የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና ያለው በሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
--------------------- // --------------------
(የካቲት 30 /2018 ዓ.ም) 11ኛው ሀገር አቀፍ የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን ''የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና አለው!'' በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በአፋር ብሔራዊ ክልል መንግስት ሰመራ ከተማ ስኬታማ ስራዎችን በመጎብኘትና የፓናል ውይይት በማካሄድ ተከብሯል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር በአስቦዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና ያለው በሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚበ ገልጸዋል።
መርሃ-ግብሩ በለውጡ መንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝና ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑንም አያይዘው አንስተዋል።
ለት/ቤት ምገባ ውጤታማነት የሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የአጋር ድርጅቶችና የህብረተሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው ይህ መርሃ ግብር በተለይም አነስተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እፎይታን የሰጠና በተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና ጤንነት ላይ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1HuYqcWsau/

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ፤
-------------------- // ----------------------
(መጋቢት 03/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግማሽ ዓመት ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዘርፉ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
እነዚህን የሪፎርም ተግባራት የበለጠ ማስተግበር የሚያስችሉ ፖሊሲዎች፣ ስታንዳርዶች፣ ማዕቀፎች እና መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።
የዩኒቨርስቲ ራስ ገዝነትን በሚመለከት ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሪፎርም ይገባሉ ተብሎ እንደማይጠበቅና በሂደት እየገቡ እንደሚሄዱ ጠቁመው ዩኒቨርስቲዎች በተልዕኮ መስክ ልየታ /differentiation/ መሠረት ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አስታውሰዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ከዲጂታላይዜሽን ጋር በተያያዘም በቀጣይ በትኩረትና በርብርብ የሚሰራ የሪፎርም አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት በበኩላቸው የሪፎርም አፈጻጸም ልዩነቶችን በማረም ተናቦና ተቀራርቦ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ከተልዕኮ መስክ ልየታ፣ የራስ ገዝነት፣ የዲጂታላይዜሽንና የሌሎች መሰል የሪፎርም ስራዎችን በግልጸኝነትና በቅደም ተከተል የቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎቻቸው በአመቱ ሥራ መፍጠራቸውን ወይም መቀጠራቸውን በጥናት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ።
--------------------- // -----------------------
(መጋቢት 4/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በአካዳሚክ ጉዳዮች ሪፎርም ተግባራት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡
አውደጥናቱን የከፈቱት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎቻቸው በአመቱ ሥራ መፍጠራቸውን ወይም መቀጠራቸውን በጥናት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡
በዚህ ረገድ የሚደረገውን ጥናት በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጡ አቅጣጫዎች መሠረት የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ለማሻሻል እና ለፖሊሲ አውጪዎች ወሳኔ ግብዓትነት በሚጠቅም መልኩ መሰነድ አንደሚገባቸውም አንስተዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው ለሥራ ፈጠራ ዝግጁ የሆነ አዕምሮ እንዲኖራቸውና የሥራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሥራ ፈጠራ ሀሳብና ክህሎት ማዳበሪያ ማዕከላት ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17a1RAJPik/

በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጸ።
------------------------ // ------------------------
(መጋቢት 05/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተሰራ ያለውን ሥራ በተመለከተ ከክልልና ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም በክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች በሁሉም የክፍል ደረጃ በተለይም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በወረደው ስትራቴጂ መሰረት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
ከማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎች ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ውጪ ያላቸውን ጊዜ ተጠቅመው እንዲያጠኑ እና ቤተ-መጻህፍትን እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታዎች በየትምህርት ቤቶቹ መፈጠራቸውን አንስተዋል።
በተለይም ተማሪዎችን በማዘጋጀት ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በየጊዜው በመፍታትና በቀሩት ቀናት ጉድለቶችን በማሟላትና የተማሪዎችን ዝግጅት በቅርበት በመከታተል ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለፈተናው ስኬታማነት በትኩረት እንደሚሰሩ የክልል ቢሮ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለመምህራንና ለተማሪዎች አጋዥ የሆኑ የትምህርት ይዘቶችንና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድህረ-ገጽ (Portal) ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉም ተብራርቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1TyPMiyPuw/

ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ሀገር በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ።
------------------------- // ---------------------
(መጋቢት 09/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች "50ኛ ዓመት የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በድምቀት ከክብረዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ሀገር በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማረጋገጥ በልማትና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ አይተኬ ሚና ያለው መሆኑን በማንሳት እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17MyBk6LsJ/

ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ በተዘጋጁ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
1. በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ https://forms.gle/KiRAQn6kjsZ6yymt6
2. የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ https://forms.gle/YEsQJwjE3wYUypJz6
3. በትምህርት ሚኒስቴር ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ
https://forms.gle/HLqZm83W2ANMWMLt5

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራዎቻቸውን በእውነት፣ በሐቀኝነትና በታማኝነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
----------------------- // ------------------------
(መጋቢት 14/2018 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በተዘጋጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ፣ የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ ደንብ ፣ ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራዎቻቸውን በእውነት፣ በሐቀኝነትና በታማኝነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
በተቋማቱ የሚካሄዱ የሪፎርም አጀንዳዎች ዓላማ ዩኒቨርስቲዎች ካሉባቸው ተለምዷዊ የአሰራር ልምዶች በማላቀቅ አርአያነት ባለው መልኩ ተልዕኳቸውን እንዲፈጽሙ ማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት የአመራር ምልመላ የሚፈለጉ የአመራር ክህሎቶችን መሠረት ያደረገ ግልጽነትና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ፣ ከኢንዱስትሪና የውጭ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጭምር በሚጋብዝ መልኩ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CNJ5oDpJf/