ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የወደፊቱ አገር ተረካቢዎች ሁለንተናዊ ሰብዕና የሚገነባባቸው ተቋማት መሆናቸው ተመላከተ፤
የቦንጋ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
------------------------ // ----------------------
(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) በአዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ እንደገለጹት አዳሪ ትምህርት ቤቶች የነገዎቹ አገር ተረካቢዎች ሁለንተናዊ ስብዕና የሚገነባባቸው ቦታዎች ናቸው።
ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጥራት ያለው ትምህርት ከማቅረብ ጎን ለጎን በጥሩ ባህሪ የተገነቡ ፣ሥነምግባር የተላበሱና በሙያቸው የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ዜጎች የሚፈሩባቸው ማዕከላት መሆናቸውንም ክቡር አቶ ኮራ አስገንዝበዋል።
የትምህርት ቤቶች ትኩረት በአብዛኛው የአካዳሚክ ዕውቀትን በማስተላለፍ ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከንድፈ ሀሳብ እውቀት ባሻገር የተማሩትን ወደ ተግባር በመለወጥ የማህበረሰቡን ችግር መፍታት የሚችሉ ዜጎችን ማፍራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግነት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BgVEuwXNA/

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቡኢ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
----------------------------- // -------------------------
(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) መርሃ ግብሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል(ዶ/ር) እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ አስጀምረውታል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ስርዓቱ የገጠመንን የሞራል ስብራት ለማስተካከል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።
እንደ ሀገር በፍጥነት ማደግ ከፈለግን በትምህርት ላይ ትኩረት አድርገን መሥራት አለብን፤ በዚህም ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት በሀሉም አካባቢ ለመሥጠት በኢትዮጵያ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በርካታ ሀብት በማሰባሰብ የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገናና የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1GDF3gQYaW/

ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
በአጠቃላይ ትምህርት የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ እና ዕድሳት አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) ይጫኑ እና ያለዎትን አስተያየት ቀጥሎ ባለው ቅፅ ይሙሉ፤
https://forms.gle/o7kGXCRMxtLLc6NSA
ይህንን ረቂቅ መመሪያ በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
ለመጀመር የተጠቀሰውን ሊንክ መጫን፤
በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር

Google Docs
በአጠቃላይ ትምህርት የመምህራንናየትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ እናዕድሳት አፈጻጸም መመሪያ ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) ይጫኑ እና ያለዎትን አስተያየት ቀጥሎ ባለው ቅፅ…
የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት በማሻሻል ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ከባቢ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
-------------------------- // ----------------------------
(ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም) የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት በማሻሻል ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ከባቢ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤ የአርብቶ አደርና ልዩ ፍላጎት ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ መሰረት በቀለ እስካሁን ድረስ በት/ቤቶቻችን ምቹ አለመሆን እና በተዛማጅ ተግዳሮቶች በርካታ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት ሳይመጡ እንደቆዩ ገልጸዋል።
መንግስት ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው የተለየ ትኩረት የድጋፍ መስጫ ማዕከላትን በማቋቋሙ እና የት/ቤቶችን ከባቢ ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ እያደረገ በመምጣቱ እስከሁን ድረስ ት/ቤት መጥተው የማያውቁ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ትምህርት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር እስከ አሁን ከ1400 በላይ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት መቋቋማቸውን የጠቆሙት ሃላፊዋ በዚህ ዓመትም ተጨማሪ 172 የድጋፍ መስጫ ማዕከላት እንደሚቋቋሙ ገልጸው እነዚህ ማዕከላት ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ሽፋን እንደሚጨምሩ ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።
የድጋፍ መስጫ ማዕከላቱን ለማቋቋምና የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ቁሳቁሶች ለማሟላት በቂ ሀብት በአጋር ድርጅቶች መመደቡን ገልጸው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ስኬታማነቱ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው በመስራት ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ኢንጂነሪንግ፣አርትና ሂሳብ (STEAM) ማዕከል ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር አስተዋጽኦው የጎላ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፣
------------------------- // --------------------------
(ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም) የSTEAM ማዕከላት ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር አስተዋጽኦው የጎላ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የሂሳብ፣ሳይንስና ሥነ-ጥበብ ማበልጸጊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተሬሳ ገልጸዋል።
በዚህም የሀገር አቀፍ የSTEAM ስልጠና ማቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው ሰነዱ ወተግባራዊ መሆን ሲጀምር ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
የሳይንስ፣አርትና ሂሳብ ትምህርቶች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተግባር ተደግፈው ለተማሪዎች እንዲሰጡ የመምህራን ኮሌጆችን ጨምሮ በየደረጃው ባሉ የአጠቃላይ ትምህርት እርከን ላይ የሚያስተምሩ መምህራንን በSTEAM የሥልጠና ማዕቀፍ መሰረት ማብቃት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አቶ ታደሰ አክለውም በቀጣይ ለማዕቀፉ ተግባራዊነት የሚያግዙ ሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነዶች እንደሚዘጋጁም ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17hQt2QuS1/

ኦንላይን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የመረጃ ወቅታዊነትና ጥራትን እንደሚያሻሽል ተገለጸ፤
---------------------------- // -------------------------
(ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም) በአዲሱ የትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ዲጂታል ሥርዓት አጠቃቀም ላይ ለወረዳ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ባለሙያዎች እና ለ2ኛ ደረጃ የኣይሲቲ ትምህርት መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘጠኝ የሥልጠና ማዕከላት ላይ የአሰልጣኞች ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
የትምህርት መረጃ አመራርና ኣይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የውስጥ አቅም የበለጸገው ኦንላይን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የዘርፉን የመረጃ ወቅታዊነትና ጥራት የሚያሻሽል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከትምህርት ተቋማት የሚሰበሰቡ መረጃዎች ላይ የሚስተዋሉ የወቅታዊነት፣ጥራትና ተዓማኒነት ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችል እና የትምህርት መረጃ ሥርዓቱን የሚያዘምን ዲጂታል ሥርዓት ማበልጸግ መ/ቤቱ እየተገበራቸው ካሉ የሪፎርም አጃንዳዎች ማካከል አንዱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አቶ ሰብስብ አክለውም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ2018 ዓ.ም የትምህርት መረጃዎችን በዚህ ኦንላይን የመረጃ ሥርዓት ብቻ እንዲያስገቡ አቅጣጫ ተሰጥቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በፌዴራል የሚሰጠው የትምህርት ቤቶች የቁሳቁስና የድጎማ በጀትም የሚለቀቀው ወደ ሥርዓቱ በሚገባው የተማሪዎች መረጃ መሰረት ብቻ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BDttc22Db/