የፌዴራል አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወችን ለመቀበል ዩኒቨርስቲዎች እያደረጉ ያለው ቅድመ ዝግጅት በፎቶ
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ-ገዝ አድርጎ መልሶ በማቋቋም ሂደት ውስጥ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
------------------------- // ---------------------
(ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም) ምክክሩ በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተመላክቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት በትምህርት ዘርፉ በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው አብራርተዋል።
የተቋማት ስኬትም ይሁን ውድቀት በዩኒቨርሲቲው አመራርና ማህበረሰብ ላይ የሚወድቅ መሆኑን በመገንዘብ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በቁርጠኝነት በማስፈጸም ዩኒቨርሲቲዎች ብቃት ያለው ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ማፍራት የሚያስችሉ ተቋማት እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም አክለው ገልጸዋል።
በዚህም ረገድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረውን የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የማድረግ ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶችን በሚገባ በመለየት በመጪው አመት ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገጥማቸውን ጫና በመቋቋም ለእውነትና እውቀት የቆሙና የማይገፋ ጠንካራ ተቋም ሆነው ለመውጣት አስፈላጊውን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Bod1xW7x1/

በኢትዮጵያና ህንድ መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ አስታወቁ።
የሦስተኛ ዲግሪ ነጻ የትምህርት እድል ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል።
------------------------- // --------------------------
(ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ መርሃ ግብሩን ሲከፍቱ እንደገለጹት በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ወዳጅነትና ትብብር እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ነው።
ይፋ የሆነው የድህረ ምረቃ ትምህርትና ምርምር መርሃ ግብርም የድህረ ምረቃ ትምህርት አቅም በመገንባት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ትልቅ ሽግግር ለማድረግ እንደሚያግዝ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
ከህንድ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጠው የትምህርት እድል፣ የምርምር፣ ቴክኖሎጅና ፈጠራን በማሳደግ ብቁ የሰው ሀይል በጥራት ማቅረብ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው የመርሃ ግብሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኢንጂነሪንግና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን የሦስተኛ ዲግሪ እጥረት እንደሚያቃልል ተናግረዋል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/16THBQaqkd/