🤔የአንድ ፕሮጀክት Defect Liability period (365 ቀናት) ተጠናቆ ሲያበቃ Retention እንድንከፍል ስንጠየቅ የተፈጠረው Structural Defect ከተያዘው ገንዘብ በላይ ቢሆን ምን እናደርጋለን?
👇
@Ethiocon143bot
👇
@Ethiocon143bot
🤔13❤6🔥1
SMH General Construction
🤔የአንድ ፕሮጀክት Defect Liability period (365 ቀናት) ተጠናቆ ሲያበቃ Retention እንድንከፍል ስንጠየቅ የተፈጠረው Structural Defect ከተያዘው ገንዘብ በላይ ቢሆን ምን እናደርጋለን? 👇 @Ethiocon143bot
መልስ:-
በconstruction contract administration ውስጥ በጥንቃቄ መያዝ ያለበት ጉዳይ ነው። Defect Liability Period (DLP) 365 ቀን መጠናቀቁ ብቻ ማለት የStructural Defect ኃላፊነት በራሱ ያበቃል ማለት አይደለም።
በተለይ Structural Defect ከRetention ገንዘብ በላይ ከሆነ፦
1. Retention በቀጥታ አትክፈሉ። መጀመሪያ defect-ው በቴክኒክ እንዲረጋገጥ ያድርጉ።
2. Structural assessment/investigation በብቃት ባለው Structural Engineer/consultant ያስደርጉ። የdefect-ው መንስኤ፣ ክብደት፣ የመጠገኛ ወጪና የህንፃው ደህንነት ይረጋገጥ።
3. Contractor በcontract መሠረት እንዲያስተካክል በጽሑፍ ይጠየቅ። ችግሩ በContractor's defective workmanship/material/design ምክንያት ከሆነ፣ የመጠገን ኃላፊነቱ በRetention መጠን ብቻ አይወሰንም።
4. Retention ከጠየቀው ገንዘብ በላይ የሚያስፈልግ የrepair cost ካለ፣ በcontract ውስጥ ያሉ ሌሎች security/remedy provisions መሠረት ይመርመሩ። ለምሳሌ Performance Security አሁንም ተፈጻሚ ከሆነ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
5. ተጨማሪው ወጪ ከContractor እንዲመለስ የሚያስችለው የcontract clause ካለ መሠረቱን በግልጽ ይያዙ። Retention ብቻ እንደ “maximum liability” መቆጠር አይገባም፣ ይህ ግን በተፈረመው contract ቃላት ይወሰናል።
6. ክፍያ ለመልቀቅ ከመወሰን በፊት የFinal/Completion Certificate፣ defect notification፣ inspection report፣ structural assessment፣ repair estimate እና contract clauses አንድ ላይ ይመርመሩ።
በተለይ የሚለየው
DLP = 365 days ማለት በዚያ ጊዜ ውስጥ የታዩ defects እንዲታረሙ የContractor's contractual obligation የሚታይበት ጊዜ ነው። ነገር ግን ከ365ኛው ቀን በኋላ የተገኘ Structural Defect ላይ ኃላፊነት አለ/የለም የሚለው በContract Particular Conditions, GCC/PCC, applicable law እና defect-ው በመጀመሪያ መነሻው ላይ ይወሰናል።
ስለዚህ በጉዳዩ ላይ “365 ቀን አልቋል፣ Retention ክፈሉ” ብሎ ብቻ መወሰን ትክክል አይሆንም። Structural defect-ው በcontractor ኃላፊነት ውስጥ መሆኑ ከተረጋገጠ በመጀመሪያ የrepair/remedy ጉዳዩ መፍትሄ ማግኘት አለበት።
https://t.me/ethioengineers1

Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍10❤7
Delay Justification, Extension of time(EOT) እና የጊዜ ጉዳት መቀጮ/Liquidated damage/:
በኢትዮጵያ ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የግንባታ ፕሮጀክቶች (Construction Projects) ላይ በስፋት ስለሚተገበሩት (Delay Justification)፣(Time Extension Request) እና (Liquidated Damages) አተገባበር በመጠኑ ሃሳብ ለመስጠት የተጋጀ አጭር ፅሁፍ ነው፡፡
1ኛ. የፕሮጀክት መዘግየት ምክንያታዊነት ማብራሪያ (Delay Justification)
Contractor የተሰጠውን ስራ በቅድሚያ በውል በተወሰነው ጊዜ ማጠናቀቅ ግዴታ እንዳለበት ግልፅ ነው። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ፕሮጀክቱ በጊዜ ላይጠናቀቅ ይችላል። ስለዚህ ለነዚህ የባከኑ ጊዜዎች አሳማኝ ምክንያቶች በማቅረብ የፕሮጀክቱን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የጊዜ ማራዘሚያ ለመጠየቅ ይችላል።
