Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች ፕሮግራምና ስርዓተ-ትምህርት ከኢንዱስትሪው ጋር የተቆራኘ ተግባር ተኮር ዕውቀትና ክህሎት ያለው ባለሙያ ማፍራት በሚያስችል መልኩ እተቃኘ መሆኑ ተገለጸ።

------------------------- // --------------------------

‎(የካቲት 10/2018 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች ከኢንዱስትሪው ጋር የተቆራኘ መካከለኛ ባለሙያ እንዲያፈሩ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
‎
‎የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች ተግባር ተኮር ዕውቀትና ክህሎት ያለው መካከለኛ ባለሙያ እንዲያፈሩ መደረጉ ለአገር እድገት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።
‎
‎በትምህርት ዘርፉ የሪፎርም ዩኒቨርስቲዎቹ በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው ላይ አትኩረው እንዲሰሩ መደረጉንና ልዩ ልዩ ሰነዶች፣ ፍኖተ ካርታዎችና የትግበራ እቅዶች መዘጋጀታቸውን የገለጹት ዶ/ር ኤባ ዩኒቨርስቲዎቹ በትኩረት መስኮቻቸው ላይ የበለጠ አትኩረው እንዲሰሩ የትኩረትና ተልዕኮ መስክ ማስፈጸሚያ የስርዓተ ትምህርትና ፕሮግራሞች ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ መደረጉን ተናግረዋል።
‎
‎በዚህም በተዘጋጀው የስርዓተ ትምህርትና ፕሮግራሞች ማዕቀፍ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ተሰብስቦ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
‎
‎የምርምር (research) እና አጠቃላይ (Comprehensive) ዩኒቨርስቲዎች ፕሮግራምና ስርዓተ ትምህርት ማዕቀፍም በባለድርሻ አካላት ግብዓት ተሰጥቶበት ለውሳኔ ዝግጁ መሆኑን ዶ/ር ኤባ ጨምረው ተናግረዋል።
የ2018 ዓም የ12ኛ ክፍል አገር ከቀፍ ፈተና በክልሉ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ እንደሚሰጥ የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
------------------------- // ----------------------------

‎(የካቲት 11/2018 ዓ.ም) የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለጹት የ2018 ዓም የ12ኛ ክፍል አገረ አቀፍ ፈተና ከ2ሺ 400 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናው በበይነ መረብ ይሰጣል።
‎
‎በክልሉ በወረቀት የሚሰጥ የ12ኛ ክፍል ፈተና የለም ያሉት ኃላፊው በክልሉ በገጠርና በከተማ የሚገኙ 18 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፈተናውን በኦንላይን እንደሚያስፈትኑ ተናግረዋል።
‎
‎ተማሪዎች ከወዲሁ የበይነ-መረብ ፈተናውን እንዲለማመዱ የቴሌግራም ቻናል ተከፍቶላቸው በየቡድናቸው ጥያቄዎች እየተላኩላቸው በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
‎
‎በክልሉ ባለፈው ዓመት በወረቀት ከተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ይልቅ በበይነ መረብ በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ማምጣታቸውንና ይህም የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ከፍ እንዳደረገው አቶ ጌቱ ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1AzpUcRN6A/
እንደ ሀገር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽ ባልሆነባቸው ወረዳዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የትምህርት ቤት ግንባታ ለማካሄድ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ይገኛል።

-------------------------- // --------------------------

(የካቲት 16/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለሟሟላትና ለማሻሻል በቀረጸው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።

በተለይም ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ትኩረት በመስጠት እና በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ነጻና የግዴታ ትምህርት እንዲሆን በማመላከት ከ34000 በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።

ባለፉት ዓመታት እነዚህ ትምህርት ቤቶች ቢገነቡም የነበረውን ክፍተት በሚፈለገው ልክ መሙላት ባለመቻሉ በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፤ ይንንም ለመቅረፍና ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

በዚህም ‎ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽ ያልሆነባቸው አካባቢዎችና የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ወረዳዎች ልየታ መደረጉም ተገልጿል።

በነዚህ በተለዩ ወረዳዎች ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ትምህርት ሚኒስቴር በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጋፍ ስርዓት ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ግንባታውን ለማከናወን አቅዶ እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/18GP5FGeFV/
ብቃት ተኮር ትምህርትን /competency-based learning) ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
------------------- // -----------------
‎
‎(የካቲት 20/2018 ዓ.ም) የብቃት ተኮር ትምህርትን ወደ ተግባር ለማስገባት ከጃፓን ዮቶሃማ ዩኒቨርስቲ የመጡ ፕሮፌሰሮች በሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ አጋርተዋል።
የሂሳብ፣ የሳይንስና ስነ ጥበብ ማበልጸጊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተሬሳ በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ ተገኝተው በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ብቃት ተኮር ትምህርትን (competency-based learning) ወደ ተግባር ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

‎ይህንንም እውን ለማድረግ ከጃፓን ዓለም ከቀፍ ትብብር ድርጅት/ JICA / ጋር በመተባበር ከዮቶሃማ ዩኒቨርስቲ በመጡ የሙያው ፕሮፌሰሮች ከ5 ክልሎችና ከፌዴራል STEAM ዴስክ ለተውጣጡ 15 ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው የተሰጠውን ስልጠና ለማስፋትም የስልጠና ሞጁሎች ተዘጋጅተው በተመረጡ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ስልጠና መሰጠቱንም የዴስክ ኃላፊው አቶ ታደሰ አብራርተዋል።
‌‎
‎የጃፓን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር/JICA/ የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ተወካይ ሚስተር ያኩሺ ሂሮዩኪ በበኩላቸው ጃይካ በኢትዮጵያ ትምህርት ዘርፍ በተለይም በሂሳብ እና የሳይንስ ትምህርት የተማሪዎች ውጤት መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/14VqGkTKzCz/
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
--------------------- // ---------------------

(የካቲት 20/2018 ዓ.ም) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ያስገነባው የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት ተመርቋል።

ትምህርት ቤቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተገኝተው መርቀውታል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ዛሬ የተመረቀው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደ ሀገር ትምህርትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የምናደርገው ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል።

ከለውጡ ወዲህ እንደ በፊቱ የመሠረት ድጋይ አስቀምጦ መሄድ ቀርቷል ያሉ ሲሆን በትምህርት ሴክተሩ ፕሮጀክት ጀምሮ በአጠረ ጊዜ መጨረስ ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

የትምህርት ሴክተሩ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ውስጥ ወድቆ በመቆየቱ ከዚህ ለማላቀቅ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት እየተተገበሩ መሆኑንና በተለይም ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ መስራትና መተማመን የሚችል ትውልድ ለመፍጠር እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Di1oWZQG5/
ኢትዮጵያ የልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ደረጃ ለመውሰድ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ።
----------------------------- // ----------------------
‎
‎(የካቲት 20/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን '' አድዋ 130፣ ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል አገራዊ መሪ ቃል አክብረዋል።
‎
‎የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አድዋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ህያው ተምሳሌት በመሆኑ አባቶቻችንና እናቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነትና ላጎናጸፉን ድል ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
‎
‎ትምህርት ለምናደርገው የእድገትና የብልጽግና ጉዞ ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ጅምር ስራዎቻችንን አልቆ በመፈጸም እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትር ደኤታ አስገንዝበዋል።
‎
‎አገራችን ለዜጎቿ የተመቸችና የልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ደረጃ ለመውሰድ የትምህርት ዘርፉ ተዋናዮች የበኩላቸውን ድርሻ በላቀ የአገር ፍቅርና ስሜት መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም ክብርት ወ/ሮ አየለች አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17wXtv3gJt/
የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ በዓለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በተመለከተ መረጃ ለማግኘት https://rb.gy/lspeey
በትምህርት ዘርፉ ሁሉም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ።

--------------------- // -----------------------

(የካቲት 21/2018 ዓ.ም) በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ አሞራቴ ከተማ የተገነባው የአሞራቴ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፤ ተጨማሪ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት እቅድ ተይዟል።

በትምህርት ሚኒስቴርና በሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት የተገነባውን ትምህርት ቤት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ መርቀውታል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ዘርፉ ሁሉም ዜጎች አኩል የትምህርት እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ ዛሬ በዳሰነች የተመረቀው አዳሪ ትምህርት ቤት አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ የራሱን ሥራ ሲሰራ ልጆቹ ተረጋግተው የሚማሩበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል።

እነሱን ሳናስተምር ይች ሀገር ለሁላችንም እኩል ነች ማለት ከባድ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የዚህ ትምህርት ቤት መገንባት ትልቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CHREwWwgs/