SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
👉ADMIXTURES

➡Admixtures are the special ingredients added during concrete mixing to enhance the properties and performance of fresh concrete.

➡️Various types of
admixtures are available in the market which is
used in construction work.
.
➡FUNCTION OF ADMIXTURES

⏹1. To accelerate or retard the setting time of fresh
concrete.
⏹2. To improve the workability or flow ability of concrete.
⏹3. To increase the strength and durability of
concrete.
⏹4. To reduce the heat of hydration.
⏹5. To reduce the segregation and bleeding.
⏹6. To decrease the permeability.
⏹7. To achieve other desired properties.
.
➡TYPES OF ADMIXTURES

*⃣1. ACCELERATING ADMIXTURES

▶️This admixture is added in concrete or mortar for
increasing the rate of hydration of hydraulic cement and for shortening the setting time. Calcium
chloride (CaCl2) is the most widely used
accelerating admixture.

*⃣2. RETARDING ADMIXTURES

▶️Retarding admixtures delay the initial rate of
hydration of cement and extend the setting time of
cement paste.

▶️This admixture can be used in high temperature and where the concrete has to be transported to a long distance.

▶️It is also suitable for using in grouting oil wells.

*⃣3. AIR-ENTRAINING ADMIXTURES

▶️Air entraining admixtures help to produce a certain
amount of air bubbles in the concrete mixture. The
main goal of this admixture is to increase the resistance against freeze-thaw degradation and cohesion.

▶️It also improves the workability of fresh concrete without changing the setting or the rate of hardening.


*⃣4. WATER REDUCING ADMIXTURES

▶️As the name suggest, water reducers are added to a concrete mixture, mortar or grout to increase the flow ability without increasing the water content.

🏷Advantages Of Water Reducing Admixtures

🚧1. The rate of concrete placement is faster.

🚧2. Strength, durability, density etc are significantly improved.

🚧3. Segregation, permeability, and cracking are reduced
.
.
➡SPECIAL ADMIXTURES

⏺1. Superplasticizing admixtures.
⏺2. Corrosion-inhibiting admixtures.
⏺3. Grouting admixtures.
⏺4. Coloring admixtures etc.


@ethioengineers1
👍1
Forwarded from SMH General Construction
👉ስለ ኦፒሲ እና ፒፒሲ የ ሲሚንቶ ኣይነቶች ትንሽ እንንገራቹ
.
⏩OPC— Ordinary Portland cement

⏩PPC —Portland pozzollana cement


➡በሀገራችን ኢትዮጲያ በስፋት ህንፃ እና መሰረተ ልማት ግንባታ
ላይ በስፋት እየተጠቀምንባቸው የምንገኝባቸው የሲሚንቶ አይነቶች ናቸው።
የሁለቱንም የሲሚንቶ አይነቶች ጥቅም አንድነት እና ልዩነት ከዚህ በታች አጠር አድርገን እናቀርባለን።
▶ኦፒሲ/OPC/ በምጣነ ስርገት( Permeability) ከ ፒፒሲ/ PPC/ ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ ነው።
ውሃ ዘልነት /Heat of Hydration/ የኦፐሲ ከፍተኛ በመሆኑ ከፒፒሲ በተሻለ መልኩ ቶሎ የሚፈለገውን ጥረንካሬ ቀድሞ ያገኛል። በተቃራኒው ደግሞ ፒፒሲ heat of hydration ቀርፋፋ በመሆኑ ለመርጋት/curing period/ ተጨማሪ ቀናት ይወስዳል
ማለት ነው።
👉በጥንካሬ ደረጃ /Grade of Strength / ኦፒሲ 42.5R grade cement ሲሆን ፒፒሲ ደግሞ 32.5R Grade Cement ነው።
➡Note: Number represent compressive strength of
cement in MPa.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
Forwarded from SMH General Construction
✅what is The circled Number with the letter R in the picture?👆
.
✅The number "42.5" and the letter "R" together gives information about the strength class of cement.
.
✅The strength class of cement classifies its compressive strength at 28 days.

https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
🔹Important concept -

▫️Which type of cement is used for underground concrete structures ?

🚧SRC (Sulphate Resisting Cement)

🚧 The use of SRC is recommended for following applications: Foundations, piles, basements and underground structures. Sewage and Water treatment plants. Chemical, Fertilizers, Petrochemical factories, Food processing units.