🌟ለፕሮጀክት መዘግየት ምክንያቶች
1. የፈጣሪ ቁጣ (Force Majeure):
*ከባድ ዝናብ፣ጎርፍ፣አውሎነፋስና የመሳሰሉ ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ምክንያቶች ናቸው።
2 በተቋራጭ ምክንያት የሚፈጠር መዘግየት:
*በውሉ ዕቅድ መሰረት የግንባታ ሀብቶችን/ማቴሪያል፣የሰው ሀይል፣ ማሽነሪና ባጀት ማቅረብ አለመቻል።
*የስራ አመራር ችግር/ከእቅድ ዝግጅት ችግር፣የማደራጀት ብቃት ማነስ፣የመምራት፣የክትትልና ቁጥጥር ብቃት ከማነስ/
3. በአማካሪ ምክንያት የሚከሰቱ
*ለማፅደቅ ማዘግየት/ዕቅድ፣ዲዛይን፣ሜትዶሎጂ፣ክፍያ... /
4. በአሰሪ ምክንያት የሚከሰቱ
*የክፍያ ማዘግየት፣ ቢሮክራሲ፣ የፍላጎት ለውጥ/Change & Variations.. /፣....
5. ከመሬት በታች ያልተጠበቁ ክስተቶች/Unforseen works/:
*ከመሬት በታች በሚሰራ ቁፋሮ ስራ ወቅት በመጠን ወይም በዓይነት የተለየ ስራ ሲያጋጥም/በውል ያልተጠቀሰ የአፈር ዓይነት/Unpredicted soil strata/፣ ቫኩም ወይም ቮይድ/void/፣ የማያቋርጥ የሚፈልቅ/ምንጭ ውሃ/Underground Water/፣ የደካማ አፈር ጥልቀትና መጠን/over volume of loss soil/፣...
6. በመንግስት የፖሊሲ ለውጥ ምክንያትና
7 የፖለቲካ ጫና፣ጦርነትና ርሃብ
2ኛ. የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ስለማቅረብ/EOT/
ሥራ ተቋራጩ ለስራው መዘግየት ምክንያት ናቸው የሚላቸውን ነጥቦች አንድ በአንድ በመጥቀስ፣በማስረጃ በማብራራት ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ጊዜ እንዲፈቀድለት ማቅረብ የሚችል ይሆናል።
3ኛ. ለባከነ የግንባታ ጊዜ ''የጊዜ ጉዳት መቀጫ''/Liquidated damage/
ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ምክንያት ለአሰሪው የጊዜ ጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡
በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር:
-የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣
-ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣
-የሳይት መረከቢያ ቀን/site handover/፣
-የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና
-የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡
እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/Partial completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡
**ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/Extension of Time / ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡
ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡
የሀገራችን የህግ ማዕቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል?
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ ጊዜ የጉዳት መቀጫ/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡
የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡
ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡
በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ10% መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡
በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡በኮመን ሎው የጊዜ የጉዳት መቀጫ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

❤18👍12
Behind the scenes! 🏗️ Recording today's educational session LIVE on TikTok right now.
