የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች «በህብር እንደጋገፍ፤ አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንቀበል» በሚል መሪ ቃል የህብር ቀንን አከበሩ።
-------------------- // --------------------
(ጳግሜ 4/2018) የትምህርት ሚኒስቴር ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞቹ ለአዲስ አመት በዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ አደረገ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት በበዓላት መደጋገፍና መተጋገዝ የቆየና ውብ የሆነ የኢትዮጵያውያን እሴት መሆኑን አብራርተዋል።
አክለውም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በተጠበቀው ልክ አድጎና ተጠናክሮ እያንዳንዱ ዜጋ ሰርቶ ራሱንና ቤተሰቡን በሙሉ አቅም መደጎም የሚችልበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ እንዲህ ያሉ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህሎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የህብር ቀን አከባበር ቴክኒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ እንደገለጹት በትምህርት ዘርፉ ስር ባሉ ልዩ ልዩ የትምህርት ተቋማት የበጎ ፈቃድና የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/14sth2kRq9P/

ማስታወቂያ
ለ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ፤
በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት መለያ ቁጥራችሁንና የይለፍ ቃል በማስገባት ማለፍ ወይም አለማለፋችሁን ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ምርጫችሁን ያላስገባችሁ ተማሪዎች በ https://student.ethernet.edu.et ድህረ ገጽ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም ምርጫችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ትምህርት በሚጀምርባቸውና እና ለነባር የፌደራል አዳሪ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንን ለመልመል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የጽሁፍ እና የቃል ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ መምህራን ዝርዝራችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን። ያለፋችሁ መምህራን መስከረም 5/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የትምህርት ቤት ምደባ እና ስልጠና የሚሰጣችሁ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በተጠቀሰው ቀን በትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፦ በዚህ ስልጠና እና ኦረንቴሽን የማይገኝ ማንኛውም መምህር ከምደባው የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በተጨማሪም መስከረም 7 እና 8/2019 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ዩኒቨርሲቲዎች)አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

📢 ማስታወቂያ
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነገ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ይጀምራል!
ውድ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና መላው የትምህርት ማኅበረሰብ፤ እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓመት እና የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ!
በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመላ ሀገሪቱ ነገ፣ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም፣ በይፋ ይጀምራል።
በዚህም ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ እናንተን ለመቀበልና የመማር–ማስተማር ሂደቱን በተቀመጠው የትምህርት ካሌንደር መሠረት ለመጀመር እየተጠባበቁ ይገኛል።
ስለሆነም፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና ሁላችሁም የሚመለከታችሁ አካላት ለትምህርት የደረሱ ልጆችን አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓት በማሟላት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ በማድረግ፣ የድርሻችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
🌟 መልካም የትምህርት ዘመን!
ትምህርት ሚኒስቴር