በኢትዮጵያና በቤልጂየም መካከል ያለው የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ።
-------------------------- // -----------------------
(ግንቦት 23/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በኢትዮጵያ የቤልጅየምን አምባሳደር የሆኑትን ዶ/ር አኔሊስ ቬርስቲቼልን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ እየተተገበሩ ስላሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራት ለክብርት አምባሳደሯ አብራርተዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት መስክ በሰው ኃይል ልማት ፣ በጥናትና ምርምር ፣በልምምድ ልውውጥና በሌሎችም ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነቶች መኖሩን አንስተዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ራስገዝነትን ጨምሮ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጥራት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያና ጅቡቲ የቤልጂየም አምባሳደርና የአፍሪካ ሕብረት የኢጋድና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ ዶክተር አኔሊስ ቨርስቲቼል በበኩላቸው በኢትዮጵያና በቤልጂየም መንግስታት መካከል 120 ዓመታትን ያስቆጠረ ወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መኖሩን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BGKjx7TpH/

ትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ በኦፍላይን የሚሰራና ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን ማመንጨት የሚችል “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI Teacher Assistant) የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አዋለ።
(ግንቦት 28/2018 ዓም) ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የዕለት ተዕለት የሥራ ጫና በእጅጉ የሚቀንስ፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት (Fully Offline) የሚሰራ እና ራሱን ችሎ ተግባራትን የሚያከናውን ኤጀንቲክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት Agentic AI Teacher Assistant) መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አውሏል።
የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ መተግበሪያ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ (Cloud) ቴክኖሎጂ ላይ የማይተማመን፣ ይልቁንም በአካባቢያዊ ኮምፒውተር (Local Machine) ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሰራና በውስጥ አቅም የበለጸገ የቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል። ሙሉ ዜናውን ለማግኘት
https://web.facebook.com/share/p/1L47ihE7jo/

በመጪው የትምህርት ዘመን 1452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር የግንባታ ማስጀመር ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ነው።
(ግንቦት 28/2018 ዓ.ም )በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች ትብብር እየተገነቡ የሚገኙ 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እስከ መጪው ነሐሴ መጨረሻ ድረስ በማጠናቀቅ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ለማብቃት የግንባታ ማስጀመር ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆናቸውን የትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ከተማ መስቀላ ገልጸዋል።
ዶ/ር ከተማ እንዳስታወቁት፣ ከአጠቃላይ 1,452 ትምህርት ቤቶች መካከል 726 በትምህርት ሚኒስቴር እና 726 በክልል ትምህርት ቢሮዎች አማካኝነት ይገነባሉ ብለዋል።
የግንባታ ሂደቱንም ለማፋጠን እስካሁን በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነቡ 341 ትምህርት ቤቶች እና በክልሎች የሚገነቡ 64 ትምህርት ቤቶች የኮንትራት ስምምነት ከተቋራጮች ጋር ተፈርሞ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን፣ 25 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የግንባታ ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸውን አብራርተዋል።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች በመጪው የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ሲበቁ ከ87,000 በላይ ሕፃናትን ተቀብለው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን በ15 በመቶ እንደሚያሳድጉ ተገልጿል።
ሥራ አስኪያጁ አክለውም በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ሂደታቸው የዘገየባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ቀሪውን ጊዜ በተጠናከረ ቁርጠኝነት በመጠቀም ትምህርት ቤቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አስፈላጊውን ትኩረትና ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ትምህርት የቻይንኛ ቋንቋን ለማስተማር የሚያስችል የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት ትላንት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሃይ በጋራ ፈርመውታል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በባህል ልውውጥ ዙሪያ አዳዲስ ምዕራፎችን የሚከፍት መሆኑ ተመልክቷል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስምምነቱ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ በቱሪዝም፣ በህዝብ ለህዝብ ትስስር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
"ዜጎቻችን የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲማሩ መደረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ትልቅ እድል ይፈጥራል" ያሉት ፕሮፌሰር ክንደያ፣ በተለይም ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ዘርፍ የደረሰችበትን የላቀ ደረጃ እና የነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) ለኢትዮጵያውያን የምታመቻችበትን ሁኔታ ለማሳለጥ ስምምነቱ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።
ስምምነቱ በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ በመምህራን ስልጠና እና በቁሳቁስ አቅርቦት ላይ የቴክኒክና የቻይና ቋንቋ መምህራንን ድጋፍ የሚያጠቃልል ሲሆን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የዕውቀት ልውውጥን እና የስኮላርሺፕ ዕድሎችንም ያሰፋል ተብሏል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት፦ https://web.facebook.com/share/p/195umB3hut/