Join me 👇
tiktok.com/@belaychane21
Join me 👇
tiktok.com/@belaychane21
❤1
🏗️ የReinforced Concrete (RC) ዲዛይን
የRC ዲዛይንን ለመረዳት ፎርሙላዎችን በመሸምደድ ብቻ መጀመር አያስፈልግም። በመጀመሪያ የህንፃውን የጭነት አሰራርና የኮንክሪት እና የአርማታ ብረት ባህሪ መረዳት ይጠቅማል።
1️⃣ ጭነት የት ይሄዳል?
ማንኛውም ህንፃ የሚሸከማቸው ጭነቶች አሉት፦
• የህንፃው የራሱ ክብደት
• የግድግዳ ክብደት
• የወለል ንጣፍና ሌሎች ቋሚ ጭነቶች
• የሰዎችና የእቃዎች ጭነት
• የንፋስ ጭነት
• የመሬት መንቀጥቀጥ ጭነት
ከዚያም ጭነቱ በአጠቃላይ፦
Slab → Beam → Column → Foundation → Soil
በሚል የጭነት መንገድ ወደ መሬት ይተላለፋል።
ይህንን የጭነት መንገድ መረዳት የRC ዲዛይን መሠረታዊ እውቀት ነው።
2️⃣ ኮንክሪት እና ብረት ምን ያደርጋሉ?
ኮንክሪት በአብዛኛው የመጨመቅ (Compression) ኃይልን በጥሩ ሁኔታ ይቋቋማል።
የአርማታ ብረት (Reinforcement Steel) ደግሞ በተለይ የመሳብ (Tension) ኃይልን ለመቋቋም ይረዳል።
ስለዚህ ብረት በኮንክሪት ውስጥ በዘፈቀደ አይቀመጥም።
የብረቱ ቦታ የሚወሰነው በአባሉ ላይ በሚሰሩት ኃይሎች ነው።
3️⃣ Beam – ጨረር
Beam በሁለት ጫፎቹ ተደግፎ ጭነት ሲጫንበት ይጎነበሳል።
በአጠቃላይ፦
🔹 የBeam ታችኛው ክፍል → Tension
🔹 የላይኛው ክፍል → Compression
🔹 የታችኛው ዋና ብረት → Tension ለመቋቋም
🔹 Stirrups → Shear ለመቋቋም
በContinuous Beam ውስጥ ደግሞ በSupport አካባቢ የኃይል ሁኔታው ስለሚቀየር የላይኛው ብረት አስፈላጊ ይሆናል።
ስለዚህ የReinforcement አቀማመጥ የBeam የኃይል ባህሪን መከተል አለበት።
4️⃣ Slab – ስላብ
Slab የወለል ጭነቶችን ተቀብሎ ወደ Beam፣ Wall ወይም Column ያስተላልፋል።
Slab በአጠቃላይ፦
• One-way slab
• Two-way slab
ሊሆን ይችላል።
የReinforcement አቀማመጥም ስላቡ ጭነቱን በሚያስተላልፍበት አቅጣጫ ይወሰናል።
5️⃣ Column – አምድ
Column በዋናነት ከላይ የሚመጣውን የህንፃ ጭነት ወደ Foundation ያስተላልፋል።
ነገር ግን Column ሁልጊዜ Compression ብቻ አይሸከምም።
ሊኖሩት የሚችሉት፦
• Compression
• Bending
• Shear
• ከንፋስ ወይም ከEarthquake የሚመጡ ኃይሎች
ናቸው።
የLongitudinal Bars ዋና ሚና የColumn ጥንካሬን ማሻሻል ሲሆን፣ Ties/Stirrups ደግሞ የLongitudinal Bars አቀማመጥን ለመጠበቅና ኮንክሪቱን ለመጠበቅ ይረዳሉ።
6️⃣ Foundation – መሠረት
Foundation የህንፃውን ጭነት ወደ መሬት ያስተላልፋል።
Building → Column → Foundation → Soil
ስለዚህ Foundation በቂ መጠንና ጥንካሬ ሊኖረው ይገባል።
