Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቋንቋ ዲጂታይዝ አድርጎ ለትምህርት ግብዓት መጠቀም የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ።
---------------------- // ----------------------

(የካቲት 26/2018 ዓ.ም) የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነዱ በትምህርት ሚኒስቴር እና በባህልና ስፓርት ሚኒስቴር መካከል የተፈርሟል።

ስምምነቱ ሀገራችን ያሉ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋን ዲጂታይዝ በማድረግ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ እና ለትምህርት ግብዓትነት እንዲውሉ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል ።

በተለይም የጽሕፈት ሥርዓት ያላቸውን ቋንቋዎች ዲጂታይዝ የማድረግ፣ የመሰነድና የቴክኖሎጂ ቋንቋ የማድረግ ሐሳብን መሰረት አድርጎ በሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ቋንቋዎቹን ለማጎልበትና ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ፍይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብንና አገርን የመለወጥ ሚናቸውን በላቀ ቁርጠኝነት ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
‎ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የግማሽ ዓመት ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
‎
----------------- // ---------------------
‌‎(የካቲት 30/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ተቋማት አገርን ለመታደግ ከአገር መከላከያ ያልተናነሰ ሚና ያላቸው በመሆኑ ህብረተሰብንና አገርን የመለወጥ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
‎
‎ዩኒቨርስቲዎች ዕውቀትና እውነት ተዋህዶ የሚሰጥባቸው ቦታዎች በመሆናቸው ችግሮችን በጥናትና በውይይት በመፍታት ከመንግስትና ከህብረተሰቡ የሚጠብቅባቸውን አስተዋጽኦ መወጣት እንደሚጠባቸውም ክቡር ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
‎
‎ከዓለም የኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ እድገት አኳያም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሞራል መሠረታቸውን በማሳደግ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ጥቅም የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ሁኔታ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሀገር እድገትና መረጋጋት ኃላፊነታቸው የላቀ መሆኑንም አንስተዋል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የውጤት የአፈጻጸም አስተዳደር ስርዓት ወደ ተግባር እንዲገባ መደረጉን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1DzzFR8Hm8/
የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና ያለው በሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
--------------------- // --------------------

(የካቲት 30 /2018 ዓ.ም) 11ኛው ሀገር አቀፍ የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን ''የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና አለው!'' በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በአፋር ብሔራዊ ክልል መንግስት ሰመራ ከተማ ስኬታማ ስራዎችን በመጎብኘትና የፓናል ውይይት በማካሄድ ተከብሯል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር በአስቦዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና ያለው በሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚበ ገልጸዋል።

መርሃ-ግብሩ በለውጡ መንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝና ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑንም አያይዘው አንስተዋል።

ለት/ቤት ምገባ ውጤታማነት የሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የአጋር ድርጅቶችና የህብረተሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው ይህ መርሃ ግብር በተለይም አነስተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እፎይታን የሰጠና በተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና ጤንነት ላይ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1HuYqcWsau/
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ፤
-------------------- // ----------------------
‎
(መጋቢት 03/2018 ዓ.ም) ‎የከፍተኛ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ‎በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግማሽ ዓመት ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዘርፉ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎
‎እነዚህን የሪፎርም ተግባራት የበለጠ ማስተግበር የሚያስችሉ ፖሊሲዎች፣ ስታንዳርዶች፣ ማዕቀፎች እና መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።
‎
‎የዩኒቨርስቲ ራስ ገዝነትን በሚመለከት ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሪፎርም ይገባሉ ተብሎ እንደማይጠበቅና በሂደት እየገቡ እንደሚሄዱ ጠቁመው ዩኒቨርስቲዎች በተልዕኮ መስክ ልየታ /differentiation/ መሠረት ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አስታውሰዋል።
‎
‎ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ከዲጂታላይዜሽን ጋር በተያያዘም በቀጣይ በትኩረትና በርብርብ የሚሰራ የሪፎርም አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።
‎
‎የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት በበኩላቸው የሪፎርም አፈጻጸም ልዩነቶችን በማረም ተናቦና ተቀራርቦ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎
‎ከተልዕኮ መስክ ልየታ፣ የራስ ገዝነት፣ የዲጂታላይዜሽንና የሌሎች መሰል የሪፎርም ስራዎችን በግልጸኝነትና በቅደም ተከተል የቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎቻቸው በአመቱ ሥራ መፍጠራቸውን ወይም መቀጠራቸውን በጥናት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ።
--------------------- // -----------------------
(መጋቢት 4/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በአካዳሚክ ጉዳዮች ሪፎርም ተግባራት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

አውደጥናቱን የከፈቱት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎቻቸው በአመቱ ሥራ መፍጠራቸውን ወይም መቀጠራቸውን በጥናት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድ የሚደረገውን ጥናት በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጡ አቅጣጫዎች መሠረት የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ለማሻሻል እና ለፖሊሲ አውጪዎች ወሳኔ ግብዓትነት በሚጠቅም መልኩ መሰነድ አንደሚገባቸውም አንስተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው ለሥራ ፈጠራ ዝግጁ የሆነ አዕምሮ እንዲኖራቸውና የሥራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሥራ ፈጠራ ሀሳብና ክህሎት ማዳበሪያ ማዕከላት ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17a1RAJPik/
በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጸ።
------------------------ // ------------------------
(መጋቢት 05/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተሰራ ያለውን ሥራ በተመለከተ ከክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም በክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች በሁሉም የክፍል ደረጃ በተለይም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በወረደው ስትራቴጂ መሰረት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ከማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎች ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ውጪ ያላቸውን ጊዜ ተጠቅመው እንዲያጠኑ እና ቤተ-መጻህፍትን እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታዎች በየትምህርት ቤቶቹ መፈጠራቸውን አንስተዋል።

በተለይም ተማሪዎችን በማዘጋጀት ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በየጊዜው በመፍታትና በቀሩት ቀናት ጉድለቶችን በማሟላትና የተማሪዎችን ዝግጅት በቅርበት በመከታተል ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለፈተናው ስኬታማነት በትኩረት እንደሚሰሩ የክልል ቢሮ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለመምህራንና ለተማሪዎች አጋዥ የሆኑ የትምህርት ይዘቶችንና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድህረ-ገጽ (Portal) ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉም ተብራርቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1TyPMiyPuw/