@ethioengineers1
🚧በኮንስትራክሽን ውል ጀኔራል ኮንዲሽን እና ስፔሻል ኮንዲሽን

# ጀኔራል ኮንዲሽኖች እንደ FIDIC , MoWUD 1994, እና PPA ህግ
አይደሉም።

# የውል አካል ሲሆኑ ብቻ በተዋዋዮች ወገኖች ላይ አስገዳጅነት ይኖራቸዋል።

# ምክንያቱም ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር
ህግ 1731 ይደነግጋል።

# ስፔሻል ኮንዲሽኖችም የውል አካል ይደረጋሉ። አስፈላጊነቱም ጀኔራል
ኮነንዲሽኑን ከሀገራቱ ህግ ጋር ማጣጣም ነው።

# የጀኔራል ኮንዲሽንን ይዘት መቀየር አይቻልም። በስፔሻል ኮንዲሽን ማሻሻል
ግን የተፈቀደ ነው።

# ስፔሻል ኮንዲሽን ደግሞ ከጀኔራል ኮንዲሽን የተፈጻሚነት ቅድሚያ አለው።

# የኢትዮጵያን የኮንስትራክሽን ህግ ስትመለከቱት የህንጻ አዋጁና መመሪያው
ሆነ የግዥ አዋጅና መመሪያ እና ሌሎች የህግ ማእቀፎች በአብዛኛው በግንባታ
ውል የተዋዋዮችን መብትና ግዴታ አይመለከቱም። የፍትሀብሄር ህጉ ምናልባት
የተበታተኑ ድንጋጌዎች አሉት።

# ስለዚህ ለምን የተዋዋዮችን መብትና ግዴታ የሚገዛ ልዩ የኮንስትራክሽን ውል
ህግ/ኮንስትራክሽን ኮድ/ አይኖረንም?ቢኖረን ምን ይጎዳናል? የሚል ጥያቄ
ሊነሳ ይችላል። ምላሹ ግልጽ ነው። በአብዛኛው ጀኔራል ኮንዲሽኖች በዘርፍ
መሀንዲሶች እንደ ህግ ነበር የሚቆጠሩት።ኮንስትራክሽን ኮድ ቢዘጋጅ በጣም
ጠቃሚ ነው።
አመሰግናለሁ!!


