በሀገር አቀፍ ደረጃ ፍትሃዊና ወጥነት ያለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የደረጃ እድገት ሥርዓት ለመገንባት እየተሠራ ነው።
---------------------- // --------------------------
(ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ከሸያሾኔ ተቋም ጋር በመተባበር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ሥራተኞች የደረጃ እድገት መመሪያን ለማሻሻል የሚያስችሉ ግብዓቶች የሚሰበሰቡበት የምክክር መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ ፍትሃዊና ወጥነት ያለው የመምህራን የደረጃ እድገት ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
መምህራን መስፈርቱን አሟልተው እድገት ሲጠይቁ ያለምንም አድሎና እንግልት በወቅቱ ማግኘት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ዶ/ር ኤባ የመመሪያው መሻሻል ዋና ዓላማ አፈጻጸሙን ወጥ ማድረግ፣ ግልጽነት መፍጠር እና መመሪያውን ዘላቂና ተራማጅ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰራዊት ሀንዲሶ ከሁለት ዓመት በፊት በሥራ ላይ የነበረው የቀድሞ መመሪያ 12 ሥርዓታዊና በርካታ የአተገባበር ችግሮች የነበሩበት፣ እንዲሁም ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጠ እንደነበር አስታውሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1DRF9hbYNm/

ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተማዘገባችሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ተማሪዎች በሙሉ፤
ለፈተና መስጫ ማዕከልነት የተመረጡት፤
Ø አዲስ አበባ ዩኒቨርቲ (6 ኪሎ ካምፓስ)
Ø የመነን አዳሪ ት/ቤት
Ø ሚኒኒክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለሆኑ ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ዛሬ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ከ9:00 ጀምሮ በእነዚህ የፈተና መስጫ ማዕከላት ተገኝታችሁ የሙከራ ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
Ø የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።
Ø ማስፈንጠሪያ (Link) https://student.ethernet.edu.et/
ማሳሰቢያ፡-
v የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።
የትምህርት ሚኒስቴር

ዩኒቨርስቲዎች ሀገርን የሚያሻግሩ የእውቀት ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ገለጹ፤
---------------------- // ---------------------
(ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም) ዩኒቨርስቲዎች ሀገርን የሚያሻግሩ የእውቀት ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ አስገነዘቡ።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ በንግግራቸው፤ ዩኒቨርስቲዎች የሙያና የስነ-ምግባር እሴቶች የሚገነቡባቸው የአካዳሚክና የምርምር ተቋማት መሆናቸውን ገልጸው የህብረተሰቡ የሞራልና የእውቀት መሪዎች በመሆናቸው፣ የሙያ ስነ-ምግባርንና የሞራል እሴቶችን በመላበስ ማህበረሰቡን በእውቀትና በሙያ ሊደግፉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አክለውም፤ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስብጥር ብዝሃነትን ባካተተ፣ መተዋወቅን፣ መከባበርን፣ መቻቻልንና ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በዩኒቨርስቲዎች ከተማሪዎች ምደባና ዝውውር ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ስርዓት እንደሚዘረጋ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ከበጀት አጠቃቀም ረገድም ተቋማቱ የተመደበላቸውን በጀት ለታቀደለት ዓላማ ብቻ በቁጠባና በተጠያቂነት መንፈስ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://web.facebook.com/share/p/1EPYjkE9WK/

የዩኒቨርስቲ ምደባ በመጠባበቅ ላይ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርሲቲ እና የባንድ ምርጫችሁን፣ እንዲሁም የልዩ ድጋፍ ማመልከቻ ለማቅረብ ከታች ያለውን ቪዲዮ መመሪያ በመከታተል መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ በተለያየ ምክንያት የመግቢያ ፈተና ላልተፈተናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣
የትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመዝግበው ለፈተና የተመረጡ ተማሪዎችን መፈተኑ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ለፈተና ተመርጣችሁ በተለያየ ምክንያት ፈተና ያልተፈተናችሁ ተማሪዎች ጷጉሜ 02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፈተና መስጫ ማዕከል በመገኘት መፈተን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፤ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በድጋሜ መፈተን የማይቻል መሆን እንገልጻለን።

ለ2019 ዓ/ም አዲስ ለተቋቋሙና ለነባር የፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ሙያ ተቀጥረው ለማገልገል የፅሁፍ ፈተና በመውሰድ የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ለቃለ መጠይቅ ለተመረጣችሁ መምህራን በሙሉ፣
ቃለ መጠይቁ የሚካሄደው ጳጉሜ 3/2018 ዓ. ም ማክሰኞ በኦንላይን የሚካሄደ ሲሆን በምዝገባ ወቅት በሰጣችሁት ስልክ ቁጥር ዋትስአፕ ላይ በመግባት እንዴት ኢንተር ቪውን በሞባይልና በላፕቶብ ማድረግ እንደምትችሉ የተጫነውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን!