Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የምስራቅና የመካከለኛ ሀገራት የፖን አፍሪካ የተማሪዎች እግር ኳስ ውድድር በዩጋንዳ ካምፖላ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
በኡጋንዳ አስተናጋጅነት የአፍሪካ የትምህርት ቤቶች እግር ኳስ ውድድር ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ ባካሄደችው ጨዋታ ከምድቧ ፍፁም የበላይነቷን አረጋግጣ በሁለቱም ጾታዎች ለዋንጫ አልፋለች ።

በውድድሩ በአጠቃላይ ከምድቧ 1ኛ ሆና ያለፈችው ኢትዮጵያ ዛሬ ማክሰኞ በሁለቱም ፆታዎች ለዋንጫ የምትጫወት ይሆናል።
ሀገራችን የወከሉ ታዳጊ ተማሪዎችም መልካም እድል እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
ብዝሃነትና አካታችነትን በማረጋገጥ የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ
‎በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ Diversity & Inclusion በሚል ርዕስ ትምህርታዊ ውይይት ተካሂዷል።

--------------------------- // --------------------------

‎(ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ብዝሃነትና አካታችነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
‎
‎ብዝሃነትና አካታችነትን በማረጋገጥ በዘርፉ ያሉ እድሎችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ቢሆንም ከሚጠበቀው አንጻር ብዙ መስራት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
‎
‎አካታችነትና ብዝሃነት የአመለካከት ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ኮራ ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥና ለማስፋት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎
‎በከፍተኛ ትምህርት በውጤት ተኮር የትምህርት አሰጣጥና በብዝሓነትና አካታችነት ላይ ያተኮረውን ትምህርታዊ ገለጻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ተክለ ማርያም ሰጥተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1GWUzAa4XS/
በግሪክ ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤት ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
---------------------------- // ------------------------

(ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም) በግሪክ ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤት ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የግሪክ ኤምባሲ ተፈርሟል።

የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ፈርመውታል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ በግሪክ ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት አመታት ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን አስታውሰው ይህ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ችግሩን ሙሉ በሙሉ በመፍታት ለዜጎች ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

አክለውም ኢትዮጵያና ግሪክ ለረጅም ጊዜ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተው ከት/ቤቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን የቆየ ችግር ለመፍታትና የትምህርት ቤቱን ሌጋሲ ለማስቀጠል በትምህርት ሚኒስቴር፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም እንደ መንግስት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/16xe4Hw91B/
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎችና ደንብ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤

የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ3 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ ሊንክ: - https://forms.gle/RXsuSUGtFFYrkAMQ9
2. የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ሊንክ: - https://forms.gle/TZTSPZrJzgEnY2Rq9
3. የተፋጠነ ትምህርት መርሃ-ግብር አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ ሊንክ: - https://forms.gle/16CDaGfzkXDF6fwt6 አዘጋጅቷል።
በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ/ ደንብ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
የፌዴራል አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወችን ለመቀበል ዩኒቨርስቲዎች እያደረጉ ያለው ቅድመ ዝግጅት በፎቶ