@ethioengineers1
👉በኮንስትራክሽን ውል አማራጭ የሙግት መፍቻ
====================
መግቢያ
----------------
▶️የኮንስትራክሽን ውሎች በባህሪያቸው ብዙ እና ውስብስብ ቴክኒካል ዶክመንቶችን የውሉ አካል አድርገው የሚያካትቱ ናቸው፡፡ከነዚህም ውስጥ ጀኔራል ኮንዲሽኖች፣ስፔሻል ኮንዲሽን፣ቢል ኦፍ ኳንቲቲ፣ስፔስፊኬሽን፣ዲዛይኖች፣የውል ማስከበሪያ፣የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነድ ጨምሮ ሌሎችንም የውል አካል ተደርገው የሚካተቱ ዶክመንቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ በአንድ የኮንስትራክሽን ውል ውስጥ ይሄን ያህል ልዩ ልዩ አይነት ሰነድ መኖሩ በይዘት እርስ በእርሱ የሚጋጭበትን እና በይዘቱ አለመግባባትን የመፍጠር እድሉ ስለሚኖር የውሉ አካል በሚሆኑት መካከል ግጭት የመፈጠሩ አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡
*በኮንስትራክሽን ውሎች ተሳታፊ የሚሆኑ አካላት ብዙ መሆናቸውም ግጭት የመፈጠር እድሉን ሰፊ ያደርገዋል፡፡ይሄውም በኮንስትራክሽን ውል አፈጻጸም ዙሪያ አሰሪ፣ተቋራጭ፣ንኡስ ተቋራጭ፣ዲዛይነር፣አማካሪ መሀንዲስ፣እቃ አቅራቢ፣የዋስትና ሰጭ ባንክና ኢንሹራንስ ተሳታፊዎች መሆናቸው ከተለያየ አቅጣጫ ግጭትና አለመግባባት ሊፈጠር የሚችልበትን አጋጣሚና ሁኔታ ሰፊ ያደርገዋል፡፡
*የኮንስትራክሽን ውል ጋር የተየያዙ ግጭቶች ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ቴክኒካዊ ውስብስብነት የሚኖራቸውና የህግ ሙያ ብቻ ባለው ሰው በቀላሉ እልባት ሊያገኙ የሚችሉ አይደሉም፡፡በኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ የኮንስትራክሽን ውል ጋር የተያያዙ ግጭቶች በአብዛኛው በቀጥታ በፍርድ ቤት በኩል እልባት የሚያገኙበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ይህ ሁኔታም በብዙ መልኩ ሲመዘን ትክክል ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡
*ስለዚሁም በአብዛኛው አለም ሀገራት ጥቅም ላይ የሚውሉ እና በኛም ሀገር በተወሰነ ደረጃ እንደ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ባሉ ተቋማት ጥቅም ላይ የሚውሉና እየዳበሩ የመጡ በጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ የተካተቱ አማራጭ የግጭ መፍቻ መንገዶችን በዚህ ጽሁፍ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
*የኮንስትራክሽን ዘርፉ ግዙፍ ሀብት የሚንቀሳቀስበት እንደመሆኑ መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ የግጭት መፍቻ መንገዶችን አሳሪ የህግ ማእቀፍ በማስተካከል፣የአሰራር ስርአት በመዘርጋት እና አለማቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን የግጭት መፍቻ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ፈጣን ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል፡፡
፡
▶️ከ 1999 በፊት የነበሩ FIDIC ጀኔራል ኮንዲሽኖች በዋናነት ለመሀንዲሱ የውሳኔ ሰጭነት ስልጣን የሚሰጡ ናቸው፡፡ መሀንዲሱም ገለልተኛ እና ነጻ ሆኖ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይገመት ነበር፡፡
*በእርግጥ በአብዛኛው መሀንዲሱ ዲዛይኑን የሚሰራበት ሁኔታ በመኖሩ እና ዲዛይን አዘግይቶ ለተቋራጭ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ስለሚኖር እና ለመሀንዲሱ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍለው አሰሪው በመሆኑ እና መሀንዲሱ ለወደፊት ከአሰሪው ስራ ለማግኘት ሊያስብ ይችላል የሚለው በመኖሩ የመሀንዲሱ ገለልተኛነት ጉዳይ በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የግጭት መነሻ እየሆነ በመምጣቱ ሌሎች ተራማጅ አማራጮችን ማየት አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል፡፡
:
▶️FIDIC 1999 general condition of contract for civil engineering works...
*ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን አዲስ የግጭት አፈታት መንገድ ይዞ ብቅ ያለ ነው፡፡ Dispute Adjudication Board(DAB) በዚህ ቨርሽን የመጣ አዲስ ሀሳብ ነው፡፡
*ይህ ቦርድ ግጭት በተከሰተ ጊዜ በአሰሪና ተቋራጭ የሚመረጥ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ውሉ ሲደረግ ስማቸው የተዘረዘረ ገላጋዮችን የያዘ ዝርዝር የውሉ አካል ተደርጐ እስከውሉ መጨረሻ ድረስ የሚከሰቱ ግጭቶችን በገላጋይነት የሚፈቱበት ሁኔታም ይኖራል፡፡
*እንግዲህ ቦርዱ(DAB) በሰጠው ውሳኔ ላይ ደስተኛ ያልሆነ ወገን ደስተኛ ያለመሆኑን በ28 ቀን ውስጥ ማስታዎቅ ይኖርበታል፡፡ (notice of dissatisfaction) በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የቦርዱ ውሳኔ ላይ ደስተኛ ያለመሆንን ማስታዎቅ ያልተከናወነ እንደሆነ የቦርዱ ውሳኔ አስገዳጅና የመጨረሻ ይሆናል፡፡
*ቀጥሎ የሚመጣው ለ56 ቀን የሚቆይ በሰላም ለመፍታት የመሞከር ሂደት(amicable settlement) ነው፡፡ይህን ሂደት ሳይሞክሩ ማለፍ አይቻልም፡፡ ይህ ሂደት ካልተሳካ የመጨረሻው ሂደት አርቢትሬሽን ይሆናል፡፡
* እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ቦርዱ(DAB) አርቢትሬተር አይደለም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጽያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀን 04/04/2012ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በፓርላማ እንዲጸድቅ ያስተላለፈው የ1958 የኒውዮርክ ኮንቨየንሽን በቦርዱ(DAB) ውሳኔ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ በዚህ አጋጣሚ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኒውዮርክ ኮንቨየንሽንን ለማጽደቅ የመምራቱ ጉዳይ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትንም የመሳብ እድል ይኖረዋል፡፡
:
*ስለ Dispute Adjudication Board(DAB) ዝርዝር ሁኔታወች በተለይ ገላጋዮች ስለሚመረጡበት ሁኔታ እና ስለስነስርአት ድንጋጌዎች በጥልቀት በጀኔራል ኮንዲሽኑ ክሎስ 20 ላይ ተቀምጧል፡፡
:
▶️The new 2017 edition of FIDIC...
ይህ አዲሱ የፊዲክ ቨርሽን ደግሞ dispute avoidance/adjudication board(DAAB) የሚል ቦርድ ያካተተ ነው፡፡ ይሄውም ከ1999 ፊዲክ ጋር በአብዛኛው ጉዳይ ተመሳሳይ ቢሆንም ግጭት ማስወገድ/ avoidance/ የሚለውን አዲስ ሀሳብ ያካተተ ነው፡፡ በዚህም ቦርዱ አሰሪና ተቋራጮች የማያግባባቸው ነገር በሚከሰት ጊዜ ተቀራርበው ተነጋግረው የማያግባባቸውን ነገር እንዲፈቱ የማገዝና ወደ ግጭት እንዳያመራ የማገዝ ስራን የጨመረ ነው፡፡
*ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር ለማወቅ ክሎስ 21 መመልከት ይቻላል፡፡

