SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
😢የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተፈጠረው ችግር አስደንጋጭና አስጊ ቢሆንም ዩንቨርሲቲው የሚሰጣችሁን ትዕዛዝ ጠብቁ ፤ ከግቢ በፍፁም እንዳትወጡ ❗️


ፈጣሪ ሀገራችንን ከገባችበት አደጋ ይፈርጃት😔



@ethioengineers1
👉የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/
.
⏩ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ
ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታ
ልኬት/Elevation/ እና በሁለቱ መካከል የሚገኘውን ማዕዘን/
Angle/ ለማውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው።
.
➡ሁለት አይነት የቅየሳ መሳሪያ ይገኛሉ
1. ቴዶላይት/Thedolite/
2. ቶታል ስቴሽን/Total Station/
➡ቶታል ስቴሽን ጂፒስ፣ጨረር እና የከፍታ መለኪያ ሴንሰር
በመጠቀም ትክክለኛ የከፍታ ልዪነት/Elevation difference እና ርቀትን ለመለካት ይጠቅመናል።
➡ቴዶላይት ደግሞ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ
ልዪነት ለመለካት ሲያገለግል በመካከላቸው ያለውን ርቀት ግን
መለካት አይችልም።
.
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇


@ethioengineers1
👍1
👉የአርማታ ብረት በሜትር ምን ያህል ይመዝናል?
.
⏩ለኮንስትራክሽን ግብዐት የምንጠቀማቸው የአርማታ ብረት በቅርፃቸው በሁለት ይከፈላሉ
1. ልሙጥ ብረት(Mild Steel or plain rebar)
2. ባለ ክርክር/አርማታ ብረት(Deformed steel rebar)
➡በጥንካሬ ደረጃ ደግሞ በስፋት Grade 60 እና Grade 40
በመባል ይለያሉ ይህም ውጥረታዊ ሀይል/tensile strength/ በመቌቌም አቅማቸው ነው።
*Grade 40=275.79MPa yield strength ሲኖረው
*Grade 60=413.68MPa yield strength ይኖረዋል።
.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

👇👇👇👇👇

@ethioengineers1
👉ስለ ብሎኬት
.
⏩Hollow Concret Block (HCB) ወይም የግድግዳ ብሎኬት/Wall HCB/ በመባል ይታወቃል።
*የብሎኬት ምርት ሲደረግ ጠቀሜታው ለሁለት ጉዳይ ነው
1. ሸክም መቌቌም የሚችል/Load Bearing/
2. ሸክም መቌቌም የማይችል /Non-Load Bearing/
*ይሄንን መሰረት ያደረገም የደረጃ ክፍፍል/Class/ ይኖራቸዋል።
*ሸክም መቌቌም የሚችሉት ብሎኬቶች "ክላስ ኤ እና ቢ" /
Class A and B/ በመባል ሲመደቡ ሸክም መቌቌም
የማይችሉት የብሎኬቶች ደግሞ "ክላስ ሲ" /Class C/ በመባል
ይመደባሉ።
➡ብሎኬት በተለምዶ በመጠናቸው ባለ10፣ ባለ15 እና ባለ 20 በመባል ይለያሉ::
ርዝመት x ስፋት x ቁመት/ Length x width x depth/
ማለትም Standard Dimenssion
*40x20x20cm
*40x20x15cm
*40x20x10cm
➡እያንዳንዱ ብሎኬት ሸክም የመቌቌም አቅማቸው
በሜጋ ፓስካል(Mpa) ይለካል
*Note:
1 kilogram per square centimetre = 0.0981 mega pascal

*Class A=3.8mpa
*Class B=3.2mpa
*Class C=1.8mpa .


https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
❤2
👉Today Tip
.
➡ በ አንድ ሜትር ካሬ ምን ያህል ብሎኬት እንጠቀማለን??
⏩የብሎኬት👇
▶ ስፋት =0.4ሜ
▶ቁመት =0.2ሜ
=1/(0.4*0.2)
=12.5
=~13
🚩ስለዚህ በ አንድ ሜትር ካሬ 13 ፍሬ ብሎኬት እንጠቀማለን ማለት ነው።



