Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 1452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱን ተገለጸ።
-------------------------- // --------------------------
(ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 1452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 1452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱን ገልጸዋል።

አዲስ የሚገነቡት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ባልተገነቡባቸው 727 ወረዳዎች ውስጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ ሀገር ሊገነቡ ከታቀዱት 1452 ትምህርት ቤቶች መካከል ግማሽ የሚሆኑት የሚገነቡት በትምህርት ሚኒስቴር መሆኑንና ቀሪዎቹ ደግሞ በክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መሆኑን አንስተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ለሚያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች የሚያስፈልገውን 40 ሚሊዮን ዶላር ከአጋር ድርጅቶች እርዳታ ማግኘቱን ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BNyXtsG5f/
የትምህርት ዘርፉን ከነበረበት ችግሮች ለማውጣት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
---------------------------- // -----------------------
‎
(ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ "የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ሐሳብ በተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች በሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ላይ በትምህርት ዘርፉ የተከናወኑና የተመዘገቡ ስኬቶችን አቅርበዋል።

በዚሁ ጊዜ ከለውጡ በፊት የትምህርቱ ዘርፍ በእጅጉ የተጎዳ፣ ሰፊ እና አፋጣኝ ተሀድሶ ከሚያስፈልጋቸው ዘርፎች አንዱ እንደነበር አብራርተዋል።

በተለይም የትምህርት ስርዓቱ እጅግ የተዳከመ፣ የመሠረተ ልማት ጥራትና የግብዓት እጥረት የነበረበት ፣ የተማሪ-መምህር፣ የተማሪ-ክፍል ጥምርታ አለመመጣጠን፣ ለትምህርት ዓይነቶች ብቁ የሆኑ መምህራን አለመኖርና የሚሉትና መሰል ችግሮች እነደነበሩበት አንስተዋል።

በተጨማሪም የስርዓተ ትምህርት አግባብነትና የመጻሕፍት ተደራሽነት ችግሮች፣ ኢ-ፍትሃዊነትና ኢ-እኩልነት፣ የትምህርት ሴክተሩ ትክክለኛነት መዳከም፣ ዝቅተኛ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተደራሽነት መኖር ከብዙ ማነቆዎች ጥቂቶች እንደነበሩ ዘርዝረዋል።
‎
በዚህም በጥናት በተደገፈ መልኩ የትምህርት ዘርፉን ፍላጎቶች እና ተግዳሮቶች በመለየት ከተመዘገቡ ዋና ዋና ለውጦች መካከል የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ፣ የመጻሕፍት ህትመት ስርጭትና ተደራሽነት፣ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበራቸውን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Kmq78hMWn/
የአንድ መሶብ አገልግሎት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማቀናጀት ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚያችል ተጠቆመ፤

----------------------- // --------------------------
‎
‎(ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም) በአንድ መስኮት መሶብ አገልግሎት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ አያያዝ ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት የአንድ መሶብ አገልግሎት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ አገለግሎቶችን በማቀናጀት ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ መስኮት መሶብ አገልግሎትን ወደ ስራ በማስገባት ለተጠቃሚዎች የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸውም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
‎
‎ዩኒቨርስቲዎች የመረጃ አያያዝ ስርዓታቸውም በማዘመንና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
‎

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
በመጪው የትምህርት ዘመን በራስ ገዝነት ሽግግር መመሪያ መሰረት 60 በመቶና ከዚያም በላይ የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ ተገለጸ።

------------------------- // -------------------------
‎
‎በዛሬው እለት ወደ ራሰ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሽግግር የሚገቡ ዩኒቨርስቲዎች የዝግጅት ግምገማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ለገለልተኛ ገምጋሚ ቡድኑ ተሰጥቷል።
‎
‎መድረኩ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) እንደገለጹት ዩኒቨርስቲዎች በአዋጅ ቁጥር1294/2015 መሠረት ወደ ራስገዝነት ሽግግር እንዲገቡ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።

‎በተለይም በመጪው የትምህርት ዘመን ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጀው መሥፈርት መሠረት የራሳቸውን ግለ ግምገማ በማድረግ ለትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።
‎
‎ተቋማቱ ያቀረቡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግም የትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅቶቻቸውን በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎች በተውጣጡ ፕሮፌሰሮችና ሌሎች ምሁራን ገለልተኛ ግምገማ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ እየተገባ እንደሆነ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Ft5oDM2q2/
ትምህርትን ሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

------------------------ // --------------------------

(ግንቦት 05/2018 ዓ.ም) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የአሶሳ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተከናውኗል።

የትምህርት ቤቶቹን ግንባታ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሌ ሀሰን እና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት አለበት በሚል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

እንደ ሀገር ለማደግ ከፈለግን ያለ ልዩነት በፍትሃዊነት የተማረ ትውልድ ያስፈልገናል ለዚህ ደግሞ ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት አለብን ብለዋል።

እነዚህ ዛሬ ግንባታቸው የተጀመረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች የሚፈሩባቸውና ሌሎች ትምህርት ተቋማት ተሞክሮ መቅሰሚያ መሆናቸውን አንስተው ሙሉ ወጪያቸው በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሸፈን ገልፀዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17jjjMDEbi/
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ።
---------------------- // -----------------------

(ግንቦት 05/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ኮራ ጡሹኔ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ እውቀት እና ምርምር የሚደረግባቸው ተቋማት መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል።

ይህ ደግሞ በነፃነት ማሰብና መናገር ይፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎች ለእንዲህ ዓይነት ነፃነት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከምንም ዓይነት ፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ መሆን አለበቸው፤ ለዚህም የዩኒቨርሲቲ አመራር ምደባ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚወጣ ማስታወቂያ በውድድር በእውቀትና በችሎታ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1JdN7SncWT/