የSoil Investigation ውጤትም በFoundation Design ውስጥ በጣም ወሳኝ ነው።
7️⃣ ብዙ ብረት ማለት ሁልጊዜ ጥሩ ዲዛይን ማለት አይደለም
❌ በጣም ትንሽ reinforcement → የመሰንጠቅ፣ የመጎንበስ እና የጥንካሬ ችግር
❌ በጣም ብዙ reinforcement → የብረት መጨናነቅ፣ የኮንክሪት አቀማመጥ ችግር እና የግንባታ ችግር
✅ ጥሩ RC Design = Safe + Economical + Serviceable + Constructible
8️⃣ Detailing እንደ Calculation አስፈላጊ ነው
የብረት መጠንን ማወቅ ብቻ አይበቃም።
መሐንዲሱ እንዲሁም መወሰን አለበት፦
• ብረቱ የት እንደሚቀመጥ
• የሚቀጥልበት ርዝመት
• የLap ቦታ
• Anchorage
• Bar spacing
• Concrete cover
• Beam-column joint detailing
ጥሩ ዲዛይን በስሌት ብቻ አይጠናቀቅም፤ በግንባታ ላይ በተግባር ሊፈጸም የሚችል መሆን አለበት።
9️⃣ በአጠቃላይ ሶስት ነገሮችን ይፈትሹ
🏗️ Strength – አባሉ የሚጠበቀውን ጭነት በደህና መሸከም ይችላል?
🏠 Serviceability – ከመጠን በላይ መሰንጠቅ፣ መጎንበስ ወይም ንዝረት አይኖርም?
🛡️ Durability – መዋቅሩ ለረጅም ጊዜ በቂ ጥበቃና አገልግሎት ይኖረዋል?
🔑 የRC Design በጣም ቀላል መንገድ
Load → Load Path → Structural Behaviour → Reinforcement → Safety + Serviceability + Durability + Constructability
ይህንን አሰራር ከተረዳን በኋላ ፎርሙላዎችን መማር፣ የStructural Analysis Software መጠቀም እና የRC Design ስሌቶችን መስራት በጣም ቀላል ይሆናል።
የStructural Engineering ትምህርት ከFormula ማስታወስ በላይ ነው፤ የStructure ባህሪን መረዳት ነው።🏗️

❤36👍1
ለኢንጅነሮች
ኣንድ Client ሬሾው 1:2:3 በሆነ 60m3 የሚሆን የኮንክሪት ስራ ቢኖረውና ስንት ስሚንቶ አሸዋና ጠጠር እንደሚያስፈልገው በዝርዝር ማወቅ ፈለጎ ስራልኝ ቢላችሁ እንዴት ትሰሩለታላችሁ? Dry volume factor 1.54
መልስ
➛ የተሰጠን ዳታ
ጠቅላላ የኮንክሪት ስራ መጠን 60ሜ3
Mix ratio 1:2:3
Assume dry-volume proportion 1.54
➛ከዚህ በመቀጠል ለ1ሜ3 ኮንክሪት የሚያስፈልገን የኮንክሪት ማተርያል እናስላ።
በመጀመርያ የሚከተሉትን እንያዝ
➛1ሜ3*1.54 = 1.54ሜ3
➛Total proportion = 1+2+3 = 6parts
1. የስሚንቶ መጠን ለማወቅ
➛ስሚንቶ፦ 1/6*1.54ሜ3 = 0.257ሜ3
በመቀጠል ይሄንን volume assumption በወሰድነው density of cement 1400kg በማባዛት በKg ወይም በ Number of bags ማማወቅ እንችላለን በዚህ መሰረት፦
🔨 ስሚንቶ≈ 1400ኪ.ግ/ሜ3 * 0.257ሜ3
≈ 359.8 ኪ.ግ
በማጠጋጋት ≈ 360ኪ.ግ ወይም 3.6ኩንታል ወይም
7.2ከረጢት ለ 1 m³ concrete.
