Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቤቶች ምገባን የሚደግፍ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመውን የትምህርት ቤቶች ምገባ የሚደግፍን ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ፕሮጀክቱ የተጀመረወን የትምህርት ቤት ምገባ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ተማሪዎች በቂና ተመጣጣኝ ምግብ በማግኘት በትምህርታቸው ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

ለፕሮጀክቱ ስኬት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አጋር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን ገልጸው፣ ተማሪዎች በጤናማ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችሉ መሰል ፕሮጀክቶች በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንዲስፋፉ ምሳሌ ይሆናል ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ቤት ምገባ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ በሞዴልነት የሚጠቀስ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

እንዲሁም የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ ይከናወን የነበረው የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከላዊ ሥርዓት በማምጣት ትልቅ የሪፎርም ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። ይህም የተማሪዎች የምግብ ዝግጅትና ስርጭት ሂደቱን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ዘላቂ እንዲሆን እንደሚያስችል ተናግረዋል።

ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/14fY9nME2GB/
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራን የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሀላፊነት በሚገባ እንዲወጡ ተጠየቀ።
 
------------------------- //---------------------------

(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም) ብቃትን መሰረት ያደረገ መማር ማስተማርን በሚመለከት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመምህራን እየተሰጠ ይገኛል።  
 
 
ትምህርት ሚኒስቴር ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች በመምረጥና በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በማስተማር የሀገሪቱን የወደፊት የሰው ሀብት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።


እነዚህ ትምህርት ቤቶች በአካዳሚክ ብቃት፣ በሥነ-ምግባር፣ በአመራር ክህሎት እና በሀገራዊ እሴቶች የተገነባ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የተገልጸ ሲሆን፣
ይህንን ሀገራዊ ተልዕኮ በተሻለ ብቃት ለማሳካትም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት መሰረት ባደረገና የመማርና የማስተማር ሥርዓት ላይ ያተኮረ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል።


ስልጠናው በትምህርት ቤቶቹ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገሩም በላይ፣ መምህራን ተማሪዎችን የእውቀት ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ችግር ፈቺዎች፣ ፈጠራ ባለቤቶች እና ሀገራቸውን የሚያገለግሉ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘመናዊ የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን እንዲላበሱ ያስችላቸዋልም ተብሏል።
ዩኒቨርስቲዎች ከፖለቲካ ጣልቃገብነት ተላቀው ነጻ እውቀትና ሃሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
 
            --------------------- //------------------------

(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም) በቀጣይ ወደ ራስገዝነት የሚሸጋገሩ ዩኒቨርስቲዎች የዝግጁነት ግምገማ ውጤት በቀረበበት መድረክ ላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የከፍተኛ ትምህርት ሪፎርሙ ዋና ዓላማ ለእውነትና ለእውቀት ቁርጠኛ፣ አገራቸውን የሚወዱና የሚለውጡ ዜጎችን ማፍራት መሆኑን ተናግረዋል።
‎
‎የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻና ከፖለቲካ ጣልቃ-ገብነት ተላቀው ነጻ ሃሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት እንዲሆኑ ወደ ራስ-ገዝነት ማሸጋገር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለእውነትና ለእውቀት ቁርጠኝነት ያላቸውና አገራቸውን የሚወዱና የሚለውጡ የሰው ሃይል የሚያፈሩ እንዲሆኑ ማስቻል የሪፎርሙ መሠረት መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው እንደገለጹት ወደ ራስገዝነት የሚሸጋገሩ ተቋማት ከአክሪዲቴሽን ጋር በተያያዘ በተለይ የሀገር ውስጥ እውቀት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል።
‎
‎ከውስጥ ገቢ ጋር በተያያዘም ተቋማቱ በዘላቂና ብዝሃ ገቢ ማስገኛ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BFQ2MqAiN/
ትምህርት ሚኒስትሩ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀመሩ
 
-------------------------- // -----------------------------

(ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ወጪ በድሬዳዋ ከተማ የሚገነባውን የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል።

በዚሁ ጊዜ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት መንግሥት የተሻለ የትምህርት ጥራትና የላቀ የትምህርት አካባቢ ለመፍጠር በመላ ሀገሪቱ የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸውን የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ አካባቢዎች እየገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ትምህርት ቤትም ከመላው ሀገሪቱ በብቃታቸው የተመረጡ ተማሪዎችን በመቀበል የሚያስተምር ሲሆን፣ ግንባታው በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን የማስፋፋት ሥራ በቀጣይነት እንደሚቀጥል ገልጸው፣ በባህርዳር፣ አርባምንጭ እና አሶሳ ተመሳሳይ የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ለከተማዋ እድገትና ለትውልድ ግንባታ እያደረገ ላለው አስፈላጊ ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ የከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤  https://web.facebook.com/share/p/1PuiqKwBrR/
በትምህርት ዘርፉ ከተወሰዱ የሪፎርም ተግባራት ዋናውና ወሳኙ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነት ላይ እየተሰራ ያለው ሥራ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
 
---------------------- // ------------------------
 
(ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በድሬዳዋ ከተማ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።
 
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ለሕፃናት የመማር መሠረትን የሚጥል በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽነቱን ለማስፋፋት ሰፊ ሥራ እየተከናወነ ነው።
 
በተለይም በትምህርት ሪፎርሙ ማዕቀፍ ውስጥ ለሁሉም ሕፃናት ፍትሃዊና ጥራት ያለው የመማር ዕድል ለመፍጠር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ማስፋፊያ ሥራዎች ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሠራ መሆን ጠቅሰዋል።
 
ክቡር ከንቲባ ከድር ጀዋር በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በከተማው ያለውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ፍላጎት ለማሟላትና የሕፃናትን የመማር ዕድል ለማስፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18Xc4aqgiL/