Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቡኢ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
----------------------------- // -------------------------

(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) መርሃ ግብሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል(ዶ/ር) እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ አስጀምረውታል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ስርዓቱ የገጠመንን የሞራል ስብራት ለማስተካከል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ሀገር በፍጥነት ማደግ ከፈለግን በትምህርት ላይ ትኩረት አድርገን መሥራት አለብን፤ በዚህም ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት በሀሉም አካባቢ ለመሥጠት በኢትዮጵያ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በርካታ ሀብት በማሰባሰብ የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገናና የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1GDF3gQYaW/
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤

በአጠቃላይ ትምህርት የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ እና ዕድሳት አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) ይጫኑ እና ያለዎትን አስተያየት ቀጥሎ ባለው ቅፅ ይሙሉ፤
https://forms.gle/o7kGXCRMxtLLc6NSA
ይህንን ረቂቅ መመሪያ በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር የተጠቀሰውን ሊንክ መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት በማሻሻል ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ከባቢ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤

-------------------------- // ----------------------------

(ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም) የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት በማሻሻል ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ከባቢ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤ የአርብቶ አደርና ልዩ ፍላጎት ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ መሰረት በቀለ እስካሁን ድረስ በት/ቤቶቻችን ምቹ አለመሆን እና በተዛማጅ ተግዳሮቶች በርካታ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት ሳይመጡ እንደቆዩ ገልጸዋል።

መንግስት ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው የተለየ ትኩረት የድጋፍ መስጫ ማዕከላትን በማቋቋሙ እና የት/ቤቶችን ከባቢ ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ እያደረገ በመምጣቱ እስከሁን ድረስ ት/ቤት መጥተው የማያውቁ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ትምህርት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

እንደ ሀገር እስከ አሁን ከ1400 በላይ ድጋፍ መስጫ ማዕከላት መቋቋማቸውን የጠቆሙት ሃላፊዋ በዚህ ዓመትም ተጨማሪ 172 የድጋፍ መስጫ ማዕከላት እንደሚቋቋሙ ገልጸው እነዚህ ማዕከላት ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ሽፋን እንደሚጨምሩ ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።

የድጋፍ መስጫ ማዕከላቱን ለማቋቋምና የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ቁሳቁሶች ለማሟላት በቂ ሀብት በአጋር ድርጅቶች መመደቡን ገልጸው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ስኬታማነቱ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው በመስራት ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ኢንጂነሪንግ፣አርትና ሂሳብ (STEAM) ማዕከል ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር አስተዋጽኦው የጎላ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፣
------------------------- // --------------------------
(ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም) የSTEAM ማዕከላት ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር አስተዋጽኦው የጎላ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የሂሳብ፣ሳይንስና ሥነ-ጥበብ ማበልጸጊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተሬሳ ገልጸዋል።

በዚህም የሀገር አቀፍ የSTEAM ስልጠና ማቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው ሰነዱ ወተግባራዊ መሆን ሲጀምር ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

የሳይንስ፣አርትና ሂሳብ ትምህርቶች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተግባር ተደግፈው ለተማሪዎች እንዲሰጡ የመምህራን ኮሌጆችን ጨምሮ በየደረጃው ባሉ የአጠቃላይ ትምህርት እርከን ላይ የሚያስተምሩ መምህራንን በSTEAM የሥልጠና ማዕቀፍ መሰረት ማብቃት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አቶ ታደሰ አክለውም በቀጣይ ለማዕቀፉ ተግባራዊነት የሚያግዙ ሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነዶች እንደሚዘጋጁም ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17hQt2QuS1/
ኦንላይን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የመረጃ ወቅታዊነትና ጥራትን እንደሚያሻሽል ተገለጸ፤

---------------------------- // -------------------------

(ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም) በአዲሱ የትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ዲጂታል ሥርዓት አጠቃቀም ላይ ለወረዳ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ባለሙያዎች እና ለ2ኛ ደረጃ የኣይሲቲ ትምህርት መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘጠኝ የሥልጠና ማዕከላት ላይ የአሰልጣኞች ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

የትምህርት መረጃ አመራርና ኣይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የውስጥ አቅም የበለጸገው ኦንላይን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የዘርፉን የመረጃ ወቅታዊነትና ጥራት የሚያሻሽል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከትምህርት ተቋማት የሚሰበሰቡ መረጃዎች ላይ የሚስተዋሉ የወቅታዊነት፣ጥራትና ተዓማኒነት ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችል እና የትምህርት መረጃ ሥርዓቱን የሚያዘምን ዲጂታል ሥርዓት ማበልጸግ መ/ቤቱ እየተገበራቸው ካሉ የሪፎርም አጃንዳዎች ማካከል አንዱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አቶ ሰብስብ አክለውም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ2018 ዓ.ም የትምህርት መረጃዎችን በዚህ ኦንላይን የመረጃ ሥርዓት ብቻ እንዲያስገቡ አቅጣጫ ተሰጥቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በፌዴራል የሚሰጠው የትምህርት ቤቶች የቁሳቁስና የድጎማ በጀትም የሚለቀቀው ወደ ሥርዓቱ በሚገባው የተማሪዎች መረጃ መሰረት ብቻ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BDttc22Db/
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎችና ደንብ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤

የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ3 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ረቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/oat5fXajoS5Fiwgj8
2. መደበኛ ያልሆነ የጎልማሶች የሙያ ክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና የአተገባበር ረቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/JFWANT1kUpYZmiLe8
3. የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች የሽግግር ረቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/3WpLE88aXBTFGZG67
4. የማታ ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ረለቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/ghKnfuhwx1u6eSJc7

በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ባስጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ጥቂት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎችን (አሁን 9ኛ ክፍል ገብተው እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች መካከል በማወዳደር) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በነዚህ ውስን ክፍት ቦታዎች ተማዝግባችሁ ለመማርና የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች https://sbs.moe.gov.et/apply በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
7ተኛው ዙር የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች ግምገማና የደረጃ ዕውቅና አሠጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።
---------------------------- // ---------------------------

(ጥር 08/2018 ዓ.ም) የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ያደረጉት ውይይት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታተሙ የምርምር ውጤቶች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የጠበቁና ተዓማኒነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል።

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት ቁልፍ መልክት የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች የግምገማና የእውቅና አሠጣጥ ሂደቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላቸው አሠራሮች ጋር የተጣጣሙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል።

የስራ ሀላፊው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ገለጻ የሀገር ውስጥ ጆርናሎች በሳይንሳዊው ማህበረሰብ ዘንድ ታይታን እንዲያተርፉ በትኩረትና በጥንቃቄ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

መሠል ተግባራት የሀገሪቱን የምርምር ባህል ከማሳደጋቸውም በላይ፣ ምሁራን በሥራዎቻቸው የሚገባቸውን ዕውቅና እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታና መደላድል የሚፈጥር መሆኑ በውይይት መድረኩ ላይ ተመላክቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/17yt2DeGgZ/