2. የአሸዋ መጠን ለማወቅ
➛በተሰጠን ሬሾ መሰረት አሸዋ 2parts ስለሆነ በቀላሉ ከላይ ያሰላነው የስሚንቶ volume በሁለት በማባዛት ማግኘት እንችላለን።
🔨 አሸዋ ≈ 2* 0.257ሜ3
≈ 0.514ሜ3 ለ 1 m³ concrete.
3. የጠጠር መጠን ለማወቅ
➛በተሰጠን ሬሾ መሰረት ጠጠር 3parts ስለሆነ በቀላሉ ከላይ ያሰላነው የስሚንቶ volume በሶስት በማባዛት ማግኘት እንችላለን።
🔨 ጠጠር ≈ 3* 0.257ሜ3
≈ 0.771ሜ3 ለ 1 m³ concrete.
4. የውሃ መጠን
➛ እዚጋ ማስቸዋል ያለብን ነገር amount of water cannot be determined from the ratio 1:2:3 alone because it depends on the required workability, aggregate moisture, cement type, and water/cement ratio.
➛የ ውሃና ስሚንቶ ሬሾ (W/C ratio) በmix design የሚወሰን ቢሆንም ባብዛኛው ግዜ ግን ከ 0.4 እስከ 0.6 ባለው ሬንጅ ውስጥ ነው።
➛በዚህ መሰረት በአማካይ 0.5 ብንወስድ ለ1ሜ3 ኮንክሪት የሚያስፈልገንን የውሃ መጠን ለማወቅ በቀላሉ
w/c = 0.5
w/0.257ሜ3 = 0.5
w = 0.5*0.257ሜ3
w = 0.1285ሜ3 ወይም በ1000 በማባዛት128.5ሊትር ያስፈልገናል ማለት ነው።
🔑 ሲጠቃለል ለ60ሜ3 የኮንክሪት መጠን
➛ስሚንቶ 3.6ኩንታል*60= 216ኩንታል
➛አሸዋ 0.514ሜ3*60= 30.84ሜ3 በማጠጋጋት 2ቢያጆ
➛ጠጠር 0.771ሜ3*60= 46.26ሜ3 በማጠጋጋት 3ቢያጆ
➛ውሃ 0.1285ሜ3*60= 7.71ሜ3 ለ curing እና ለሌሎች ታሳቢ በማድረግ 10ሜ3 ያስፈልገናል።

❤54👍13🤔2
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
✅ 100% Recorded Video Package
✅ Learn at your own pace
✅ Practical design workflow from start to finish
✅ Weekly live virtual support sessions
Package 1 – ETABS Full Course
💰 8,500 ETB
Structural Modeling,Load Application,Structural Analysis,Design Checks,Professional workflow for multi-storey buildings with Design Permit Check Lists
Package 2 – SAFE Full Course
💰 6,500 ETB
Slab Design,Foundation Design,Mat Foundation Analysis,Detailing and interpretation of results
Package 3 – ETABS + SAFE Complete Bundle
💰 12,750 ETB (15% Discount)
Full ETABS Course,Full SAFE Course
🎯 Designed For
Civil Engineers,Structural Engineers,Engineering Students,Design Office Professionals
📩 Limited seats available. Contact us today to reserve your place.
Learn. Design. Build with Confidence.
📞 Registration & Information
Phone: +251 711 890 392
Telegram 👉 @BelayChaneST

👍8❤2
🚀 BELAY CHANE MASTER CLASS
🏗 ETABS & SAFE Online Course
B+G+M+21 RC Building Project
Modeling, Analysis & Design
በተግባር ይማሩ!
📢 አሁኑኑ ይመዝገቡ!
+251711890392
📲 @BelayChaneST
🏗 ETABS & SAFE Online Course
B+G+M+21 RC Building Project
Modeling, Analysis & Design
በተግባር ይማሩ!
📢 አሁኑኑ ይመዝገቡ!
+251711890392
📲 @BelayChaneST
❤1
⚡️በ Work Brake down እና Cost Brake down ያለው ልዩነት ምንድ ነው?