▶️በመጨረሻም....
@ethioengineers1

*መንግስት ጊዜ መፍጀት ሳያስፈልገው የፍትሀብሄር ስነስርአት ህጉ አንቀጽ 315 ድንጋጌን በማስተካከል የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በግልግል እንደማይታዩ የሚደነግገውን እንዲያሻሽለው ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡
*በሀገራችን 80 በመቶ የሚሆነው ግንባታ በመንግስት አሰሪነት የሚከናወን እንደመሆኑ እና አለማቀፉን የአርቢትሬሽን ውሳኔ ማስፈጸሚያ ኮንቨየንሽን ለማጽደቅ እየተንቀሳቀስን ባለንበት ሁኔታ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በአማራጭ የግጭት መፍቻ መንገድ እንደማይፈቱ የሚደነግገውን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315 ባለበት ማስቀጠል አስፈላጊ አይደለም፡፡
*ከዚህ ጋር በተያያዘ በጣና ውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ድሬዳዋ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን መካከል በሰ/መ/ቁ 127459 በቀን መስከረም 23/2010ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔም መታየት አለበት፡፡ይዘቱም የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለ ው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም አርቢትሬተር ነው ይላል፡፡አርቢትሬተር የአስተዳደር ውሎችን እንዳይዳኝ በህግ ክልከላ ከተደረገበት አላማ አንጻር አጁዲኬተርም ሊፈቀድለት አይገባም ምክንያቱም የሁለቱም ውሳኔአቸው አስገዳጅነት ያለው ስለሆነ እና ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ አለመግባባት የሚፈታባቸው ናቸው ይላል፡፡ስለዚህ በዚህ ውሳኔ መሰረት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውል ጉዳይ በግልግል ዳኝነት አይታይም ማለት ነው፡፡ይህ ውሳኔ ተራማጅ የሆነውን አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ በአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች ጉዳይ ተፈጻሚ እንዳይሆን በማድረግ ምእ
ራፉን የዘጋ ነው፡፡
*ስለሆነም ምእራፉ የተዘጋው አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ ተፈጻሚነት ዳግም እንዲነሳ እና ከአለማቀፉ እድገትና ዝማኔ ጋር መራመድ እንችል ዘንድ መንግስት የኒውዮርክ ኮንቨየንሽንን ለማጽደቅ በጀመረው አግባብ ጎን በጎን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) እና በሰ/መ/ቁ 127459 በቀን መስከረም 23/2010ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ(ህግ ስለሆነ) የህግ ማእቀፉን ሊያስተካክለው ይገባል፡፡ .
⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ
።

@ethioengineers1
👉DIFFERENCE BETWEEN PERT AND CPM # repost

➡PERT and CPM are most commonly used methods for project management.

