የትምህርት ስርዓቱን በማጎልበት ሂደት ውስጥ የቴክኖሎጂ አቅምን አጠናክሮ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ተገለፀ።
----------------------------- // ---------------------------
(የካቲት 01/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ምክክር የክልል ትምህርት ቢሮዎች ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን የትምህርት ዘርፉን በሚደግፍ አግባብ እና የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በሚያሳልጥ መልኩ የተጀመሩ ስራዎችን አስፍቶ የበለጠ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ አስገነዝበዋል።
ሚንስትር ዴኤታዋ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የትምህርት መሰረተ ልማትን ከማስፋት አንጻር በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ዕድሳት በስፋት መከናወኑን ጠቅሰዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተማሪዎችን ከታች ቀርጾ ለማውጣት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ትኩረት በመስጠት በስፋት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://www.facebook.com/share/p/1FA4Q3FoT8/

ባለፉት የለውጥ አመታት በትምህርቱ ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለጸ።
-------------------------- // -----------------------------
(የካቲት 01/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በትምህርት ዘርፉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተተገበሩ የሪፎርም ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
በዚህም በትምህርቱ ዘርፍ ባለፉት የለውጥ አመታት በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
እነዚህ የሪፎርም ስራዎች በዋናነት የትምህርቱን ስርዓት ከወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ጋር ለማጣጣምና የዜጎችን የዕውቀት አድማስ ለማስፋት ያለሙ መሆናቸውንም አመላክተዋል።
ከእነዚህ ስኬቶች መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በትምህርት ለትውልድ ፣በትምህርት ቤት ምገባ በስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣የመምህራንና የትምህርት ቤት ምገባ፣በማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሁም የትምህርትጥራትና ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር የተመዘገቡ ስኬቶች ተስፋ ሠጪ መሆናቸውን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤https://www.facebook.com/share/p/18HqHbsw4o/

አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የለውጥና መደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ሂደት የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቆመ።
--------------------------------- // ----------------------------
(የካቲት 01/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚገመግም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የዘርፉ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በዚህም የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተጀመረበትን ግለት ጠብቆ በህብረተሰቡ ዘንድ መቀዛቀዝ እንዳይኖር እስከመጨረሻው እንዲቀጥል በቁርጠኝነት መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በተለይም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትን ለማስፋፋት የተሰራው ሥራ የሚደነቅ ሲሆን የበለጠ በሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የአመራር አጀንዳ አድርጎ በቁርጠኝነት መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከዚህም ባለፈ የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥን ከመቀነስና ውጤታማነትን ከማረጋገጥ አኳያ የትምህርት ቤት ምገባን በበጀት በመደገፍ፤ ሀብት በማሰባሰብ እንዲሁም ማህበረሰቡን በስፋት በማሳተፍ ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባ አመላክተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17yudUaPuR/

የዚህ አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል።
በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ2018 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
----------------------- // ------------------------
(የካቲት 02/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ፈተናው በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደረበር አንስተው በዚህ ዓመት የሚሰጠውን ማጠናቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ለዚህም የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ይሰራል ብለዋል።
ክልሎች በዚህ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ኮምፒዩተር ፣ ኔትዎርክና አማራጭ የሀይል አቅርቦት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ሰጥተው መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበው ለተማሪዎች በቂ ሥልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BtjazXtwR/

መጪዎቹ ስድስት ወራት ከ1200 በላይ የሚሆኑ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለመገንባት መታቀዱ ተገለፀ።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች እንደ ሀገር ምንም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሌላቸው ወረዳዎችን የሚገነቡ ናቸው።
--------------------------------- // -----------------------------
(የካቲት 02/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቀሪ ስድስት ወራት የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ለክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ባገኘው የማቺንግ ፈንድ ድጋፍ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙና ምንም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሌላቸው 626 ወረዳዎች ውስጥ አንድ አንድ ትምህርት ቤት የሚገነባ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክትም ተጠቃሚ የሚሆኑ ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ሚኒስቴር በማቺንግ ፈንድ በየወረዳው በሚገነባው ትምህርት ቤት ተመሳሳይ ሌላ ት/ቤት እንዲገነቡ የሚያስገድድ በመሆኑ በቀጣይ 6 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የሚገነቡት ት/ቤቶች ቁጥር ከ1200 በላይ እንደሚሆን ሚንስትሩ አብራርተዋል።
በዚህም የትምህርት ቤቶቹ ዲዛይን ተሰርቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገለፀው በቀጣይ ከክልሎች ጋር በመሆን ኮንትራክተሮችን በመለየት ግንባታው በፍጥነት እንደሚጀመርም አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Eu35bqEFe/

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተማሪ መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
----------------------- // --------------------
(የካቲት 03/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት በተገኘ ድጋፍ ያሳተማቸውን 23.9 ሚሊየን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍት ጅቡቲ ወደብ ደርሰው ወደ ሃገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ እየተሰራ ነው።
ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የተማሪ መጽሃፍትን በሁሉም የትምህርት እርከኖች አንድ ለአንድ ለማድረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍትን ማሟላት የክልል ትምህርት ቢሮዎች ሃላፊነት መሆኑን ያነሱት የትምህርት ሚኒስትሩ ነገር ግን እንደ ሀገር የሚታየውን የተማሪ መጽሃፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ ሀብት በማፈላለግ ከ23.9 ሚሊየን በላይ መጽሃፍትን ማሳተም መቻሉን አብራርተዋል።
እነዚህ የታተሙት መጽሃፍት ጅቡቲ ወደብ ደርሰው የተወሰኑት ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸውን ጠቅሰው በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ ተጠናቀው በመግባት ለሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተቀናጀ ሁኔታ የሚሰራጩ በመሆኑ ክልሎች በፍጥነት በመረከብ ወደ ትምህርት ቤት በማውረድ ተማሪዎቹ መጽሃፍቱን እንዲያገኙ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1E65DoVwpX/

ትምህርት ሚኒስቴር ያሳተማቸው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍት ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸው ተገለጸ።
-------------------------- // -----------------------
(የካቲት 05/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ባገኘው ድጋፍ ያሳተማቸው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍት በገላን የመጽሃፍት ክዘና ማዕከል እየተራገፉ ይገኛል።
የትምህርት ሚኒስቴር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ ከአጋር አካላት ባገኘው ድጋፍ ከ23.9 ሚሊየን በላይ መጽሃፍትን በማሳተም ከጅቡቲ ወደ ሃገር ውስጥ ማጓጓዝ መጀመሩን የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ ገልጸዋል።
በዚህም ከ30 ኮንቴነር በላይ መጽሃፍት በገላን የክዘና ማዕከል መድረሳቸውን የገለጹት ሥራ አስተፈጻሚዋ አሁን የደረሱትን መጽሐፍት ክልሎች እንዲረከቡ ከስር ከስር የማሰራጨት ሥራ ይሰራል ብለዋል። በትክክል ለተማሪዎች መሰራጨታቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
መጽሐፍቶቹም ሲታተሙ በሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ዞኖች የሚያሳይ መለያ ኪውአር ኮድ (QR CODE) የተካተተ በመሆኑ የሁሉንም ዞኖች መጽሐፍቶች በመለያ ኮዳቸው መከታተል የሚቻልበት አሰራር መኖሩንም አብራርተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍትን አንድ ለአንድ ያደረሰ ሲሆን የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ እንዲቻል ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ ረገድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።