1. WBs (ዎርክ ብሬክዳውን)፦
በኮንስትራክሽን ዘርፍ Work Brake down ማለት እያንዳንዱ የኮንስትራክሽን ስራ ወደ ትናንሽ'ና በቀላሉ ማኔጅ የሚደረጉ ሥራዎች መከፋፈል ማለት ነው ለምሳሌ የሚከሉትን እንመልከት
a. Earth work
➛ Site clearing
➛ Bulck Excavation
➛ Trench Excavation
➛ Pit Excavation
➛ Back Filling
➛ Hard Core
b. Foundation work
➛ Lean concrete
➛ Form work
➛ Reinforcement
➛ Concrete casting
ከላይ እንደምናየው በዚህ መልኩ የኮንስትራክሽን ስራዎችን ብንከፋፍላቸው በቀላሉ የስራ ዕቅድ ለማውጣትና ስራዎቹን በቀላሉ ለመቆጣጠረ ይረዳናል።
2. CBs (ኮስት ብሬክዳውን)፦
ኮስት ብሬክዳውን ማለት ግን ለእያንዳንዱ Single Item work ማለትም ከላይ በ WB ለከፋፈልናቸው ስራዎች አዋጭ መስርያ ዋጋ በዝርዝር አስልቶ ማስቀመጥ ማለት ነው። ዋጋ ስናወጣ በዋናነት ማካተት ያለብን ነገር የሚከተሉት ናቸው
a. Manpower cost
b. Material cost
c. Equipment or Machinery Cost ከዚህ በተጨማሪ Profit እና Overhead cost ማካተት ግድ ይለናል።

❤19👍12🙏2
📢 WE ARE HIRING: FREELANCE QUANTITY SURVEYING ENGINEERS (3 POSITIONS)
Company/Project: Construction | Design
Work Arrangement: Freelance | Remote | Monthly
Number of Vacancies: 3 Engineers
Application Deadline: October 16, 2026
Job Description
Successful candidates will be responsible for preparing accurate Bills of Quantities (BOQs), quantity take-offs, construction cost estimates, material schedules, and detailed cost breakdowns based on architectural and structural drawings.
Application Requirements
Interested applicants should submit:
🔹Updated CV.
🔹Samples of previous BOQs, quantity take-offs, or cost-estimation projects.
🔹A brief description of relevant experience and software skills.
🔹Expected monthly freelance fee.
🔹Availability and contact information.
Selection Process: Shortlisted candidates may be required to complete a practical quantity take-off assessment using sample construction drawings.
📅 Application Deadline: October 16, 2026
📩 To Apply: Send your CV and work samples to @Belay_Ceng

❤8👍1
Cost Breakdown
👉 ማለት ለእያንዳንዱ የግንባታ ሥራ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን በዝርዝር ለይቶ ማስላት ነው።
ዋና ዋና የወጪ ክፍሎች፦
✅Material Cost: ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ብረት፣ ውሃ እና ሌሎች ዕቃዎች።
✅Labour Cost: የሠራተኞች ደመወዝ፣ የቀን ክፍያ ወይም የሰዓት ክፍያ።
