Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ለትምህርት ጥራትና ውጤታማነት መጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

7ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (ESDP VII) ረቂቅ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጎበታል።

--------------------- // --------------------

(ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም) በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ በስትራቴጂክ ጉዳዮች የቀረበው 7ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (ESDP VII 2026/27 to 2030/31) ረቂቅ ዕቅድ፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ውጤታማነትን ማጠናከር ዋና ትኩረት እንደሚሆን አመላክቷል።


በረቂቅ ዕቅዱ መሠረት፣ የትምህርት ጥራትንና ተገቢነትን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል የተጀመሩ ሥራዎችን በአዳዲስ አሠራሮች ማጠናከር፣ የትምህርትን ውጤት በተጨባጭ መለካት እና በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል።


ፕሮግራሙ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በውጤታማነት መተግበር፣ ምዘናን በብቃት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ፣ የተማሪዎችን የመማር ውጤት ማሻሻል እንዲሁም በቋንቋ፣ በሂሳብ እና በሳይንስ ትምህርቶች ያላቸውን ብቃት ማሳደግን እንደ ዋና ተግባራት አካቷል።


በተጨማሪም የዲጂታል ትምህርትን ማስፋፋት፣ የብሔራዊ ፈተናዎችን ማዘመን፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና (TVET) እና በከፍተኛ ትምህርት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር፣ የመምህራንን ሙያዊ ብቃትና ማበረታቻ ማሻሻል፣ እንዲሁም የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ማጠናከር በዕቅዱ ውስጥ ተካትተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/14iiD7gsMmP/
የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ።

------------------------ // ---------------------

(ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች "ተስፋን እንተክላለን" በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ አካባቢ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሂደዋል።


በዛሬው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ ጠቃሚ የሆኑ የአቮካዶ፣ የብርቱካን፣ የሮማን እና የዘይቱና የመሳሠሉት ችግኞች ተተክለዋል።

በመርሃ ግብሩ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ እና የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት በቦታው በመገኘት ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።


በዚሁ ወቅት ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ለአገራችን ሁለንተናዊ ልማትና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች ችግኝ በመትከል አርአያነታቸውን በተግባር ማሳየታቸውን በማድነቅ ይህንን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።


ችግኝ መትከል ከራስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የመልካም አካባቢ ውርስ ማስቀመጥ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከራስ አልፎ ለትውልድና ለሀገር ማሰብ የሰው ልጅ ትልቅነትን የሚያሳይ መለኪያ መሆኑንም አስገንዝበዋል።


በቢሾፍቱ አካባቢ በተካሄደው የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት ችግኞች ከምግብ ምንጭነታቸው ባሻገር ለደን ልማት፣ ለአፈር ለምነት ጥበቃ እና ለአካባቢ ሥነ-ምህዳር መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ተገልጿል።
የሮተሪ ኢንተራክት ኢትዮጵያ ክለብ አባላት አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

-------------------- // ------------------------

‎
‎(ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ታምሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እጥረት ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲቀሩና እንዲያቋርጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።


በትምህርት ቤቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች መኖር ሴት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው በቆይታቸው ሳይጨነቁና ሳይሳቀቁ በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

‎
‎በአዲሱ የትምህርት አዋጅም በትምህርት ቤት ውስጥ እድሜያቸው የደረሱ ሴት ልጆች ሁሉ የንጽህና መጠበቂያዎችን ማግኘት እንዲችሉ በህግ መደንገጉንም ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ጠቁመዋል።
‎
‎በመንግስት አቅም ብቻ አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎችን የንጽህና መጠበቂያ አቅርቦት ችግሮችን ማሟላት ስለማይቻል የህብረተሰቡ ተሳትፎ በተለይም እንደ ሮተሪ ኢንተራክት ክለብ ያሉ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ተነሳስተው የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
‎
‎የኢንተራክት ኢትዮጵያ ክለብ አባላት ላደረጉት አርአያነት ያለው ተግባር አመስግነው ድጋፉ የተቸገሩ ሴት ተማሪዎች ጋር በትክክል እንደሚደርስና በትምህርታቸውም ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/197ra4Lvbx/
ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማስታወቂያ
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን  ለማስተማር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል። በዚህም ለ10 ክፍል ተመዝጋቢዎች የተጠቀሰው 95% ወደ 85 % ዝቅ ያለ መሆኑን አውቃችሁ 85% እና በላይ ያላችሁ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መመዝገብ  የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ለመመዝገን ይህንን ሊንክ ጥጫኑ፤ https://sbs.moe.gov.et/apply
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በታንዛኒያ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ብድር ቦርድ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑካን ቡድን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግሩ።

‎ -------------------------- // -----------------------

‎
‎(ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም) በሁለቱን ሀገራት መካከል በዘርፉ የልምድ ልውውጥና የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።

‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በታንዛኒያ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ብድር ቦርድ ዋና ዳይሬክተር በዶ/ር ቢል ኪዊአ የተመራ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

‎
‎ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ብቃትና አቅም በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

‎
‎በኢትዮጵያ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች የሚያገኙትን የትምህርትና የአገልግሎት ወጪ የሚካፈሉበት የወጪ መጋራት (Cost Sharing) ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1D4w2mcc5k/