➡️In this article, we will discuss the differences between PERT and CPM.

🚧WHAT IS PERT?

➡️PERT or Programme Evaluation and Review
Technique is an event oriented method of network planning. In it, the emphasis is focused on start and completion events rather than on activities.

➡️The activities taking place between events are not specified.

➡️In PERT network, the events fall in logical
sequence But the logic of events may be different
for different planners. Hence PERT network may
vary from planner to planner depending upon their decision as which event to precede or occur
concurrently.

➡️In PERT network the start circle is omitted and only the completed event is recorded.

➡️PERT helps in identifying critical area which threatens the completion of the work.

➡️It provides the means to
determine how resources can be transferred from
one job to another job.

🚧WHAT IS CPM?

➡️CPM is also network comprising events and
activities.

➡️This network is activity based.

➡️The activities are represented by arrowed lines and events by circles.

➡️The activities are connected in logical sequence.

➡️The time allotted to each activity is related to cost.

🚧DIFFERENCE BETWEEN PERT AND CPM

🏷1. PERT is event oriented whereas CPM is activity oriented.
▶️In simple words, in PERT network interest is focused upon start or completion of events and
not on activities themselves.

🏷2. In CPM network no allowance is made for
uncertainties in the duration of time involved
whereas in PERT network uncertainty is considered.

🏷3. In PERT, time is not related to cost whereas in
CPM the object is to develop an optimum time
cost relationship. However, PERT has since been
extended in this direction and the line dividing
PERT/CPM is gradually fading out.

🏷4. In CPM duration of activity is estimated with a
fair degree of accuracy. In PERT duration of
activities are not so accuraten and definite.

🏷5. In CPM both time and cost can be controlled
during planning. Pert is basically a tool for
planning

🏷6. PERT is used in research and development
project, basically for non-repetitive type projects.
CPM is widely used in construction projects.

#PERT

#CPM

#ConstructionPlanning
👍1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👉ስለ ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
⚡ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን
ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
*ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው።
ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ።
የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength)
ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች
አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት
ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
(compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ
ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ
ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
*ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
*አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ
መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15
የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15
የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ
«C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።


@ethioengineers1
👍1
"በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ አንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም።

💚💛❤️
#itsmydam
#itsyourdam
#itsallethiopiandam
❤1
👉Specific Gravity of Fine Aggregate Test

➡️Fine aggregate is used in many fields in sites for many purposes.

⏺So the determination of specific gravity of fine aggregate is very essential.

➡️Specific gravity of fine aggregate can be defined as the ratio of the weight of given volume of coarse aggregate to the weight of given volume of distilled water.

🚧Apparatus for determination of specific gravity of fine aggregate

📌Pycnometer Balance weight

🚧Procedure for the determination of specific gravity of fine aggregate

▶️Clean the pycnometer, dry it, Find the weight of the pycnometer.

▶️Take about 200gm of coarse aggregate sample in the pycnometer.

▶️Weight the pycnometer, Note the weight W2Fill the remaining part of pycnometer with distilled water and weight W3 Empty the pycnometer and clean it and fill it with distilled water.
Note the weight W4

➡️Calculations

▶️Empty weight of pycnometer =   W1 Weight of pcynometer + sample= W2 Weight of pycnomete+ sample+water = W3 Weight of pycnometer + water =   W4

⏹The specific gravity of fine aggregate (G) = W2-W1 / (W2-W1) – (W3-W4)

#ConcreteTechnology

@ethioengineers1
👉 እስቲ ኣሁን ደሞ ስለ Sheet Pile Wall ትንሽ እንንገራቹ።
.
*እነዚህን ከላይ የምታዩትን ምስል Sheet Pile ይባላሉ እነዚህ ሲስተሞች በማያያዝ አንድ ወጥ ግድግዳ/wall ለመገንባት እንጠቀምባቸዋለን፡፡

*Sheet pile ዎል እንደ Retaining wall, cofferdam እና ተመሳሳይ የ ግድግዳ ስትራክቸሮች ለመገንባት ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡

