በኢትዮጵያ ትምህርት የቻይንኛ ቋንቋን ለማስተማር የሚያስችል የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት ትላንት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሃይ በጋራ ፈርመውታል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በባህል ልውውጥ ዙሪያ አዳዲስ ምዕራፎችን የሚከፍት መሆኑ ተመልክቷል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስምምነቱ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ በቱሪዝም፣ በህዝብ ለህዝብ ትስስር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
"ዜጎቻችን የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲማሩ መደረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ትልቅ እድል ይፈጥራል" ያሉት ፕሮፌሰር ክንደያ፣ በተለይም ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ዘርፍ የደረሰችበትን የላቀ ደረጃ እና የነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) ለኢትዮጵያውያን የምታመቻችበትን ሁኔታ ለማሳለጥ ስምምነቱ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።
ስምምነቱ በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ በመምህራን ስልጠና እና በቁሳቁስ አቅርቦት ላይ የቴክኒክና የቻይና ቋንቋ መምህራንን ድጋፍ የሚያጠቃልል ሲሆን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የዕውቀት ልውውጥን እና የስኮላርሺፕ ዕድሎችንም ያሰፋል ተብሏል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት፦ https://web.facebook.com/share/p/195umB3hut/

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና የሰዎችን ደኅንነት ያከበሩ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል የምርምር ሥነ-ምግባር ግምገማና እውቅና አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
======================================
(ሰኔ 5 /2018 .ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን የጠበቁና የሰዎችን ደኅንነት ያከበሩ እንዲሆኑ የሚያስችል የምርምር ሥነ-ምግባር ግምገማና እውቅና አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ገልጸዋል።
ይህ አዲሱ ሥርዓት በተለይም ከሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ምርምሮች ከመጀመራቸው በፊት የሰዎችን ጥቅምና ጉዳት፣ ሂደቱን እንዲሁም የምርምር ቦታውን በጥብቅ መስፈርት በመመዘን ፍቃድ ለመስጠትና ለመከልከል የሚያስችል ጠንካራ መዋቅር የሚዘረጋ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን የግምገማ ሥርዓት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በዚህ ረገድ የተሻለ ልምድ ካለው ከኡጋንዳ ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት ጋር ጠንካራ የሁለትዮሽ ትብብርን አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑንም ገለጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒሰትር ዴኤታው አከለውም ይህ ሥርዓት፣ የሀገሪቱ የሳይንስና ምርምር ዘርፍ በሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ፍጹም አመኔታና ግልጽነት እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ተናገረዋል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት ፦ https://web.facebook.com/share/p/18sgZ3qPzG/

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቤቶች ምገባን የሚደግፍ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ
የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመውን የትምህርት ቤቶች ምገባ የሚደግፍን ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ፕሮጀክቱ የተጀመረወን የትምህርት ቤት ምገባ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ተማሪዎች በቂና ተመጣጣኝ ምግብ በማግኘት በትምህርታቸው ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
ለፕሮጀክቱ ስኬት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አጋር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን ገልጸው፣ ተማሪዎች በጤናማ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችሉ መሰል ፕሮጀክቶች በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንዲስፋፉ ምሳሌ ይሆናል ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ቤት ምገባ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ በሞዴልነት የሚጠቀስ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ ይከናወን የነበረው የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከላዊ ሥርዓት በማምጣት ትልቅ የሪፎርም ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። ይህም የተማሪዎች የምግብ ዝግጅትና ስርጭት ሂደቱን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ዘላቂ እንዲሆን እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/14fY9nME2GB/

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራን የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሀላፊነት በሚገባ እንዲወጡ ተጠየቀ።
------------------------- //---------------------------
(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም) ብቃትን መሰረት ያደረገ መማር ማስተማርን በሚመለከት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመምህራን እየተሰጠ ይገኛል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች በመምረጥና በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በማስተማር የሀገሪቱን የወደፊት የሰው ሀብት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች በአካዳሚክ ብቃት፣ በሥነ-ምግባር፣ በአመራር ክህሎት እና በሀገራዊ እሴቶች የተገነባ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የተገልጸ ሲሆን፣
ይህንን ሀገራዊ ተልዕኮ በተሻለ ብቃት ለማሳካትም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት መሰረት ባደረገና የመማርና የማስተማር ሥርዓት ላይ ያተኮረ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል።
ስልጠናው በትምህርት ቤቶቹ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገሩም በላይ፣ መምህራን ተማሪዎችን የእውቀት ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ችግር ፈቺዎች፣ ፈጠራ ባለቤቶች እና ሀገራቸውን የሚያገለግሉ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘመናዊ የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን እንዲላበሱ ያስችላቸዋልም ተብሏል።

ዩኒቨርስቲዎች ከፖለቲካ ጣልቃገብነት ተላቀው ነጻ እውቀትና ሃሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
--------------------- //------------------------
(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም) በቀጣይ ወደ ራስገዝነት የሚሸጋገሩ ዩኒቨርስቲዎች የዝግጁነት ግምገማ ውጤት በቀረበበት መድረክ ላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የከፍተኛ ትምህርት ሪፎርሙ ዋና ዓላማ ለእውነትና ለእውቀት ቁርጠኛ፣ አገራቸውን የሚወዱና የሚለውጡ ዜጎችን ማፍራት መሆኑን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻና ከፖለቲካ ጣልቃ-ገብነት ተላቀው ነጻ ሃሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት እንዲሆኑ ወደ ራስ-ገዝነት ማሸጋገር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለእውነትና ለእውቀት ቁርጠኝነት ያላቸውና አገራቸውን የሚወዱና የሚለውጡ የሰው ሃይል የሚያፈሩ እንዲሆኑ ማስቻል የሪፎርሙ መሠረት መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው እንደገለጹት ወደ ራስገዝነት የሚሸጋገሩ ተቋማት ከአክሪዲቴሽን ጋር በተያያዘ በተለይ የሀገር ውስጥ እውቀት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል።
ከውስጥ ገቢ ጋር በተያያዘም ተቋማቱ በዘላቂና ብዝሃ ገቢ ማስገኛ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BFQ2MqAiN/