Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ትምህርት በሚጀምርባቸውና እና ለነባር የፌደራል አዳሪ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንን ለመልመል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የጽሁፍ እና የቃል ፈተና ወስዳችሁ   ያለፋችሁ መምህራን ዝርዝራችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን። ያለፋችሁ መምህራን መስከረም 5/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የትምህርት ቤት ምደባ እና ስልጠና የሚሰጣችሁ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በተጠቀሰው ቀን በትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
 
ማሳሰቢያ፦ በዚህ ስልጠና እና ኦረንቴሽን የማይገኝ ማንኛውም መምህር ከምደባው የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 
በተጨማሪም መስከረም 7 እና 8/2019 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ዩኒቨርሲቲዎች)አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
📢 ማስታወቂያ
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነገ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ይጀምራል!
ውድ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና መላው የትምህርት ማኅበረሰብ፤ እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓመት እና የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ!

በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመላ ሀገሪቱ ነገ፣ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም፣ በይፋ ይጀምራል።

በዚህም ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ እናንተን ለመቀበልና የመማር–ማስተማር ሂደቱን በተቀመጠው የትምህርት ካሌንደር መሠረት ለመጀመር እየተጠባበቁ ይገኛል።

ስለሆነም፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና ሁላችሁም የሚመለከታችሁ አካላት ለትምህርት የደረሱ ልጆችን  አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓት በማሟላት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ በማድረግ፣ የድርሻችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

🌟 መልካም የትምህርት ዘመን!
ትምህርት ሚኒስቴር
2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች የመንግስት ኒቨርስቲዎች እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፤ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎችን አነጋግረዋል፡፡
………………………………….. // …………………………….

‎(መስከረም 04/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በ2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቁባቸው ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

‎
‎ክቡር ሚኒስትሩ እንደገለጹት ጦርነትና ግጭት ሸሽተው ከትግራይ የወጡ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባቸው ከቻሉ ከትግራይ ወጥተው አሊያም ባሉበት በኦንላይ ለመማር የሚችሉበት ቦታ ላይ እንደሚመዘገቡና ትምህርትታቸውን መማር እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

‎
‎ተማሪዎቹን ምዝገባ ለማካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር በበይነ መረብ የምዝገባ ስርዓት ማዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትሩ ሁሉም በትግራይ ክልል ባሉ አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ በሚደረገው የኦንላይን መተግበሪያ ፕላት ፎርም በመሙላት እንዲመዘገቡ አሳውቀዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BgiGPjwXJ/
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም መስክ የወደፊቱ አገር መሪዎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ ።

------------------------ // -------------------------

‎
‎(መስከረም 05/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ ከተመደቡ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች መምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት
‎ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም በኩል የወደፊቱ የአገር መሪ የሚሆኑ ዜጎች የሚፈልቁባቸው ተቋማት ይሆናሉ ብለዋል።

‎
‎ትምህርት ቤቶቹ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ፣ በሳይንስ፣ በፖለቲካ ፣በፍልስፍና በሌሎችም የሚገነቡ አገር ወዳድ ዜጎች መፍለቂያዎች እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

‎
‎አያይዘውም ለሁሉም እኩል የሚያስቡና ሁሉንም እኩል መምራትና ማገልገል የሚችሉና አገርን ከቅርቃርና ከችግር ማውጣት የሚችሉ ዜጎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።

‎
‎ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የሚማሩባቸውና ከሁሉም ቦታ የተውጣጡ መምህራንና በችሎታ ተመርጠው የሚያስተምሩባቸው ተቋማት መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1Efqvo52qb/
በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!
‎
‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።

‎
‎ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።

‎
‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።

‎
‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያና ስሎቫኪያ በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
---------------------- // -------------------------

(መስከረም 06/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስሎቫኪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር በኢትዮጵያ ራስቲስላቭ ክሪዛንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት መካከል በትምህርቱ ዘርፍ ሊኖር ስለሚችለው ትብብር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ ከስሎቫኪያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸው፣ በሀገሪቱ እየተካሄዱ ስላሉ የትምህርት ሪፎርም ሥራዎች ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።

በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት መስክ በመለየት እንዲደራጁ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ አስተዳደራዊ ነፃነት እንዲኖራቸው ራስ ገዝ በሆነ መልኩ እንዲደራጁ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

የትምህርት ሪፎርሙ የበለጠ ውጤታማና ዘላቂ ውጤት እንዲያመጣ የተለያዩ የድጋፍና የትብብር አማራጮች እንደሚያስፈልጉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአዲስ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በመገኘቷ ከዚህ ጋር በተያያዙ አዳዲስና ተፈላጊ የትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት እንደምትፈልግ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1HF5jLJ5fu/