Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎችና ደንብ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤

የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ3 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ ሊንክ: - https://forms.gle/RXsuSUGtFFYrkAMQ9
2. የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ሊንክ: - https://forms.gle/TZTSPZrJzgEnY2Rq9
3. የተፋጠነ ትምህርት መርሃ-ግብር አፈፃጸም ረቂቅ መመሪያ ሊንክ: - https://forms.gle/16CDaGfzkXDF6fwt6 አዘጋጅቷል።
በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ/ ደንብ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
የፌዴራል አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወችን ለመቀበል ዩኒቨርስቲዎች እያደረጉ ያለው ቅድመ ዝግጅት በፎቶ
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ-ገዝ አድርጎ መልሶ በማቋቋም ሂደት ውስጥ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

------------------------- // ---------------------

(ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም) ምክክሩ በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተመላክቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት በትምህርት ዘርፉ በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው አብራርተዋል።

የተቋማት ስኬትም ይሁን ውድቀት በዩኒቨርሲቲው አመራርና ማህበረሰብ ላይ የሚወድቅ መሆኑን በመገንዘብ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በቁርጠኝነት በማስፈጸም ዩኒቨርሲቲዎች ብቃት ያለው ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ማፍራት የሚያስችሉ ተቋማት እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም አክለው ገልጸዋል።

በዚህም ረገድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረውን የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የማድረግ ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶችን በሚገባ በመለየት በመጪው አመት ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገጥማቸውን ጫና በመቋቋም ለእውነትና እውቀት የቆሙና የማይገፋ ጠንካራ ተቋም ሆነው ለመውጣት አስፈላጊውን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Bod1xW7x1/
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገላቸው አቀባበል