Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ማስታወቂያ
በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለመቀጠር የተመዘገባችሁ እና ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ለተካተተ መምህራን የጽሁፍ ፈተናው ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ፈተናው በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚቀርባችሁን በመምረጥ በአካል በመገኘት እንድትፈተኑ እናሳውቃለን፦
ፈተናው የሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች፤
1. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ
7. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
2. ወሎ ዩኒቨርሲቲ
5. ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ
8. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
3. ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
6. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
9. መቀሌ ዩኒቨርሲቲ
   
 ማሳሰቢያ፣


1.   ለውድድር የተመዘገባችሁበትን መለያ ቁጥር (Reference Number) በመጠቀም የፈተና መግቢያ መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username & Password) ማግኘት ትችላላችሁ፤
2.   በተጨማሪም መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username & Password) ለፈተና በምትመጡበት ቀን በየዩኒቨርሲቲዎቹ ከሚመደቡ የፈተና አስተባባሪዎች ዘንድ ማግኘት ይቻላል፤
3.   ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ።

በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ ተመዝግቧል።

----------------------------- // -------------------------------
‎
‎(ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች 50% እና በላይ ወጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።

‎
‎ባለፈው ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 8.9 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የማለፊያውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ20 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

‎
‎በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆኑንም ተናግረዋል።

‎
‎በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በወንድ ፤ 583.03 በሴት ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 576.25 በሴት 569.17 ሆኖ መመዝገቡን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1EmG2EkeY7/