Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በኢትዮጵያ የትምህርት ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ያለመው የ2026 የኤድቴክ (EdTech) ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

---------------------------- // -----------------------

(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የትምህርት ቴክኖሎጂ (EdTech) ዘርፍን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመው የ2026 የኤድቴክ ሳምንት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።

መርሃ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ማልማትና ጥቅም ላይ ማዋል ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተለይም የትምህርት ስራውን የሚደግፉ ቴክኖሎጂዎች የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና ያላቸው በመሆኑ በስፋት በማልማትና ተደራሽ በማድረግ ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከዚህ አኳያም የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተቋማዊ አሰራር (System) በመቀየር ረገድ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/14cTCdFKk9V/
የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት እጥረትን ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፤
-------------------- // -------------------
(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም) የትምህርት ጥራቱን የበለጠ ለማሻሻል የቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት እጥረት የታየባቸው የትምህርት አይነቶችንና የክፍል ደረጃዎችን በመለየት ለማሳተም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሥርዓተ-ትምህርት ማበልጸጊያ ተ/ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዛፏ አብርሃ ገልጸዋል።

በዚህም እጥረት የታየባቸውን መጻህፍት በቀጣይ ለማሳተም የክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎችን የህትመት ፍላጎት ልየታ እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

እንደ መሪ ሥራ አስፈፃሚዋ ገለፃ የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት እጥረት የታየባቸው ደረጃዎችንና የትምህርት አይነቶችን ለይቶ ድጋፍ ለማድረግ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓትን በመጠቀም (EMIS) እና ከክልልና ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በተሰበሰበው መረጃ መሰረት በማድረግ የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት ህትመት ፍላጎት እየተለየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ የመጻህፍት ተማሪ ጥምርታን 1ለ1 ለማድረስ በተመረጡ አምስት የትምህርት አይነቶች የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ ሂሳብ፣ እንግሊዝኛ፣ አካባቢ ሳይንስ፣ ግብረገብና የስነ-ጥበብ ትምህርቶች መጽህፍትን ለማሳተም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል

ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ከ23.9 ሚሊየን በላይ የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍትን አሳትሞ ለክልሎች እያሰራጨ እንደሚገኘኝ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ እና ስሎቬኒያ በትምህርቱ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
-------------------//-------------------
(መጋቢት 23/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የስሎቬኒያ አምባሳደር የሆኑትን ክሪስቲና ራደጅን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ዘርፉ ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ያሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራትን ለአምባሳደሯ ያብራሩ ሲሆን ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ በማድረግ ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል የትምህርት ሥርዓት ለመዘርጋት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ገልጸውላቸዋል።

በኢትዮጵያ የስሎቬኒያ አምባሳደር ክርሲቲና ራደጅ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ እየተገበረቻቸው ያሉ የሪፎርም ተግባራት ከፍተኛ አድናቆት የሚቸራቸው መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ ሥራዎች በሚፈለገው መልኩ ውጤታማ እንዲሆኑ ሀገራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ማድርግ እንደምትፈልግ አንስተዋል።

በዚህም መሠረት አምባሳደሯ በአጠቃላይ እና በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በተለይም በነጻ የትምህርት እድል፣ በመምህራን ልውውጥ እና በተማሪዎችና መምህራን ሥልጠናዎች ላይ በጋራ መሥራት እንደሚፈልጉ አብራርተውላቸዋል።

በመጨረሻም ሁለቱ ወገኖች በትምህርት ልማት ዘርፉ የሚኖራቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከርና በቀጣይ ጊዜ የስሎቫኒያ ትምህርት ሚኒስትርን ያከተተ ውይይት ለማካሄድና የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ለመፈራረም ከስምምነት ደርሰዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስፔስ ኤክስ የስታርሊንክ አለም አቀፍ ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክተር ከሆኑት Ms. Rebecca Hunter ጋር ተወያዩ።
------------------------------- // ---------------------------

(ሚያዝያ 08/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ከስታርሊንክ አለም አቀፍ ፈቃድ አሰጣጥ ዋና ዳይሬክተር Ms. Rebecca Hunter ጋር ትምህርትን ዲጅታላይዝ ለማድርግ የስታርሊንክ ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ትምህርት ቤቶችን በሳተላይት ማገናኘት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉን ዲጅታላይዝ ለማድርግና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራች ያለችውን ሥራ አብራርተዋል።

በተለይም የፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል ፈተናን በበየነ መረብ ለመስጠት የተሰራውን ሥራ የጠቀሱ ሲሆን በዚህ ዓመትም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ገልጽዋል።

የስታርሊንክ አለም አቀፍ ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክተር Ms. Rebecca Hunter በበኩላቸው ስታርሊንክ በዓለም አቀፍ ደረጃ በበርካታ ሀገሮች በሳተላይት የተመሠረተ ፈጣን ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፋት የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CkDWZoQ25/
ሀገራዊ የምርምር ስራዎች ስነ-ምግባራቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ የሚያስችል የዲጂታል አሰራር ስርዓት ይፋ ሆነ
------------------------// ------------------------
(ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚካሄዱ የምርምር ስራዎች ጥራታቸውን እና የምርምር ስነ-ምግባር መርሆዎችን ጠብቀው እንዲከናወኑ የሚያስችል አዲስ የሶፍትዌር መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ ይህ አዲስ የዲጂታል ስርዓት በ European & Developing Countries Clinical Trials Partnership (EDCTP) ድጋፍ የለማ መሆኑን ጠቁመው፣ የምርምር ስራዎችን ለመገምገም፣ ለመከታተልና ለመደገፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የክትትልና የግምገማ ስራዎችን ማዘመን የምርምር ስራዎች በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1LCmRraKsH/
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተተገብሩ ባሉ የለውጥ አጀንዳዎች ላይ የፖሊሲ ጥናት መደረጉ ተገልጸ።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተተገበሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ አጀንዳዎች በጥሩ ሂደት ላይ ስለመሆናቸው በተካሄዱ የፖሊሲ ጥናቶች መረጋገጡም ተመላክቷል።
=====================================
(ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በትግበራ ላይ ባሉ አራት ዋና ዋና የለውጥ አጀንዳዎች ዙሪያ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተውጣጡ ምሁራን ጥናት አካሂዷል።

ምሁራኑ ባካሄዱት ጥናት መሰረት የተገኙ ውጤቶች ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተተገበሩ ያሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራት አተገባበር ሂደት ምን እንደሚመሰል ለማወቅና መስተካከል ያለባቸውን አስቀድሞ ለማስተካከል ምሁራንን ያሳተፈ ጥናት መካሄዱን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የፖሊሲ ጉዳዮች ባለቤት በመሆኑ የወጡ ፖሊሲዎች አተገባበር ምን ይመስላል የሚለውን እያስጠና መፍትሄ እያስቀመጠ መሄድ እንዳለበት ጠቅሰው መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

ክቡር አቶ ኮራ አክለውም የፖሊሲም ሆነ የለውጥ አጀንዳዎች ወደ ተግባር እንደገቡ በሂደት በሚፈለገው መልኩ እየተተገበሩና ውጤት እያመጡ ስለመሆናቸው በጥናት ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1EovRLkTuV/