Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በመጪው የትምህርት ዘመን በራስ ገዝነት ሽግግር መመሪያ መሰረት 60 በመቶና ከዚያም በላይ የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ ተገለጸ።

------------------------- // -------------------------
‎
‎በዛሬው እለት ወደ ራሰ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሽግግር የሚገቡ ዩኒቨርስቲዎች የዝግጅት ግምገማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ለገለልተኛ ገምጋሚ ቡድኑ ተሰጥቷል።
‎
‎መድረኩ ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) እንደገለጹት ዩኒቨርስቲዎች በአዋጅ ቁጥር1294/2015 መሠረት ወደ ራስገዝነት ሽግግር እንዲገቡ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።

‎በተለይም በመጪው የትምህርት ዘመን ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጀው መሥፈርት መሠረት የራሳቸውን ግለ ግምገማ በማድረግ ለትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።
‎
‎ተቋማቱ ያቀረቡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግም የትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅቶቻቸውን በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎች በተውጣጡ ፕሮፌሰሮችና ሌሎች ምሁራን ገለልተኛ ግምገማ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ እየተገባ እንደሆነ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Ft5oDM2q2/
ትምህርትን ሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

------------------------ // --------------------------

(ግንቦት 05/2018 ዓ.ም) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የአሶሳ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተከናውኗል።

የትምህርት ቤቶቹን ግንባታ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሌ ሀሰን እና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት አለበት በሚል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

እንደ ሀገር ለማደግ ከፈለግን ያለ ልዩነት በፍትሃዊነት የተማረ ትውልድ ያስፈልገናል ለዚህ ደግሞ ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት አለብን ብለዋል።

እነዚህ ዛሬ ግንባታቸው የተጀመረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች የሚፈሩባቸውና ሌሎች ትምህርት ተቋማት ተሞክሮ መቅሰሚያ መሆናቸውን አንስተው ሙሉ ወጪያቸው በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሸፈን ገልፀዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17jjjMDEbi/
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ።
---------------------- // -----------------------

(ግንቦት 05/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ኮራ ጡሹኔ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ እውቀት እና ምርምር የሚደረግባቸው ተቋማት መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል።

ይህ ደግሞ በነፃነት ማሰብና መናገር ይፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎች ለእንዲህ ዓይነት ነፃነት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከምንም ዓይነት ፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ መሆን አለበቸው፤ ለዚህም የዩኒቨርሲቲ አመራር ምደባ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚወጣ ማስታወቂያ በውድድር በእውቀትና በችሎታ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1JdN7SncWT/
ክብርት ወ/ሮ አየለች እሽቴ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተገኝተው በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተገነቡ ተቋማትን ጎበኙ፤

------------------------- // ---------------------------

(ግንቦት 06/2018 ዓ.ም) ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በመገኘት በ“ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ማዕቀፍ የተገነቡና የተሻሻሉ የትምህርት ተቋማትን ጎብኝተው የትምህርት ልማቱ እያስመዘገበ ያለውን አበረታች ውጤት አድንቀዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጉብኝታቸው ወቅት በክልሉ ህብረተሰብ፣ በመንግስት እና በባለድርሻ አካላት ትብብር የተከናወኑ የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ስራዎች ለተማሪዎች የተሻለ የመማሪያ ከባቢ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ዓመታት በ“ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ስር በመላ ሀገሪቱ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎች በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በተለይም ለተማሪዎች ምቹና ዘመናዊ የመማሪያ አካባቢ መፍጠር ለትምህርት ጥራት መሻሻል መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በጉብኝታቸው ያስተዋሉት እንቅስቃሴ አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆኑን የገለጹት ክብርት ወ/ሮ አየለች፤ ይህን የተጀመረ መልካም ጅምር ይበልጥ በማጠናከር የትምህርት ተቋማትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሁሉም አካላት ተሳትፎ በቀጣይነት ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1B162iFFif/
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።
-------------------------- // -------------------------

(ግንቦት 07/2018 ዓ.ም) ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል።
በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።
ምንም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሌላቸው ወረዳዎችን ተደራሽ ማድረግ አስመለክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሰጡት ማብራሪያ https://youtu.be/0kf4c2D7-YA

YouTube