*የተወሰነው አካላቸው መሬት ውስጥ የሚቀበረውም pile driving ማሺን በመጠቀም ነው፡፡ በከለር ፎቶ የሚታየው Larson/ U Type ይባላል::


@ethioengineers1
👉 ከ ታሪክ ማህደር በ Building Codes ዙርያ

🚧Building Codes :-
የሚገነቡ ህንፃዎች ማሟላት የሚገባቸውን
እስታንዳርዶች የያዘ የህጎች ስብስብ ነው፡፡
ህንፃዎች የግንባታ
ፍቃድን ለማግኘት Building Code መከተል አለባቸው፡፡
የእስታንዳርዶቹ አስፈላጊነትም - ሴፍቲ ፤ ጤና እና ጠቅላላ
የህንፃውን ደህንነት ( Structural , Mechanical , Sanitary , Fire resistance. Earth quake, Flood , Water Supply, Light, Ventilation, ወዘተ ) ለማረጋገጥ ነው ……. ኣለማችን ላይ EBCS,Eurocode , IS, BS, ወዘተ የምንላቸው የህንጻ ኮዶች ኣሉ፡፡ የኛ ደሞ EBCS(Ethioian building code of standards) ይባለል።
.
.
ከላይ የምትመለከቱት ህንፃ በሃገረ ሩሲያ - ሙሉ ለሙሉ
ከእንጨት ተገንበቶ የነበረ ረጅም ህንፃ ሲሆን Fire resistance
standard ባለሟሟላቱ የአካባቢው ባለስልጣናት አፍርሰውታል፡፡


@ethioengineers1
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

@ethioengineers1
👉Load Combination
.
🚧Load Combination - አንድ ፎቅ ላይ የሚመጡ ሎዶችን Analyze ስናደርግ ሁሉም ሎዶች (LL,DL,EQ,WL, etc)
በተመሳሳይ ሰዓት ይከሰታሉ ተብሎ አይታሰብም እንደዛ ቢሆን ኖሮ ለትንንሽ ፎቆች ትልልቅ size ያላቸው Beam, Column እና
Slab ባስፈለገንና Uneconomical በሆንን ነበር፡፡
እንትን ሎድና እንትን ሎድ አንድ ላይ ሲከሰት ወዘተ እያልን Load
Combination እናወጣለን፡፡ ሎዶቹንም በ Factor እናባዛቸዋለን:: Factor ያስፈለገበትም ምክንያት Load
occurrence probability እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ
Load Uncertainties ለማስወገድ ነው፡፡
.
ስንት Load Combination አለ??
.
.
ብዙ ምሁራን በ Load Combination ብዛት ሲወዛገቡ ይታያል፡፡
አንዳንዶች 2 ነው ይላሉ ፤ ሌሎች 7 ነው ይላሉ ፤ ሌሎሎሎች 5
፤ ሌሎሎሎሎሎች 11……..ለማንኛውም ሰባትና ዘጠኝ ናቸው!!!
.
.
ሰባት የሚሆነው Earth Quake እና Wind Loadን እኛ
ካልኩሌት አድርገን ከሁለቱ Govern የሚያደርገውን ከለየን በኋላ
Governing ሎዱን በቁጥር ለሴፍትዌሩ (SAP/Etabs)
ስንሰጠው ሰባት ነው፡፡
.
.
ዘጠኝ የሚሆነው የ Earth Quake ወይም Wind ሎዱን የተለያዩ ፋክተሮች ለሶፍትዌሩ እንሰጠውና እራሱ ሶፍትዌሩ ሎዱን ካልኩሌት አድርጎ አንዲጠቀም ከፈለግን ዘጠኝ Combo እንጠቀማለን፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍1
🚧አርክቴክቸራል ምስል (Architectural Diagram):-

🔹ይህ ምስል አርክቴክቸራል ስዕል ነው። ከዚህ ምስል ብዙ ነገሮችን መረዳት ብንችልም በጥቂቱ ለማየት እንሞክር:-
👉የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ሌይኣውት ዲያግራም ያሳያል።
👉እያንዳንዱን የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች የሚቀመጡበትን ቦታ ና ልኬታቸውን ያሳያል።
👉የተለያዩ የኤሌክትሪክ ሰርኪዩቶችን ያሳየናል።
👉በተለያዩ አክሰሰሪዎች መካከል ያለውን የኤሌክትሪክ ገመድ ብዛት ያሳየናል።
👉የተለያዩ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎችን (ማብሪያ ማጥፊያዎች፣ መብራቶች፣ ሶኬቶች ወዘተ) ያሳየናል።

Source :- amen

👉ለሌሎችም ያጋሩ!