@ethioengineers1
አስቸኳይ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች
ዙሪያ # ከተቋራጮች፣ # አማካሪዎች እንዲሁም # ከጥቃቅንና_አነስተኛ_ኢን
ተርፕራይዞች ጋር የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ስለሆነም ከታች በተዘረዘረው
መርኃ-ግብር መሰረት በቢሮው 12ኛ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ
እናስተላልፋለን፡፡
መረጃው ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ሼር ያድርጉ
1.ከቢሮው ጋር በስራ ላይ የሚገኙ አማካሪዎች-----ሰኞ ሕዳር 07/2013 ዓ/ም
ከ3፡00-4፡00
2.ከቢሮው ጋር በስራ ላይ የሚገኙ ተቋራጮች-----ሰኞ ሕዳር 07/2013 ዓ/ም
ከ5፡00-6፡00
3.በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ልዩ አማካሪዎች---- ሰኞ ሕዳር 07/2013 ዓ/
ም ከ7፡30-8፡30
4.ደረጃ 6 ተመራቂዎች----- ሰኞ ሕዳር 07/2013 ዓ/ም ከ9፡00-10፡00
የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ ሕዳር 05/2013 ዓ/ም


@ethioengineers1
👉የጠቅላላ ሁኔታ ኮንስተራክሽን ውል (General Condition of contract)
.
▶🚧የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ አንድ ህንፃ ተቌራጭ ስራውን ለማከናወን ወደ ኮንስትራክሽን ሳይት የሚያስገባቸው የህንፃ
ግብዓቶች ከኮንስትራክሽን ሳይት የማስወጣት መብቱ ምን ያህል
ነው ድረስ ነው?

▶አማካሪ/መሐንዲሱ/ ስራው አልቌል ብሎ እስካልተስማማ
ድረስ እቃ ወይም ሰራተኛ ለማመላለስ ከሚወጣ መኪና በስተቀር ማንኛውም ለፕሮጀክቱ የተመደበ የህንፃ ግብዓት ከኮንስትራክሽን ሳይት እንዳይወጣ በደብዳቤ መከልከል ይቻላል።
.
83. 🚧Ownership of plant and material
83.1 All equipment, temporary works, plant and materials provided by the Contractor shall,
when brought on the Site, be deemed to be exclusively intended for the execution of the works and the Contractor shall not remove the same or any part thereof, except for the purpose of moving it from
one part of the site to another, without the consent of the Engineer. Such consent shall, however, not be required for vehicles engaged in transporting any staff, labor, equipment, temporary works, plant or
materials to or from the Site.


@ethioengineers1
🚧መያዥያ ገንዘብ (Retention money) vs
ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)???


1,ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)
.
➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል
1) ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
2)በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
3) ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።


2,መያዥያ ገንዘብ (Retention money)
.

👉ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።
▶ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።
▶ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።
▶በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።
ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በ
አርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

.
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

@ethioengineers1
👍1
👉What is standard box size?
.
▶width*length*depth
.
1. 40*50*20cm (mostly for cement mortar)
2. 40*50*18cm (for C-25 concrete)
3. 40*50*16cm (for C-30 concrete)
4. 40*50*14cm (for C-40 concrete but depend on mix design )
.
⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድር
ጉ።

@ethioengineers1
🚧ስለሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) እና የጥገና/የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)

========== ===========
#የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ የሚባለው በኮንስትራክሽን ውል አስተዳደር ወቅት ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ፈጽሞ ክፍያ በሚጠይቅበት ወቅት የፕሮጀክቱ ባለቤት ከግንባታው አማካሪ መሀንዲስ ጋር በመሆን ስለሥራው ጥራት ደረጃ በሚል ሊይዘው የሚችለው ዋስትና ነው፡፡
የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ዓላማ የግንባታውን ጥራት ለማስጠበቅ ሲባል ሥራ ተቋራጮች ለአሰሪዎች የሚገቡት ዋስትና ነው፡፡የግዥ መመሪያውም በአንቀጽ 28.5(ለ) ላይ በግልጽ እንደሚደነግገው በእያንዳንዱ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ 5(አምስት) ፐርሰንት የክፍያው ገንዘብ የሚያዝ ይሆናል፡፡
በዋናነት ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት የሚሆነው ገንዘብ ሥራው እንደ ተጠናቀቀ እና ጊዚያዊ የርክክብ ምስክር ወረቀት (provisional acceptance certificate) ከተሰጠ በኋላ ለሥራ ተቋራጩ ይመለስለታል፡፡ የቀረው ገንዘብ ደግሞ እስከ አንድ አመት ድረስ ዋቢ ሆኖ ይቆያል፡፡ ነገር ግን የተቀረው የመያዣ ገንዘብን አስቀድሞ ሥራ ተቋራጩ ለአንድ አመት የሚጸና ዋስትና ማቅረብ ከቻለ የተያዘበትን ቀሪ ገንዘብ ማስለቀቅ ይችላል፡፡
በተመሳሳይ መልኩም የሲቪል ሥራዎችን በተመለከተም እኤአ በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውልም ስለ የዋና ገንዘብ መያዣ ዋስትና በአንቀጽ 59(5) እና 60 ላይ ተቀራራቢ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡
BUT,,,,የሪቴንሽን ገንዘብ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ እና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡ በዚህ ሳቢያም ሥራ ተቋራጮች ለሌላ ወጪ የሚዳረጉበት ሁኔታ አለ፡፡////The law stipulates that the retention bond shall be paid to contractor after provisional acceptance or final acceptance but its applicability is denied by government side most of the time. So, dear contractors, please ask before you bankrupt///

#የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡ በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡ በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡


@ethioengineers1
👍2
🚧የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/

---------- ----------------

#የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡አንድ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡
#ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡
#ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡
#ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤትስ?(Announcing the successful bidder)
#ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡፡ የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የጨረታ ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡

@ethioengineers1
##የቅድሚያ ክፍያ (Advance Payment)

------------- -
------------ ------------

🚧በዚህ ፅሁፍ ቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው? አላማውስ? አቅራቢውና ተጠቃሚውስ ማን ነው? ያለባቸው ግዴታስ ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች እንዳስሳለን፡፡
የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና በኮንስትራክሽን ዉሎች ከሚዘወተሩ የዋስትና አይነቶች አንዱና የተለመደዉ ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ የቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው እሚለውን እንይ፡፡ በመንግስት ግዢ አዋጁ አንቀፅ 48 ላይ በመንግስት ገዥ አፈፃፀም ጊዚ አቅራቢዎች ከክፍያው ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቅርቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደሚስጥ ይገልፃል፡፡
ይህ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ከጠቅላላው የውሉ ዋጋ ሰላሳ ፐርሰንት (30%) መበለጥ እንደለለበትና ሊከፈል የሚችለው የገንዘብ መጠንም በጨረታ መመሪያው ላይ መገለፅ እንደሚገባው የመንግስት ግዢ መመሪያ አንቀፅ 16.26.1 ያስገድዳል፡፡
ተዋዋይ ተቋራጮችም ይህንን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት ከማመለከቻ ጋር የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ያልተገደበ ዋስትና (Unconditional Bak Guarantee) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሐገር ውስጥ ተቋራጮች ሲሆኑ በሁኔታዎች የተገደበ ዋስትና ከኢንሹራንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሚያቀርቡትም ዋስትና ከሚጠይቁት የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዋስትናው ምትክ ከመሰረታቸውና ከሚከታተላቸው ባለሰልጣን መስሪያ ቤት የሚያቀርቡት ደብዳቤ እንደ ዋስትና ተቀባይነት ይኖረዋል ሲል የመመሪያው አንቀፅ 16.20.5(ሐ) ይደነግጋል፡፡
ከዚህም በፊት ግን ተቋራጩ በግዢ ስነ-ስርዓቱ ያሸነፈውን ዉል መፈረምና የውል ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ዋስትና ያቀረበ መሆን አለበት (አዋጅ ቁ.649/2001፣ አንቀፅ 48/2/)፡፡
በአዋጁ አንቀፅ 78(3) መሰረት የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ አዋጁንና መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው መደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ [The Public Procurement Agency Standard Bidding Document: General Condition of Contracts: PPA-2011] ክሎስ 60(1) ላይ የቅድሚያ ክፍያው ለተቋራጩ መከፈል ያለበት ተቋራጩ ስራውን ለመጀመር የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን እነዲረዳው ታስቦ ሲሆን ይህም የሚከፈለው ተቋራጩ ለግንባታ ስራው የሚያገለግሉ ማሽኖችን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን መግዛቱን ወይም ማዘዙን የሚያሳይ መረጃ ሲያቀርብ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ በስራው ጊዜያትም ገንዘቡን እነዚህን ዕቃዎችና ማሽኖችን ለመግዛትና ወደ ግንባታ ቦታው ለማንቀሳቀስ/ለማዘዋወር የተጠቀመበት መሆኑን የሚያሳይ ፋክቱር/Invoices ለኢንጂነሩ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ የሚስተዋለው ችግር ቡዙ ጊዜ ተቋራጮች የቅድሚያ ክፍያውን ለታለመለት አላማ አያውሉም የሚል ሲሆን ይህም ችግር በተለይ በግንባታው ዘርፍ በተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ይህም ትልቁ ችግር መነሻው እነዚህ ተቋማት ምንም የሚያቅርቡት ዋስትና ሳይኖር ባቋቋማቸው መስሪያ ቤት ደብዳቤ ላይ ብቻ ተማምኖ ክፍያው ስለሚሰጣቸው ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ወይም በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የኢንሹራንስ ዋስትና ያቀረቡ ተቋራጮችን አሰሪው/ተዋዋዩ የመንግስት አካል አስፈላጊ ሲሆን፡ የቅድሚያ ክፍያው ገቢ የሚደረግበትና ከውሉ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ብቻ በመንግስትና በኢንተረፕራይዙ ወይም በኮንትራክተሩ ተወካዮች በጋራ ፊርማ ወጪ የሚደረግ የተለየ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ሊያዝ ይችላል፤ ገንዘቡም ለታሰበለት አላማ ብቻ እንዲውል የተለየ ስምምነት መፈራረም አለበት፡፡
ስለዚህ የቅድሚያ ክፍያ ማለት ተቋራጩ ለስራው ማስጀመሪያ የሚሆኑትን የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች መግዢያነት የሚውል በአሰሪው የመንግስት መስሪያ ቤት በቅድሚያ የሚከፈለው ገንዘብ ነው፡፡ ይህም ምንም ስራ ሳይሰራ የሚከፈል ገንዘብ ስለሆነ ለተቋራጩ ዕዳ ወይም ብድር ነው፡፡ ስለሆነም ተቋራጩ ብድሩን እንዲምልስ ይገደዳል ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ተቋራጩ ይህንን ብድር እንዴት ይመልሳል የሚለው አንዳንድ ጊዜ በግንባታ ውሎች ላይ አለመግባባት ያስነሳል፡፡ በግዢ መመሪያው አንቀፅ 16.26.9 ላይ እንደተገለፀው ለተቋራጮችና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተከፈለ የቅድሚያ ክፍያ በውሉ አፈፃፀም የተለያዩ ደረጃዎች ላይ በክፍያ ሰርተፍኬት ፀድቀው ከሚከፈሏቸው እያንዳንዱ ክፍያዎች ላይ እየተቀነሰ ሙሉ የቅድሚያ ክፍያው እስኪመልስ ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ያስቅራል፡፡ ይህም ማለት ተቋራጩ የወሰደውን የቅድሚያ ክፍያ ሙሉውን ከአንድ ወይም ከሁለት ክፍያዎች ላይ የመክፈል ግዴታ የለበትም፡ አሰሪ መስሪያ ቤቱም ሙሉ ክፍያውን አንዴ ቀንሶ ማስቀረት አይችልም ማለት ነው፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዳድ ጊዜ ሙሉ ቅድሚያ ከፍያውን በአንዴ ቀንሰው በማስቀረት ከተቋራጮች ጋ እሰጣገባ ሲገጥሙ ይስተዋላል፡፡ ይህ ከህጉ አግባብ ውጭ ነው፡፡
የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ሙሉውን ሳይመለስ በተለያዩ ምክንያቶች ውሉ ቢቋረጥ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ የከፈለውን ገንዘብ ማስመለስ እንዲያስችለው ተቋራጩ የሚያቀርበው ዋስትና ክፍያው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስገዳጅነት እንደሚኖውም መመሪያው ይገልፃል፡፡ ውሉ ቢቋረጥ እንኳን ያልተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው ወዲያውኑ ካለምንመ መቃወሚያ እንዲከፍል ይገደዳል ይላል የመደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ ክሎስ 60.7፡፡


@ethioengineers1
👉Some important facts

🚧1. Weight of one cement bag = 50 kg

🚧2. Minimum thickness of slab = 125 mm

🚧3. Minimum lintel thickness =15 cm

🚧4. Minimum diameter of bars used in slab= 8 mm

🚧5. Minimum diameter of bars Used in column = 12 mm

🚧6. Maximum diameter of bars in slab= 1/8x(thickness of slab )

🚧7. Maximum chair spacing = 1m

🚧8. Initial setting time of cement = 30 min

🚧9. Final setting time = 10 hrs ( 600 minutes )

🚧10. DPR = Detailed Project Report

🚧11. Unit weight

▶RCC = 25 KN/ m3
▶PCC = 24 KN/ m3
▶Steel = 7850 kg/ m3

🚧12. Minimum number of bars For square column or rectangular = 4 bars & For circular column = 6 bars

🚧13. Weight of steel = D2/162.2 kg/m.

