የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ።
በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ ተመዝግቧል።
----------------------------- // -------------------------------
(ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች 50% እና በላይ ወጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።
ባለፈው ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 8.9 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የማለፊያውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ20 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በወንድ ፤ 583.03 በሴት ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 576.25 በሴት 569.17 ሆኖ መመዝገቡን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1EmG2EkeY7/

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት
ማዕከላት(CEED) ውስጥ እየታዩ ያሉ ጅምር ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተገለጸ።
----------------------- // -----------------------
(ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመተግበር ላይ የሚገኘው የሥራ ፈጣሪነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማዕከል (CEED) ፕሮጀክት ተማሪዎችና መምህራን በራሳቸው የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና የሥራ ፈጣሪነት ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማዕከል አስተባባሪዎች ጋር በመሆን የማዕከላቱን አመታዊ የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።
ፕሮጀክቱ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አዲስ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕረነርሺፕ ባህል እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጄና በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት አመላክተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘይ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/19FPRieyiq/

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈጸሙ የሙስና እና የስነ-ምግባር ግድፈቶችን ተጠያቂነትን በማስፈንና የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርስቲ የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
------------------------ // -------------------------
(ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈጸሙ የሙስና እና የስነ-ምግባር ግደፈቶችን ለመከላከል ተጠያቂነትንና የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ተጠያቂነትንና የአሰራር ስርዓትን ከመገንባት ባሻገር በመዋቅር ፣ በአሰራርና በሰው ሃይል ስምሪት ነገሮችን መለወጥና ማስተካከል እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከገንዘብና ንብረት ሙስና ውጪ የተማሪ ምደባን ጨምሮ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ ቀድሞ ያልነበሩ አዳዲስ የሙስና ስጋቶች መኖራቸውንም ክቡር አቶ ኮራ ጠቁመዋል።
በመሆኑም የዩኒቨርስቲ የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚዎች በምሉዕነት የህዝብና የጋራ ጥቅሞችን በማስቀደም የትምህርት ጥራት ጸር የሆነውን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በጽናት መታገል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BqyZxFCk6/