ማስታወቂያ
ለልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ መምህራን በሙሉ፡
በትምህርት ሚኒስቴር ለፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ መምህራን ስም ዝርዝር እና የተመደባችሁበትን ተቋም እያሳወቅን ፤ በየተመደባችሁበት የፌደራል ልዩ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች እስከ ህዳር 22/2018ዓ.ም ድረስ ሪፖርት አንድታደርጉ እያሳሰብን በተጨማሪም ከዚህ በታች በተቀመጠው መረጃ መሰረት የልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮችን በማግኘት ተጨማሪ መረጃ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
1. ጋምቤላ - በስልክ ቁጥር 0911590938
2. አምቦ - በስልክ ቁጥር 0920189695/0989123320
3. ጅግጅጋ - በስልክ ቁጥር 0922648636
4. ወልቂጤ - ስልክ ቁጥር 0943165470
5. ቦንጋ - በስልክ ቁጥር 0913192165

በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተመርቃችሁ ለመምህርነት ሙያ ማመልከት ለምትፈልጉ
ቀደም ሲል በወጣው መመልመያ መስፈርት መሰረት ለመመዝገብ የምትፈልጉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶችና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት ላይ በዚህ ሊንክ https://shorturl.at/ORED9 በመግባት “የትምህርት ዓይነትና ተዛማች የትምህርት መስኮች” የሚለውን download በማድረግ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ገልጸን፤ የ5 ዩኒቨርስቲዎችን የመመዝገቢያ ሊንኮች ማሳወቃችን ይታወሳል፤
ከተገለጹት 5 ዩኒቨርስቲዎች በተጨማሪ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መመዝገብ የሚቻል ሲሆን ለመመዝገብ የምትፈልጉ አመልካቾች በዚህ ሊንክ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdRwj89yQ50AiUeZZeDe8tr8aJ5GQZO4B0IqUVJzJJCNJzWPQ/viewform በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ከደቡብ አፍሪካ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይትም University of South Africa (UNISA) በኢትዮጵያ እንዴት በትብብር መስራት እንደሚችል ተወያይተዋል።
----------------------------- // ---------------------------
(ሕዳር 20/2018 ዓ.ም) በዚሁ ጊዜ የልዑካን ቡድኑን የመሩት የUnisa’s Principal and Vice-Chancellor Prof Puleng LenkaBula፤ UNISA ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ከ2006 ጀምሮ በትምህርት፣ በምርምር እና በቴክኖሎጂ መስክ በርካታ ተማሪዎችንና የመንግስት ሰራተኞችን ሲያስመርቅ መቆየቱን ለክቡር ሚኒስትሩ አብራርተውላቸዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የነበረው የትምህርት ሥርዓት ከፍተኛ ችግር የነበረበትና በከፍተኛ ትምህርት ዜጎች ዲግሪ በገንዘብ የሚገዙበት ጭምር የነበረ በመሆኑ፤
ይህንን ለማስተካከል በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ የትምህርት ጥራትን ሊያረጋግጡ እንዲሁም ብቃት ያላቸው፣ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎች እየተተገበሩ መሆኑና በዚህም ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1AKNFmGFjA/

ትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች 22ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን አክብረዋል።
--------------------------- // -----------------------
(ህዳር 25/2018 ዓ.ም) 22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
በዕለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ እንደ ሀገር ከገጠመን የሥነ ምግባርና የሞራል ክስረት ለመላቀቅ ትውልዱ ሁለንተናዊ ብቃትና ስብዕና የተላበሰ ሆኖ እንዲቀረጽ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተንሰራፋ የመጣውን ዘርፈ ብዙ የሙስና ተግባር ለመከላከል ብሎም ለመግታት የመንግሥት አግልግሎት ለሁሉም ዜጎች በእኩልነት እንዲሰጥ ቴክኖሎጂን መጠቀምና የአሠራርን ግልጽነትን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የሙስና ተግባራትን ፈጽምው በሚገኙ ዜጎች ላይ ወቅቶች ተጠብቀው ለፖለቲካ ፍጆታነት ከሚወሰዱ እርምጃዎች ባሻገር ዘላቂነት ባለው መልኩ አራሚ እና አስተማሪ እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባም አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17PLCG5mKK/

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ።
--------------------------- // -------------------------
(ህዳር 26/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች 20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝብቦች ቀን በዓልን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል አክበረዋል።
"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚለው በዘንድሮ 20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መሪ-ቃል መነሻነት የውይይት መነሻ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ብዝሀነትና ሀገራዊ አንድነትን አጉልተው የሚያሳዩ ሀሳቦች በሰፊው ተዳሰዋል፡፡
በበዓሉ አከባበር የብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበር ህገ መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ እሴቶች ተጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ የሚያስችል መሆኑንና የዜጎች ሀገራዊ አመለካከትና ብሔራዊ መግባባትን እንዲጎለብት በማስቻል ረገድም ከፍ ያለ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል፡፡
ዴሞክራሲና ፌዴራላዊ ስርዓት በማጠናከር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን መገንባት ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ለማስተሳሰር የጋራ መረዳት የሚፈጥር እንደሆነም በመድረኩ ተመላክቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ከቻይና የመጡ የልዑካን ቡድን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
-------------------------- // ----------------------------
(ህዳር 26/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቻይና የመጡ የልዑካን ቡድን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ጊዜ የልዑካን ቡድኑን የመሩት የቻይና የቋንቋ ትምህርትና ትብብር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር Yu Yunfeng ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር የቆየ ወዳጅነት ያላት ሀገር መሆኗን አንስተዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ የቻይና ስትራቴጂክ አጋር ናት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በኢንቨስትመንት ረገድ ከምታደርገው ትብብር በተጨማሪ የቻይና ቋንቋ ትምህርት በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን በሌሎች የትምህርት ተቋማት በማስፋፋት የቻይና ቋንቋን ማስተማር እንደሚፈልጉ ገልጸውላቸዋል።
ይህም ዜጎች በርካታ ቋንቋዎችን እንዲያውቁ ከማድረጉም ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ትብብርን የበለጠ በማጠናከር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17ibX2ynrJ/