@ethioengineers1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቻይናዊያን አንድ ባለ5 ፎቅ የት/ት ቤት ሕንፃን ካለበት ስፍራ ነቅለው በሌላ ቦታ የተከሉበት ቴክኖሎጂ እና ድርጊት ዓለምን እያነጋገረ ነው፡፡‼️

☑️ በሻንጋይ ከተማ ይገኝ የነበረው በዕድሜው 85 ዓመት የሞላው ታሪካዊ ሕንፃ የቆመበት ስፍራ ለሌላ ልማት በመፈለጉ ነው ሕንፃው ሳይነካ እንዳለ ተነቅሎ በሌላ ቦታ የተተከለው፡፡

☑️ ይህ ባለ አምስት ፎቅ ሕንፃ ከቦታ ቦታ 65 ሜትር እንዲጓዝ የተደረገውም ተራማጁ ማሽን በተባለ አዲስ የሮቦት ቴክኖሎጂ ነው፡፡

☑️ከሕንፃው መሰረት ስር 200 ያህል የሮቦት እግሮች ስለተገጠሙለት ሕንፃው ጉዳት ሳይደርስበት በተገጠመለት እግር ተጉዞ ከተፈለገው ቦታ እንዲቆምተደርጓል፡፡

@ethioengineers1
👉ስኬል/Scale/

➡️ዛሬ ለ አንድ የህንፃ ፕላን ለማንበብ ከሚጠቅሙን አንዱ የሆነውን ስኬልን እናያለን።

▶️አርክቲክቱ የህንፃው ፕላን ዲዛይን ሲያደርግ ከሚገነበው ቤት እኩል መጠን ያለው አድርጎ መስራት አይችልም።

▶️በዚህም የተነሳ በስኬል አሳንሶ ሶፍትዌር(AutoCAD) ላይ ዲዛይን ያደርገውን በወረቀት ፕሪንት ተደርጎ በተቀመጠው ስኬል መሰረት ህንፃው ይገነባል።

➡️ለተለያየ አላማ የተለያዩ የስኬል አይነቶችን ሊጠቀም ቢችልም ለ ህንፃ እና መንገድ ግንባታ በብዛት የሚጠቅሙ የ ስኬል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው:-

🚧1. 1:200 ሲነበብ አንድ ለሁለት መቶ ሲሆን ትርጉሙም 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 200 ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

🚧2. 1:100 ሲነበብ አንድ ለአንድ መቶ ሲሆን ትርጉሙም 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 100ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

🚧3. 1:50 (አንድ ለ ሃምሳ) ትርጉሙ 1 ሚ.ሜ ፕላን ላይ 50 ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

🚧4. 1:20 (አንድ ለ ሃያ) ትርጉሙ 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 20ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

Via:- Amen

#Architecture


@ethioengineers1
👍1
🚧በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ
ኢንጅነርዎች ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ ነጥቦች...

.
1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING
MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ
አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል
የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ
አንማር ይሆናል
ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር
ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም
ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::
:
2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና
ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን።
እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።
:
3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት
አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !
:
4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካ ምድራቸው
የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር
የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ
(Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።
፡
5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ
አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች
የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና
ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ።
ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል
፡
6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።
ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ
ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል
ማለት ነው።
ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው::
፡
7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው።
(እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)
፡
8 የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)
ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።
ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ
ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።
አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ
መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት
የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን
አደጋ ለመከላከል።
፡
9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣
ለጥንቃቄ
የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን
ነው
:
10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION
WITHLABOR) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ
እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ
ሊኖረን ይገባል።
ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።
ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና
ወሳኝ ነገር ነው።
.
.
አንድ ጥሩ የሚባል CONSTRUCTION እንጅነር ማወቅ
ስለሚገባው ነገሮች ትንሽም ቢሆን እውቀት እንደሰጠናቹ ተስፋ
እናረጋለን::


@ethioengineers1