🚧14. Slope of staircase = 25° -40° from horizontal.

🚧15. Size of concrete testing cube= (150x150x150)mm.

🚧16. Concrete cube is filled in 3 layers.

🚧17. Slump cone is filled in 4 layers.

🚧18. Cement should be used within three months of manufacturing.

🚧19. Minimum thickness of shear wall = 150 mm.

🚧20. Maximum thickness of shear wall = 400 mm.

🚧21. Universal testing machine is used for compression Test of concrete and tensile test of steel reinforcement.

🚧22. Minimum curing period of normal weather conditions is = 7 days

🚧23. Minimum curing period of dry and hot weather conditions is = 10 days

🚧24. Minimum percentage of steel in column = 0.8% of the cross section.

🚧25. Normal cover

➡️Footing = 50 mm
➡️Column = 25 mm
➡️Slab = 15 mm
➡️Beam = 25 mm

🚧26. Number Of Clear span stirrups in beam = Center to Center length /Total Length +1

🚧27. RCC is affected by water because of the corrosion of reinforcement bars.

🚧28. PCC is not affected by the water

🚧29. Maximum free fall of concrete = 1.5 m

🚧30. Air voids left in concrete is called as Honey Combing.

🚧31. The transverse reinforcement of column are called TIES.

🚧32. The transverse reinforcement in beams are called STIRRUPS.

🚧33. Cement ingredients are Burnt @ 1400°C temperature

🚧34. Short columns fail in Crushing.

🚧35. Long columns fail in Buckling.

🚧36. Intermediate columns can fail both in Buckling and Crushing.

🚧37. Strength of reinforcement shouldn't be less than 15 % of its designated strength.

🚧38. Compressive strength of bricks

▶️1st class bricks = 105 kg/cm2.

▶️2nd class bricks = 70 kg/cm2.

▶️3rd class bricks = 35 kg/cm2.

🚧39. PH value of water used concrete should not be less than 6.

🚧40. Riser = (150 - 200) mm.

🚧41. Tread = (250 - 300) mm.

🚧42. Height of parapet wall should be= 1m.

🚧43. TMT - Thermo mechanically treated bars.

🚧44. TMX - Thermax powered bars

🚧45. SDB - Super ductile bars.

#ConstructionNotes


@ethioengineers1
🚧ስለ ሐመር ቴስት

#ሐመር ቴስት/Hammer test/ አፍራሽ ያልሆነ (Non destructive) የአርማታ ጥንካሬ ደረጃ ማወቂያ ፍተሻ ሲሆን ትክክለኛ እና ፈጣን መመርመሪያ ዘዴ ነው።
.
▶ሐመር ቴስት የሚከናወንበት መንገድ ስፕሪንግ መቆጣጠርያ
ያለውን ክብደት መለኪያ መሳርያ ከላይ በምስል እንደሚታየው
የአርማታውን ገፅ ተጭኖ በመያዝ መልሶ የሚመታበትን አሀዝ
ልኬት መዝግቦ በመያዝ ይሆናል።
.
▶የሐመር ቴስት አላማውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያካትታል፤
1. የአርማታ የመታመቅ አቅም/compressive strength/
ለማወቅ።
2. የአርማታውን አንድ አይነትነት ወይም ወጥነት ለመገምገም።
3. የአርማታውን ክብደት የመሸከም አቅምን ከተወሰነለት ዲዛይን አንፃር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ።
.
▶የሐመር ቴስት ከማሰራት በፊት ሊደረግ የሚገባ ቅድመ
ሁኔታዎች፤
1) የአርማተዉ ገፅ የለሰለሰ፣ንፁህ እና ደረቅ መሆን ይጠበቅበታል
2) ናሙና የሚወሰደው ቦታ ቢያንስ 20ሚሊ ሜትር ከጠርዝ ሊርቅ ይገበዋል።
3) ስድሰት (6) ንባብ ከእያንዳንዱ የአርማታ አካል ይወሰዳል፤
አማካይ ስሌት ተሰርቶ ጥንካሬ መለኪያ ይደረጋል።
4) አርባ አምስት(45) ቀን የሞለው አርማታ መሆን ይጠበቅበታል።


