወደ ተግባር ለማስገባት የሚያስችል ስልጠና ለባለሙያዎች ተሰጥቷል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ አሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡
በቴክኖሎጂ የዘመነ አሰራር ጊዜን፣ ጉልበትን፣ ገንዘብንና ሌሎች ወጪዎችን በመቀነስ አገልግሎቶችን ጥራት ባለው ሁኔታ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ በተመሳሳይ ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ እድል የሚፈጥር በመሆኑ እነዚህን አገልግሎትዮች ዲጅታላይዝ ማድረግ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ዶ/ር ኤባ ተናግረዋል፡፡ ሙሉ ዜናውን https://web.facebook.com/share/p/17eVUr1GXr/

የትምህርት ሚኒስትሩ የናይጄሪያ ቴክኒካል ድጋፍ በጎፈቃደኞች ድርጅት ልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
(ህዳር 12/2018 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከናይጄሪያ ቴክኒክ ድጋፍ በጎፈቃደኞች ድርጅት ልዑክ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።
የሁለቱ አካላት ውይይት ናይጄሪያ ከዚህ ቀደም ለሀገራችን ስትሰጥ የነበረውና ተቋርጦ የቆየውን የበጎ ፈቃደኞች የቴክኒክ ድጋፍ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ።
በዚሁ ጊዜ ናይጄሪያ ከኢትዮጵያጋር የቆየ ወዳጅነት ያላት ሀገር መሆኗን ያነሱት የልዑካን ቡድኑ መሪ ሀገራቸው ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ የበጎ ፈቃደኞች ቴክኒክ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን አንስተዋል።
ነገር ግን ይህ የበጎ ፈቃደኞች የቴክኒክ ድጋፍ በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱንና አሁን ላይ የናይጄሪያ መንግስት ይህንን በትምህርቱ ዘርፉ የሚያደርገውን የበጎ ፈቃደኞች ቴክኒክ ድጋፍ ማስቀጠል ፍላጎት ያለው በመሆኑ በጎ ፍቃደኞችን ለማሰማራት የሚቻልበትን ሁኔታ ለክቡር ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል። ሙሉ ዜናውን ፦https://web.facebook.com/share/p/1CeAmPncmG/

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እሴት የሚፈጥሩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራዎችን ማፍለቅ እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ
የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ የማበልጸጊያ ማዕከላት ጥምረት/Ethiopian University Incubation Center Alliance EUICA/ ይፋ ሆኗል ።
---------------------------------- // --------------------------------
(ህዳር 13/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲዎች ምሩቃንን ከማፍራት ባለፈ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እሴቶችን መፍጠር፣ ችግር መፍታትና አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችን ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ።
የዩኒቨርስቲ ማበልጸጊያ ማዕከላት /Incubation centers/ ከተለምዷዊ ኢኮኖሚ በዕውቀት ላይ ወደ ተመሰረተ ኢኮኖሚ ሽግግር የሚደረግባቸው ማዕከላት በመሆናቸው የአገሪቱ ኢኮኖሚ አምራች ሞተር መሆን እንዳለባቸው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርስቲ ማበልጸጊያ ማዕከላት ከግል ማበልጸጊያዎች ኢንዱስትሪዎችና ክልላዊ ገበያዎች ጋር ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ለአገር የኢኮኖሚ እድገት ንቁ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸውም ክቡር አቶ ኮራ ተናግረዋል።
የማበልጸጊያ ማዕከላት በግብርና ፣በማኑፋክቸሪንግ፣ በጤና ፣በዲጂታል መፍትሄዎች ፣በቱሪዝም ፣በአየር ንብረትና በሌሎችም የፈጠራ ስራዎች አበርክቷቸውን በማሳደግ ለአገር የኢኮኖሚ እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1DQCAFz4YY/