ኢትዮጵያና ስሎቫኪያ በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
---------------------- // -------------------------
(መስከረም 06/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስሎቫኪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር በኢትዮጵያ ራስቲስላቭ ክሪዛንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት መካከል በትምህርቱ ዘርፍ ሊኖር ስለሚችለው ትብብር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ ከስሎቫኪያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸው፣ በሀገሪቱ እየተካሄዱ ስላሉ የትምህርት ሪፎርም ሥራዎች ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።
በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት መስክ በመለየት እንዲደራጁ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ አስተዳደራዊ ነፃነት እንዲኖራቸው ራስ ገዝ በሆነ መልኩ እንዲደራጁ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።
የትምህርት ሪፎርሙ የበለጠ ውጤታማና ዘላቂ ውጤት እንዲያመጣ የተለያዩ የድጋፍና የትብብር አማራጮች እንደሚያስፈልጉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአዲስ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በመገኘቷ ከዚህ ጋር በተያያዙ አዳዲስና ተፈላጊ የትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት እንደምትፈልግ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1HF5jLJ5fu/

ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል
በትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል።
ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል።
1. የምደባው ዋና መስፈርቶች
1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም
የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል።
1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት
በዩኒቨርሲቲዎቻችን ብዝሃነትን ለማጠናከር እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦
• 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤
• 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። ሙሉ መረጃውን ለየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com

በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ና ነባር ተማሪዎች በሙሉ
በትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የትምህርት ሂደታችሁ እንዳይስተጓጎልና ደህንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል፣ በጠየቃችሁት መሰርት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መምጣት የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እየገለጽን በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የሚገለፅላቹህ ሲሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
በተለያየ ምክንያት ትግራይ ባሉት ዩኒቨርስቲዎች መቀጠል የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገርን ስለሆነ በትእግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።
የትምህርት ሚኒስቴር

በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።
የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ትውልድ ለመቅረጽ በትምህርት ዘርፉ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ነው፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
-------------------------- // -------------------------
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ ብቁ፣ በቴክኖሎጂ የዳበረ፣ አገር ወዳድ እና ከግል ጥቅም ይልቅ ለጋራ ጥቅም የሚያስብ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ የትምህርት ስርዓት አተገባበርን ባለፉት ሦስት ዓመታት ተኩል ውስጥ በትኩረት ስትተገብር ቆይታለች።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ አዳዲስ የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያዎችን ከመተግበር ጀምሮ፣ የብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን በማጥበቅ የኩረጃን ልማድ ከመከላከል አንጻር ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት 3 ዓመታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰበሰበ 146 ቢሊዮን ብር ወጪ ከ17 ሺህ በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ከ36 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነባር ትምህርት ቤቶችም እድሳት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ከነበረበት 4 ሺህ ወደ 36 ሺህ ከፍ ሊል ችሏል።
ከትምህርት መሣሪያዎችና ከአቅም ግንባታ አንጻርም ከተካሄደው የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ ከ45 ሚሊዮን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መጻሕፍት ታትመው ለተማሪዎች የተዳረሱ ሲሆን፣ ከ120 ሺህ እስከ 130 ሺህ የሚጠጉ መምህራንም በዘመናዊ የሥልጠና አሰጣጥ ዘዴዎች አቅማቸውን የሚያሳድግ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1DsufQdXUL/

ለ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
በ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች፣ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ስማችሁንና ሪፈረንስ ቁጥራችሁን በማስገባት እስከ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ ፦ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው በተጠባባቂነት ከተያዙ መካከል የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን እየገለጽን ምደባ የሚካሄደው ክፍት ቦታዎች ባሏቸው ት/ቤቶች እንደሚሆን እናሳውቃለን።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ትኩረት መሰጠቱ ገለጸ፤
በክልሉ የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።
--------------------------- // ------------------------------
(መስከረም 11/2019 ዓ.ም) የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለጹት በ2019 በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያካሄዱ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በባለፈው የትምህርት ዘመን በክልሉ በትምህርት መሠረተ ልማት ማሻሻል ፣ በመምህራን አቅም ግንባታ፣ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል
በተለይም በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ በክልሉ ከ4.4 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል ።
ከሥርዓተ ትምህርት ፣ ከግብዓት ማሟላት ፣ ከተማሪ መጽሀፍት ሥርጭት እንዲሁም የፈተና እና ምዘና ስርዓቱን ከማጠናከር አንጻርም ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውል ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BxFBirzav/

