የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ ከአካባቢ ልማትና ጸጋ ጋር የተያያዘ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ።
----------------------------- // -----------------------------
(ሰኔ 19/2018 ዓ.ም) የቡሌሆራና ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲዎች በማዕድንና ነዳጅ ላይ አትኩሮ ከሚሰራው የኦስትሪያው ሊዮቤን ዩኒቨርስቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የዩኒቨርስቲዎች የተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ ከአካባቢ የልማት ጸጋ ጋር የተያያዙ እንዲሆን እየተሰራ ነው።
የትኩረት መስክን ከተፈጥሮ ፀጋ ጋር ማያያዝ ሀብት፣ ጊዜና አቅምን በአግባቡ በመጠቀም ውጤታማ አንደሚያደርግም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
የቡሌሆራና የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲዎች የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነትም በመምህራን ልማትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርስቲ ኢንዲስትሪ ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያስችል ተናግረዋል ።
የቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ ከሊዮቤን ዩኒቨስቲ እና ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ስምምነት መፈራረሙን ጠቅሰው ይህም በማዕድን ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል።
የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርስቲም ከሊዮቤን ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ጋር የተፈራረመው ስምምነት ዩኒቨርስቲው በአገር ውስጥ ብዙም ባልዳበረው የነዳጅና ኤነርጂ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆን ያግዘዋል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1E2Y46YHWQ/

የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሳሰቡ።
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 በበይነ መረብና በወረቀት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል።
-------------------------- // -----------------------
በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
በተለይም በፈተና ሂደት ወቅት ፈተና ለመስረቅም ይሁን ለማሰረቅ የሚሞክሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ለፈተናው ስኬታማነት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው የፈተናው አጠቃላይ ሂደት ደህንነቱ የተጠበቀ በሰላምና በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ በተባበረ አግባብና በተቀናጀ ሁኔታ መሰራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
የዘንድሮ የ12ኛ ክል ብሄራዊ ፈተና ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል በአብዛኛው በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑና የፈተና ተቋማቱ በርከት ባለ ሁኔታ በክልል ደረጃ የተደራጁ መሆናቸው ልዩ እንደሚያርገውም ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የፈተናውን ደህንነቱን የማረጋገጥ ጉዳይ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያፈልግ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1HCE2Y1BwH/

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
**************
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
አገልግሎቱ እንዳመለከተው፣ ፈተናው በበይነ መረብ (ኦንላይን) መሰጠት የጀመረ ሲሆን፣ ተፈታኞች በስድስት ዙሮች ተከፋፍለው በተሳካ ሁኔታ ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ ብሏል።
ሆኖም የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የኮምፒውተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናውን በአራት ዙሮች በወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበይነ መረብ ለመፈተን ለተመዘገቡ 14 ሺህ 755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።
በሌላ በኩል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15 ሺህ 325 የክልሉ ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
እነዚህ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መቐለ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት፣ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን ገለጻ (ኦሬንቴሽን) በመከታተል ፈተናቸውን መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጨምሮ ገልጿል።

የቡኢ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በፍጥነት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ።
----------------------- // ------------------------
(ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም) የቡኢ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል በሚያስችል ሁኔታ በፍጥነትና በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት የተመራ ልዑክ የትምህርት ቤቱ የግንባታ ሥራ የደረሰበትን ወቅታዊ ደረጃ በቦታው በመገኘት ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የሕንጻዎቹ የግንባታ ሂደት በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን፣ ትምህርት ቤቱ በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆን ከሥራ ተቋራጩ ጋር በቀሪ ሥራዎችና በማጠናቀቂያ ሂደት ላይ ዝርዝር ውይይት ተካሂዷል።
በተጨማሪም ከግንባታው ጎን ለጎን ትምህርት ቤቱን ለማስጀመር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ምልመላና ምደባ ጨምሮ ሁሉንም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከመስከረም 2019 ዓ.ም በፊት ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በውይይቱ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፣ የቡኢ ከተማ ከንቲባ፣ የሥራ ተቋራጩ ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹም ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅና ትምህርት ቤቱ በወቅቱ ተማሪዎችን እንዲቀበል የየድርሻቸውን ኃላፊነት በሙሉ እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BkueAVRCc/

ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር በነባርና አዲስ ትምህርት በሚጀመርባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ርዕሳነ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም መፈርቱን የምታሟሉ በሙሉ በበየነ መረብ ባልችሁበት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገልጽን
በመምህርነት መመዝገብ ለምትፈልጉ በ https://sbs.moe.gov.et/career/teacher
በርዕሰ መመህርነት ለመመዝገብ የምትፈልጉ https://sbs.moe.gov.et/directors መጠቀም የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።