በትምህርት ሚኒስቴር፣ በውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የ5 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት ተፈረመ፤
------------------------------- // ----------------------------
(ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር፣ በዩናይትድ ኪንግደም የውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማሻሻል የሚያስችል የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በለንደን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የአለም የትምህርት ፎረም 2026 ጎን ለጎን የትምህርት ሚኒስቴር፣ በውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማጠናከርና ለማሻሻል የሚያስችል የአምስት ሚሊየን ፓውንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የመምህራን አቅምን ለማጎልበት እና የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ተገልጿል።
ይህ ስምምነት የአምስት ሚሊየን ፓውንድ ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ተብሏል።
በተጨማሪም ስምምነቱ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ዓለም አቀፍ ትብብር የሚያጠናክር ሲሆን፣ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የቋንቋ ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ አፈጻጸም ረቂቅ ደንብን አጸደቀ።
(ግንቦት 18/2018 ዓ.ም) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ አፈጻጸምን ለመደንገግ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በስፋት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ምክር ቤቱ በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ፣ አስፈላጊ ግብአቶችን በማከል ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።
ደንቡ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመንግስት የበጀት ድጋፍ በታወቀ የጥቅል በጀት ስርዓት ላይ በመመስረት፣ የፋይናንስ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትን እና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ያለመ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ወጪ በራሳቸው የመሸፈን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያሳድጉ ያግዛል።
በተጨማሪም፣ በተቋማቱ መካከል ተመጣጣኝ የመማርና ማስተማር ጥራት፣ የአገልግሎት ፍትሃዊነት እና ኃላፊነት የተሞላበት አሰራር እንዲጠናከር ያስችላል።
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ See less

በኢትዮጵያና በቤልጂየም መካከል ያለው የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ።
-------------------------- // -----------------------
(ግንቦት 23/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በኢትዮጵያ የቤልጅየምን አምባሳደር የሆኑትን ዶ/ር አኔሊስ ቬርስቲቼልን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ እየተተገበሩ ስላሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራት ለክብርት አምባሳደሯ አብራርተዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት መስክ በሰው ኃይል ልማት ፣ በጥናትና ምርምር ፣በልምምድ ልውውጥና በሌሎችም ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነቶች መኖሩን አንስተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ራስገዝነትን ጨምሮ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጥራት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያና ጅቡቲ የቤልጂየም አምባሳደርና የአፍሪካ ሕብረት የኢጋድና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ ዶክተር አኔሊስ ቨርስቲቼል በበኩላቸው በኢትዮጵያና በቤልጂየም መንግስታት መካከል 120 ዓመታትን ያስቆጠረ ወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መኖሩን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BGKjx7TpH/

ትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ በኦፍላይን የሚሰራና ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን ማመንጨት የሚችል “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI Teacher Assistant) የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አዋለ።
(ግንቦት 28/2018 ዓም) ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የዕለት ተዕለት የሥራ ጫና በእጅጉ የሚቀንስ፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት (Fully Offline) የሚሰራ እና ራሱን ችሎ ተግባራትን የሚያከናውን ኤጀንቲክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት Agentic AI Teacher Assistant) መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አውሏል።
የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ መተግበሪያ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ (Cloud) ቴክኖሎጂ ላይ የማይተማመን፣ ይልቁንም በአካባቢያዊ ኮምፒውተር (Local Machine) ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሰራና በውስጥ አቅም የበለጸገ የቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል። ሙሉ ዜናውን ለማግኘት
https://web.facebook.com/share/p/1L47ihE7jo/

በመጪው የትምህርት ዘመን 1452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር የግንባታ ማስጀመር ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ነው።
(ግንቦት 28/2018 ዓ.ም )በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች ትብብር እየተገነቡ የሚገኙ 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እስከ መጪው ነሐሴ መጨረሻ ድረስ በማጠናቀቅ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ለማብቃት የግንባታ ማስጀመር ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆናቸውን የትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ከተማ መስቀላ ገልጸዋል።
ዶ/ር ከተማ እንዳስታወቁት፣ ከአጠቃላይ 1,452 ትምህርት ቤቶች መካከል 726 በትምህርት ሚኒስቴር እና 726 በክልል ትምህርት ቢሮዎች አማካኝነት ይገነባሉ ብለዋል።
የግንባታ ሂደቱንም ለማፋጠን እስካሁን በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነቡ 341 ትምህርት ቤቶች እና በክልሎች የሚገነቡ 64 ትምህርት ቤቶች የኮንትራት ስምምነት ከተቋራጮች ጋር ተፈርሞ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን፣ 25 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የግንባታ ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸውን አብራርተዋል።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች በመጪው የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ሲበቁ ከ87,000 በላይ ሕፃናትን ተቀብለው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን በ15 በመቶ እንደሚያሳድጉ ተገልጿል።
ሥራ አስኪያጁ አክለውም በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ሂደታቸው የዘገየባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ቀሪውን ጊዜ በተጠናከረ ቁርጠኝነት በመጠቀም ትምህርት ቤቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አስፈላጊውን ትኩረትና ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ትምህርት የቻይንኛ ቋንቋን ለማስተማር የሚያስችል የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት ትላንት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሃይ በጋራ ፈርመውታል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በባህል ልውውጥ ዙሪያ አዳዲስ ምዕራፎችን የሚከፍት መሆኑ ተመልክቷል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስምምነቱ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ በቱሪዝም፣ በህዝብ ለህዝብ ትስስር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
"ዜጎቻችን የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲማሩ መደረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ትልቅ እድል ይፈጥራል" ያሉት ፕሮፌሰር ክንደያ፣ በተለይም ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ዘርፍ የደረሰችበትን የላቀ ደረጃ እና የነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) ለኢትዮጵያውያን የምታመቻችበትን ሁኔታ ለማሳለጥ ስምምነቱ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።
ስምምነቱ በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ በመምህራን ስልጠና እና በቁሳቁስ አቅርቦት ላይ የቴክኒክና የቻይና ቋንቋ መምህራንን ድጋፍ የሚያጠቃልል ሲሆን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የዕውቀት ልውውጥን እና የስኮላርሺፕ ዕድሎችንም ያሰፋል ተብሏል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት፦ https://web.facebook.com/share/p/195umB3hut/