በኢትዮጵያ እና ሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለውን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
…………………………………………. // ………………………………..
(መስከረም 11/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ከሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን የትምህርት፣ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ልውውጥ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የምታደርገውን ሪፎርም ለማስቀጠል ከቀጣናዊ እና አህጉራዊ ትምህርት ተቋማት ጋር የሚደረጉ የጋራ ትብብሮች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች ለሁለቱ ሀገራት ተመራማሪዎች እና ተማሪዎችያለውን የልምድ ልውውጥ ለማሳደግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
አክለውም አሁን የተጀመረው የግንኙነት ፍላጎት ወደ ተግባር ለማውረድ በቀጣይ የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም ፍላጎት ያለ መሆኑን አመላክተዋል።
የሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አስፈጻሚዎች በበኩላቸው ከኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እንደሚፈልጉ እና በተለይም በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም የምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያላችው መሆኑን ገልጸዋል።

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በማለፍ በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፤
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና በመውሰድ ያለፋችሁ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ የመግቢያ ቀን መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።
ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው፤
1. ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤ ለምሳሌ፡- ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ ወዘተ፣
2. ለመኝታ አገልግሎት የሚያስፈልጉ አንሶላና ብርድ ልብስ፣
3. እስካሁን ሲማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት የተሰጣቸውን መሸኛና የትምህርት ውጤታቸውን የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ይዘው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፤
4. ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ከደረሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን ዩኒፎርም በራሳቸው ወጪ የሚያስዘጋጁ በመሆኑ፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ትምህርት ሚኒስቴር

በትምህርት ዘርፍ የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና ፍትሐዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ።
--------------------------//------------------------
(መስከረም 14/2019 ዓ.ም) በትምህርት ዘርፍ ያለውን የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና አካታችነት ሁኔታ የሚያሳይ አጠቃላይ ሀገራዊ የጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተደረገ።
በውይይት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ፣ ቀደም ሲል በዘርፉ የተሠሩ ሥራዎች በርካታ ለውጦችን ማምጣታቸውን አስታውሰው፣ ይህ ጥናት በትምህርት ዘርፉ የሚታዩ የጾታና የአካታች ትምህርት ክፍተቶችን በመለየት፣ በዘርፉ አዎንታዊና አካታች ለውጥ የሚያመጡ አሠራሮችን ለመዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገራዊ ጥናቱ ዋና ዓላማም በትምህርት ዘርፉ ያለውን የጾታ እኩልነትና አካታችነት በጥልቀት መገምገም፣ ዘላቂ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ምክረ-ሐሳቦችንና የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ማዘጋጀት እንዲሁም ወደ ተግባር እንዲለወጡ ማድረግ መሆኑንም አብራርተዋል።
በዚህም በጥናቱ ግኝቶች ላይ በመመሥረት የሚወጡ የውሳኔ ሐሳቦች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጸው የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና ፍትሐዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በመድረኩ እንደተገለጸው፣ የጥናቱ ውጤት በትምህርት ዘርፉ ፖሊሲዎች፣ በመምህራን ማሻሻያ ፕሮግራሞች፣ በትምህርት ቤት ማሻሻያ፣ በሥርዓተ-ትምህርትና በጎልማሶች ትምህርት ውስጥ የጾታ እኩልነትን በዘላቂነት ለማካተት የሚያስችሉ ግልጽ ጠቋሚዎችንና ተግባራዊ የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ለማዘጋጀት ትልቅ መሠረት ይሆናልም ተብሏል።

ለወሊሶ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦
በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት የምትገቡበትን የመግቢያ ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እስኪገለጽ ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ፦ በሌሎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተገኝታችሁ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ወደ ትምህርት ቤቶቹ በምትገቡበት ጊዜ መረጃ በሚከተሉት ስልኮች እየደወላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን፣

📢 በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።
2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦

3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁንእያሳወቅን፤
ቅሬታ ለማቅረብ https://student.ethernet.edu.et/university.../complaints ይህንን ሊንክ መጠቀም የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው እስከ መስከረም 22/2019 ከቀኑ 6:00 ብቻ መሆኑን እንገልጻለን።