@ethioengineers1
❤1
🚧የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat
with Drop or Solid Slab

.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::


@ethioengineers1
👍1
Forwarded from SMH General Construction
👉‌ጥናታዊ ጽሑፍ ለምታዘጋጁ ተመራቂ ተማሪዎች ስለምትሠሩት Proposal እና Research ትንሽ እገዛ እንስጣቹ ...
@ethioengineers1

▶️ በመጀመሪያ ደረጃ የሚመርጡት የጥናት ርዕስ መነሻውና መድረሻውን ሥነፍኖት በትክክል የተረዱትን መሆን ይገባዋል። ጥናታዊ ጽሑፍ መጨረሻ መታወቅ ያለበት ውጤቱ ነው እንጂ ሂደቱ መሆን የለበትም። ህደቱን ገና ከመጀመሪያው በትክክል እና በግልጽ (Accurately and clearly) መረዳትና ማወቅ ለውጤታማነት ተገቢ ነው። የጥናቱ ንድፈ ሀሳብ (Proposal) በሚገባ የሚመራ መንገድ መሆን አለበት። ጥናትን በተመለከተ ምሁራኑ የሚሉትን አንድ ታላቅ ገለፃ ላስታውሳችሁ "A research is as good as its propsal" -(የአንድ ጥናት ጥሩነት እንደ ንድፈ ሀሳቡ/ዕቅዱ/ ጥሩነት ይታወቃል) እንደማለት ነው። በመሆኑም የተወሰነ ምክረ ሃሳብ እገዛ ለማድረግ ጥቂት ነገር ላስታውሳችሁ። ልብ ሊባል የሚገባው ግን የግል ድጋፍ እንጂ የተቋም ይፋዊ format እያሳወቅሁ አለመሆኑን ነው።
.
▶️1ኛ. Title ፦ ርዕስ ለመመረጥ የመጀመሪያው ትኩረት ከሙያዎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ያስተውሉ። ከዚህ ባለፈ ሙያዎትን ተጠቅመው በአካባቢዎ ባለው ማህበረስብ ውስጥ ያለውን ችግር በመፍታት አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉበት ቢሆን ይመረጣል። ከዚህ አንጻር "ይህንን አይነት መፍትሔ ብሠራለትስ" የሚሉትን ችግር መርጠው አጭር እና ገላጭ የሆነ የጥናት ርዕስ መምረጥ ነው። ከተቋሙ አካባቢ ወጣ ያሉ ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ርዕሶች መሆንም ይችላሉ።
.
▶️2ኛ. Introduction to Your title ፦ በዚህ ርዕስ ሥር ስለ ጥናቱ ርዕስ ምንነት ገለጻ ማድረግ ነው። በዚህ ርዕስ ሥር የሚያካትቷቸው ይዘቶች defnitions, theories, materials used, tests, methods, constructions systems, types, ..... የመሳሰሉት ቢሆኑ መልካም ነው።
.
▶️3ኛ. Background to your title ፦ ይህ ደግሞ ስለሚያጠኑት ጥናት ታሪካዊ ዳራ/አመጣጥ (hisorical status) ገለጻ ማድረግ ነው። [who start investigate first, which country use, improvement (ማን ጀመርው? የት ቦታ? መቼ? በምን ተጀምሮ ወዴት ተሻሻለ all improvements፣ አሁን የት ደረሰ፣ .....) የሚሉትን የርዕሳችሁን ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስካለበት ድረስ ብቻ የምታስቀምጡበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ እርስዎ ሊጨምሩበት ወይም ሊቀይሩት ወይም ሊያስተካክሉት የሚችሉበትንም ጎን ጠቆም ማድረፍ መልካም ነው።
.
▶️4ኛ. Statement of the problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
.
▶️5ኛ. Objectives {General and Specific}፦ ጠቅላይ/ዋና ዓላማ ከአንድ ዓረፍተ ነገር ባይበልጥ ከበዛ ደግሞ ከሁለት በላይ እንዳይሆንይመከራል። በዝርዝር ዓላማ (specific objectives) የሚቀመጡት ደግሞ በዋና ዓላማ ዉስጥ የሚገኙ በጥናቱ መከናወን የሚታወቁ የተለያዩ መልሶችን ታስቀምጣላችሁ።
.
▶️6ኛ. Scope of the Research ፦ ይህ የሚገልጸው የጥናትችሁን ስፋተ-ሜዳ ነው። ምን ምን እንደሚያጠቃልል ወይም እንደሚዳስስ፣ ምን ምንን ደግሞ እንደሚተው /እንደማያጠቃልል/ ከነምክንያቱ፣ ለምን አይነት ተግባር የሚውል እንደሆነ ... በአጠቃላይ የጥናቱን መጠነ-ስፋት ወይም ይዘት የሚያስረዳ ይሆናል።
.
▶️7ኛ. Litrature review ፦ [በርዕሱ ዙሪያ እስካሁን የተጠኑ ጽሁፎች ምን ብለዋል?] “ማን የተባለው ሰው በየትኛው መጽሐፉ/ጥናቱ የትኛው ገጽ ላይ ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ምን ብሏል?“ የሚለውን መረጃ የያዘ ነው። በ"Litrature" ሥር የሚያካትቱት የቀደሙ ህትመቶች ማስረጃ ከእርስዎ ጥናት ጋር ተያያዥ ሀሳብ ያላቸውን ብቻ ነው። እርስዎ የማይዳሡትን ነገር በዚህ ርዕስ ሥር ማስገባት ከማንዛዛት እና ትርጉም አልባነት አያልፍም፣ ይልቁንም ሥራዎትን ውጤት (value) እና ተቀባይነት (acceptance) ሊያሳጣ ይችላል። በዚህ ሥር የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች reference specification [books, quastionary, journals, published apers, recorded interviews, vedio evidences] መሆን አለባቸው እንጂ guide specification [oral speeking, internet notes, handouts, non published documents] ላይ ያገኙትን ነገር ባይጠቀሙ ይመከራል። የተጠቀሙትን ምንጭም ከነመገኛ ገፁ አብረው ዋቢ ማስቀመጥም ተገቢ እና ግዴታ ነው።