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና የሰዎችን ደኅንነት ያከበሩ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል የምርምር ሥነ-ምግባር ግምገማና እውቅና አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
======================================
(ሰኔ 5 /2018 .ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን የጠበቁና የሰዎችን ደኅንነት ያከበሩ እንዲሆኑ የሚያስችል የምርምር ሥነ-ምግባር ግምገማና እውቅና አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ገልጸዋል።
ይህ አዲሱ ሥርዓት በተለይም ከሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ምርምሮች ከመጀመራቸው በፊት የሰዎችን ጥቅምና ጉዳት፣ ሂደቱን እንዲሁም የምርምር ቦታውን በጥብቅ መስፈርት በመመዘን ፍቃድ ለመስጠትና ለመከልከል የሚያስችል ጠንካራ መዋቅር የሚዘረጋ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን የግምገማ ሥርዓት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በዚህ ረገድ የተሻለ ልምድ ካለው ከኡጋንዳ ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት ጋር ጠንካራ የሁለትዮሽ ትብብርን አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑንም ገለጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒሰትር ዴኤታው አከለውም ይህ ሥርዓት፣ የሀገሪቱ የሳይንስና ምርምር ዘርፍ በሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ፍጹም አመኔታና ግልጽነት እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ተናገረዋል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት ፦ https://web.facebook.com/share/p/18sgZ3qPzG/

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቤቶች ምገባን የሚደግፍ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ
የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመውን የትምህርት ቤቶች ምገባ የሚደግፍን ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ፕሮጀክቱ የተጀመረወን የትምህርት ቤት ምገባ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ተማሪዎች በቂና ተመጣጣኝ ምግብ በማግኘት በትምህርታቸው ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
ለፕሮጀክቱ ስኬት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አጋር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን ገልጸው፣ ተማሪዎች በጤናማ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችሉ መሰል ፕሮጀክቶች በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንዲስፋፉ ምሳሌ ይሆናል ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ቤት ምገባ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ በሞዴልነት የሚጠቀስ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ ይከናወን የነበረው የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከላዊ ሥርዓት በማምጣት ትልቅ የሪፎርም ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። ይህም የተማሪዎች የምግብ ዝግጅትና ስርጭት ሂደቱን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ዘላቂ እንዲሆን እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/14fY9nME2GB/

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራን የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሀላፊነት በሚገባ እንዲወጡ ተጠየቀ።
------------------------- //---------------------------
(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም) ብቃትን መሰረት ያደረገ መማር ማስተማርን በሚመለከት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመምህራን እየተሰጠ ይገኛል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች በመምረጥና በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በማስተማር የሀገሪቱን የወደፊት የሰው ሀብት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች በአካዳሚክ ብቃት፣ በሥነ-ምግባር፣ በአመራር ክህሎት እና በሀገራዊ እሴቶች የተገነባ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የተገልጸ ሲሆን፣
ይህንን ሀገራዊ ተልዕኮ በተሻለ ብቃት ለማሳካትም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት መሰረት ባደረገና የመማርና የማስተማር ሥርዓት ላይ ያተኮረ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል።
ስልጠናው በትምህርት ቤቶቹ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገሩም በላይ፣ መምህራን ተማሪዎችን የእውቀት ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ችግር ፈቺዎች፣ ፈጠራ ባለቤቶች እና ሀገራቸውን የሚያገለግሉ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘመናዊ የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን እንዲላበሱ ያስችላቸዋልም ተብሏል።