የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ።
------------------------ // ---------------------
(ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች "ተስፋን እንተክላለን" በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ አካባቢ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በዛሬው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ ጠቃሚ የሆኑ የአቮካዶ፣ የብርቱካን፣ የሮማን እና የዘይቱና የመሳሠሉት ችግኞች ተተክለዋል።
በመርሃ ግብሩ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ እና የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት በቦታው በመገኘት ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በዚሁ ወቅት ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ለአገራችን ሁለንተናዊ ልማትና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች ችግኝ በመትከል አርአያነታቸውን በተግባር ማሳየታቸውን በማድነቅ ይህንን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ችግኝ መትከል ከራስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የመልካም አካባቢ ውርስ ማስቀመጥ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከራስ አልፎ ለትውልድና ለሀገር ማሰብ የሰው ልጅ ትልቅነትን የሚያሳይ መለኪያ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በቢሾፍቱ አካባቢ በተካሄደው የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት ችግኞች ከምግብ ምንጭነታቸው ባሻገር ለደን ልማት፣ ለአፈር ለምነት ጥበቃ እና ለአካባቢ ሥነ-ምህዳር መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ተገልጿል።

የሮተሪ ኢንተራክት ኢትዮጵያ ክለብ አባላት አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
-------------------- // ------------------------
(ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ታምሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እጥረት ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲቀሩና እንዲያቋርጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
በትምህርት ቤቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች መኖር ሴት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው በቆይታቸው ሳይጨነቁና ሳይሳቀቁ በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
በአዲሱ የትምህርት አዋጅም በትምህርት ቤት ውስጥ እድሜያቸው የደረሱ ሴት ልጆች ሁሉ የንጽህና መጠበቂያዎችን ማግኘት እንዲችሉ በህግ መደንገጉንም ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ጠቁመዋል።
በመንግስት አቅም ብቻ አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎችን የንጽህና መጠበቂያ አቅርቦት ችግሮችን ማሟላት ስለማይቻል የህብረተሰቡ ተሳትፎ በተለይም እንደ ሮተሪ ኢንተራክት ክለብ ያሉ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ተነሳስተው የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኢንተራክት ኢትዮጵያ ክለብ አባላት ላደረጉት አርአያነት ያለው ተግባር አመስግነው ድጋፉ የተቸገሩ ሴት ተማሪዎች ጋር በትክክል እንደሚደርስና በትምህርታቸውም ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችል ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/197ra4Lvbx/

ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ለፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስተማር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል። በዚህም ለ10 ክፍል ተመዝጋቢዎች የተጠቀሰው 95% ወደ 85 % ዝቅ ያለ መሆኑን አውቃችሁ 85% እና በላይ ያላችሁ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ለመመዝገን ይህንን ሊንክ ጥጫኑ፤ https://sbs.moe.gov.et/apply

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በታንዛኒያ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ብድር ቦርድ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑካን ቡድን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግሩ።
-------------------------- // -----------------------
(ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም) በሁለቱን ሀገራት መካከል በዘርፉ የልምድ ልውውጥና የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በታንዛኒያ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ብድር ቦርድ ዋና ዳይሬክተር በዶ/ር ቢል ኪዊአ የተመራ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ብቃትና አቅም በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።
በኢትዮጵያ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች የሚያገኙትን የትምህርትና የአገልግሎት ወጪ የሚካፈሉበት የወጪ መጋራት (Cost Sharing) ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1D4w2mcc5k/

የመምህራን ስልጠና እና የተግባር ተኮር ትምህርት ማስተማሪያ ሞጁል ዝግጅት ጥራትን እና ወጥነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።
--------------------------------- // -------------------------------
(ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከፊንላንድ መንግስት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የመምህራን ትምህርት ስልጠና እና የተግባር ተኮር ትምህርት ማስተማሪያ ሞጁል ዝግጅት ማዕቀፍ ላይ ዓውደ ጥናት ተካሂዷል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍን በመወከል በመድረኩ የተገኙት የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዬሴፍ አበራ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ስራዎች አካታችነትና ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሚዘጋጁት የመምህራን ትምህርት ማሠልጠኛ ሞጁሎች የመምህራንን ሙያዊ አቅም በከፍተኛ ደረጃ የመገንባት እና በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ የሚታዩ የጥራት ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆኑንም ገልጸዋል።
ማሪያ ማቲር የ”Teacher Education for Inclusion and Quality (TEFIQ)” ፕሮጀክት በኢትዬጵያ አስተባባሪ በበኩላቸው የመምህራን ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ያለውን የሞጁልና ሌሎች መሰል የትምህርት ፓሊሲ ማስፈፀሚያ ዶክመንቶች ዝግጅት ወጥነትና ጥራትን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የዘርፉ ባለሙያዎች ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/17QVX6g282/