የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ።
--------------------------- // -----------------------------
(ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እያካሄዱ ከሚገኘው የምክክር መድረክ ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ለአካባቢ ጥበቃና ዘላቂ ልማት ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል።
መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ COP 32 ልዩ ተልዕኮ ለትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በቢሾፍቱ የፍጥነት መንገድ በተሰጠው 6.2 ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ ተከላው ተከናውኗል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ለ8ኛ ዙር በምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የትምህርት ዘርፉም የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
ልዩ ተልዕኮ በተሰጠው የCOP 32 የአረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀምበር እንደ ሀገር ለሚካሄደው መርሃ ግብር ችግኝ የማዘጋጀት፣ ጉድጓድ የመቆፈር እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰዋል።
እንዲሁም ለተከላ የተዘጋጁት ችግኞች ለአካባቢ ጥበቃ ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ በተጨማሪ፣ የፍራፍሬና ሌሎች ተጠቃሚ ችግኞችን በማካተት ለአርሶ አደሮች የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1AfcDPFCoD/

እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መላክ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።
-------------------------- // ------------------------
(ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም) የ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ የትምህርት ንቅናቄ ሰነድ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ ላይ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለች እሸቴ እንደገለጹት፣ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ መሠረት ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ዜጎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረግ የመንግሥትና የማኅበረሰቡ የጋራ ኃላፊነት ነው።
በመሆኑም ሕብረተሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ እንዲሁም በተለያዩ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የነበሩ ተማሪዎች እንደገና ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የትምህርት ዘርፍ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ በማድረግ ረገድ የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/19JdkqUhkP/

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ለትምህርት ጥራትና ውጤታማነት መጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል
7ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (ESDP VII) ረቂቅ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጎበታል።
--------------------- // --------------------
(ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም) በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ በስትራቴጂክ ጉዳዮች የቀረበው 7ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (ESDP VII 2026/27 to 2030/31) ረቂቅ ዕቅድ፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ውጤታማነትን ማጠናከር ዋና ትኩረት እንደሚሆን አመላክቷል።
በረቂቅ ዕቅዱ መሠረት፣ የትምህርት ጥራትንና ተገቢነትን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል የተጀመሩ ሥራዎችን በአዳዲስ አሠራሮች ማጠናከር፣ የትምህርትን ውጤት በተጨባጭ መለካት እና በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል።
ፕሮግራሙ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በውጤታማነት መተግበር፣ ምዘናን በብቃት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ፣ የተማሪዎችን የመማር ውጤት ማሻሻል እንዲሁም በቋንቋ፣ በሂሳብ እና በሳይንስ ትምህርቶች ያላቸውን ብቃት ማሳደግን እንደ ዋና ተግባራት አካቷል።
በተጨማሪም የዲጂታል ትምህርትን ማስፋፋት፣ የብሔራዊ ፈተናዎችን ማዘመን፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና (TVET) እና በከፍተኛ ትምህርት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር፣ የመምህራንን ሙያዊ ብቃትና ማበረታቻ ማሻሻል፣ እንዲሁም የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ማጠናከር በዕቅዱ ውስጥ ተካትተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/14iiD7gsMmP/

የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ።
------------------------ // ---------------------
(ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች "ተስፋን እንተክላለን" በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ አካባቢ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በዛሬው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ ጠቃሚ የሆኑ የአቮካዶ፣ የብርቱካን፣ የሮማን እና የዘይቱና የመሳሠሉት ችግኞች ተተክለዋል።
በመርሃ ግብሩ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ እና የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት በቦታው በመገኘት ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በዚሁ ወቅት ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ለአገራችን ሁለንተናዊ ልማትና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች ችግኝ በመትከል አርአያነታቸውን በተግባር ማሳየታቸውን በማድነቅ ይህንን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ችግኝ መትከል ከራስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የመልካም አካባቢ ውርስ ማስቀመጥ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከራስ አልፎ ለትውልድና ለሀገር ማሰብ የሰው ልጅ ትልቅነትን የሚያሳይ መለኪያ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በቢሾፍቱ አካባቢ በተካሄደው የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት ችግኞች ከምግብ ምንጭነታቸው ባሻገር ለደን ልማት፣ ለአፈር ለምነት ጥበቃ እና ለአካባቢ ሥነ-ምህዳር መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ተገልጿል።

የሮተሪ ኢንተራክት ኢትዮጵያ ክለብ አባላት አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
-------------------- // ------------------------
(ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ታምሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እጥረት ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲቀሩና እንዲያቋርጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
በትምህርት ቤቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች መኖር ሴት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው በቆይታቸው ሳይጨነቁና ሳይሳቀቁ በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
በአዲሱ የትምህርት አዋጅም በትምህርት ቤት ውስጥ እድሜያቸው የደረሱ ሴት ልጆች ሁሉ የንጽህና መጠበቂያዎችን ማግኘት እንዲችሉ በህግ መደንገጉንም ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ጠቁመዋል።
በመንግስት አቅም ብቻ አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎችን የንጽህና መጠበቂያ አቅርቦት ችግሮችን ማሟላት ስለማይቻል የህብረተሰቡ ተሳትፎ በተለይም እንደ ሮተሪ ኢንተራክት ክለብ ያሉ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ተነሳስተው የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኢንተራክት ኢትዮጵያ ክለብ አባላት ላደረጉት አርአያነት ያለው ተግባር አመስግነው ድጋፉ የተቸገሩ ሴት ተማሪዎች ጋር በትክክል እንደሚደርስና በትምህርታቸውም ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/197ra4Lvbx/