.
▶️8ኛ.METHODOLOGY ፦ ይህ ደግሞ ዋናው የጥናት ሂደት መረብ ነው። ትናቱ የሚከናወንበት አካባቢ (study area)፣ ናሙና የሚወሰድበት የናሙና አወሳሰው ሥነዘዴ - ሥነዘዴው የተመረጠበትን ማስረጃ ምክንያት ጨምሮ (sampling system)፣ ከንድፈ ሀሳብ እስከ ፍጻሜ ያለውን የሚያሳይ የጥናቱ መነሻና መድረሻ ፍሰት (research deign - ብዙ ጊዜ በ"Chart" ሊገለፅ ይችላል) መካተት አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪ ቤተሙከራዊ ጥናት (Experimental research) ከሆነ የተለያዩ የቤተሙከራ ፍተናዎች (laboratory tests) የሚሠሩበት ስለሆነ የሚሰሩት ሙከራዎች (tests) የሚያስፈልጉ መሥሪያ ነገሪች (materials), መሥሪያ መሳሪያዎች (equipments), የሙከራ ሂደቶች (procedures to be used) የሚሉት ይዘቶች በግልፅ መታወቅ አለባቸው።
ከቤተሙከራ ውጪ ከሆነ ደግሞ አንዳንዶቹ ተግባራዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ የሚጠቀሙትን ሂደት ማስቀመጥ ተአቢ ነው። (ምሳሌ ~ መኪና መሥራት፣ በፀሀይ ጉልበት የሚሰራ ባቡር መሥራት ሊሆን ይችላል)።
በሌላ በኩል Theoretical or statistical data analaysis ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ከሆኑ ደግሞ የሚጠቀሟቸው የቃለመጠይቅ ጥያቄዎች (interiview questions)፣ የሚያስሞሉት የሰነድ ጥያቄ (questionair formats for data statistics)፣ የሚጠቀሟቸው የኮምፒዉተር ፕሮግራም (softwares to be used)፣ የሚፈልጉት ስታቲካዊ መረጃ (statistic data)፣ የሚሳተፉት ባለድርሳዎች (participants /responsible bodies)፣ የጥናት ማመዛዘኛ መንገድ (analaysis statics method..) የመሳሰሉትን ማካተት ተገቢ ሲሆን ይህ "Methodology" የሚባለው ክፍል አንድ ሰው በየትኛው ሥነዘዴ እንደሠራ የክንውን ሂደቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ነው።
.
✉️NB ፦ እነዚህ ከላይ ያሉት በሙሉ በንድፈ ሀሳብ ሰነድ (proposal document) ላይ ጭምር መስፈር ኣለባቸው ሲሆኑ ቀጥሎ ያለው ተራ ቁጥር 9፣ 13፣ 14 ብቻ ግ ን ጥናቱ ከተጀመረ በኋላ የሚካተ
Forwarded from SMH General Construction
‌▶️9ኛ .RESULT AND DISCUSSION ፦
.
❖RESULT [ፕሮጀክቱ የሚሰራው በTEST ከሆነ የተገኘውን ዉጤት፣ theory ከሆነ የ[intrview, questionaier, system documented data, real and visual application,...] የሚያሳዩትን ዉጤት/አኳኋን ማስቀመጥ ነው፡፡
❖DISCUSSION [ከተገኘው ውጤት አንጻር ለእያንዳንዱ ውጤት ሙያዊ ማብራሪያ እና የማሻሻያ ድጋፍ ሀሳብ ማስቀመጥ የሚጠበቅብዎት ክፍል ነው። [discuss weather the result implies good or bad accourding to proffesional point of view based on standards, laws, codes, contract agreement document, principles, softwares ... and put your proffesional solution for failures in the results]
.
▶️10ኛ. Beneficiariers of your project output {may not mandatory}፦ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጠቃሚ አካላት እነማ ናቸው። [may be scientists, teachers, students, farmers, gevornment, contractors, or all ethiopians or world.... as per your study scope]
.
▶️11ኛ. Desimination of output [i.e. how you make available your study paper for users? May be by puting at different libraries, publishing and posting on google, by training.....]
.
▶️11ኛ. የማጥኛ ጊዜ ሰሌዳ (Schedule)
▶️12ኛ. የሚያስፈልገው በጀት (Budget/cost)
.
▶️13ኛ . Conclusion
▶️14ኛ. Recommendation፦ [this should be not advice rather it is the measure to be taken for problems and organaizatinal failures based on your proffesional know how!]
.
▶️15ኛ. Reference
▶️16ኛ. Appendex .
⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
👉1. ኪነህንጻ እና ቀለም

🏷1.1 ጥቁርና ነጭ ቀለማት በውስጥ እይታ

▶️ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው በአዲሳባ ከተማ በደንበል ህንጻ ውስጥ የሚገኝ የቶሞካ የቡና መጠጫ ካፌ ነው።

🚧ጥቁርንና ነጭ ቀለምን በመጠቀምና ተቃርኖን በማምጣት ውስጣዊ ስሜቱን ህይወት አላብሰውታል።

🚧በተለይ በእንደዚህ ሰዎች ብዙ ግዜአቸውን በማያጠፉባቸው ቦታዎች ላይ ተቃርኖን መጠቀም ሲመከር ፣ ለመኖርያ ቦታ ውስጣዊ ክፍሎች ግን ተደጋጋፊ ቀለማት ይመረጣሉ።


#ColorAndArchitecture

@ethioengineers1
👉በቁፋሮ ወቅት ሳይት ላይ ሊገኙ ስለሚችሉ አንዳንድ ነገሮች
ኮንስትራክሽን ኮንትራት ውል ምን ይላል???


⏩ለምሳሌ: ወርቅ ወይም ሌላ መዐድን ቢገኝ

🚧ምላሹ ከዚህ ፅሁፍ በምስል አያይዘንላቹዋል።

#ConstructionLaw


@ethioengineers1
🚧ፓራሜትሪክ ስነ-ህንጻ ንድፍ

➡️ፓራሜትሪክ ስነ-ህንፃ በንድፍ መስፈርቶች እና በዚህ ሂደት የመጨረሻ ንድፍ ውጤት ምርት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገልፁ እና የሚያቀናጁ መለኪያዎች እና ደንቦችን መጠቀም የሚያስችል በአልጎሪዝም መርሃግብር ላይ የተመሠረተ  አሁናዊና አለም የደረሰበት የንድፍ ሂደት ነው፡፡

🚧በዚህም ባብላጫው የኮምፒውተር ስሌት እርዳታ የሚያስፈልግ ሲሆን ባገራችን እስካሁን ይሄንን የተገበረ ህንጻ የለም።

🚧የባህር ማዶ ህንጻ ምሳሌ ከላይ ኣያይዘንላቹዋል።

#Architecture

@ethioengineers1