✅Equipment Cost: የማሽን ኪራይ፣ ነዳጅ፣ ኦፕሬተርና ጥገና።
✅Overhead Cost: የጣቢያ አስተዳደር፣ ጊዜያዊ ቢሮ፣ ደህንነትና ሌሎች ተዘዋዋሪ ወጪዎች።
✅Profit: ተቋራጩ ከወጪዎች በላይ ለማግኘት የሚያስቀምጠው ትርፍ።
በእውነተኛ የዋጋ ስሌት የታክስ፣ የትራንስፖርት፣ የብክነት እና የገበያ ዋጋ ልዩነት ተጽዕኖዎችም እንደ ውሉ ሁኔታ መታሰብ አለባቸው።

👍18❤4
⚡️የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድ ስታንዳርዶች (EBCS)
⚡️ዋና ዋና የEBCS ተከታታይ ስታንዳርዶች
EBCS-1፡ የዲዛይን መሠረቶች እና በመዋቅሮች ላይ የሚፈጸሙ ጫናዎች የመዋቅር ዲዛይን መሠረታዊ መርሆዎችን ያቀርባል፣ እነዚህም የመጨረሻ የአቅም ሁኔታ (Limit State Design)፣ የጭነት ጥምረቶች፣ የደህንነት መጠኖች (Safety Factors)፣ የሞተ ጭነት (Dead Load)፣ የተግባር ጭነት (Imposed Load)፣ የነፋስ ጭነት (Wind Load) እና ሌሎች የአካባቢ ተጽዕኖዎችን ያካትታል።
EBCS-2፡ የሕንፃዎች ዲዛይን
የሕንፃ ዕቅድ፣ የቦታ ምርጫ፣ የአጠቃቀም ብቃት፣ ተደራሽነት እና ሥነ-ሕንፃዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አጠቃላይ መስፈርቶችን ይገልጻል።
EBCS-3 እስከ EBCS-6፡ የመዋቅር ቁሳቁስ ዲዛይን ስታንዳርዶች
* EBCS-3፡ የኮንክሪት መዋቅሮች
* EBCS-4፡ የብረት እና የተዋሃዱ (Composite) መዋቅሮች
*EBCS-5፡ የእንጨት መዋቅሮች
* EBCS-6፡ የግንበኝነት (Masonry) መዋቅሮች
እነዚህ ስታንዳርዶች ለእያንዳንዱ ቁሳቁስ የዲዛይን ዘዴዎች፣ የቁሳቁስ መግለጫዎች፣ የዝርዝር ማብራሪያ መስፈርቶች እና የግንባታ ሂደቶችን ይዘረዝራሉ።
EBCS-7፡ የጂኦቴክኒክ ዲዛይን እና መሠረቶች
የቦታ ምርመራ፣ የአፈር ምደባ፣ የአፈር ተሸካሚ አቅም ግምገማ፣ የሰፈር ትንተና (Settlement Analysis)፣ የመሠረት ዲዛይን፣ የድጋፍ ግድግዳዎች (Retaining Structures) እና የመሬት ሥራዎችን ይመለከታል።
* EBCS-8፡ የርዕደ መሬት መቋቋም የሚችሉ መዋቅሮች ዲዛይን
የሴይስሚክ ዲዛይን መስፈርቶች፣ የሴይስሚክ ዞኖች ግምት፣ የመዋቅር ትንተና ሂደቶች እና ለርዕደ መሬት መቋቋም የሚያስፈልጉ ዝርዝር መስፈርቶችን ይዟል።
* EBCS-9፡ የሕንፃዎች የፕላምቢንግ አገልግሎቶች
የውሃ አቅርቦት ሥርዓቶች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የቆሻሻ ውሃ አወጋገድ፣ የዝናብ ውሃ ፍሳሽ፣ ሴፕቲክ ታንኮች፣ ሶክአዌይ ጉድጓዶች (Soakaway Pits) እና ተያያዥ የፕላምቢንግ ሥራዎችን ያካትታል።
* EBCS-10፡ የሕንፃዎች የኤሌክትሪክ ተከላዎች
የኤሌክትሪክ ሽቦ ሥርዓቶች፣ የመከላከያ መሣሪያዎች፣ አርቲንግ (Earthing/Grounding)፣ የኤሌክትሪክ ደህንነት እና በሕንፃዎች ውስጥ የኃይል ስርጭትን ይወስናል።
* EBCS-11 እስከ EBCS-13፡ የሕንፃ አገልግሎቶች
የሕንፃ ሜካኒካል አገልግሎቶች፣ የአየር ማናፈሻ (Ventilation) ሥርዓቶች፣ የአካባቢ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የእሳት መከላከያ መስፈርቶችን ይዳስሳል።
* EBCS-14፡ በህንፃ ግንባታ ውስጥ ጤና እና ደህንነት
የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት፣ የአደጋ መለያየት፣ የደህንነት ምልክቶች፣ የግል መከላከያ መሣሪያዎች (PPE) እና ደህንነቱ የተጠበቀ የግንባታ ሥራ ሂደቶችን ይወስናል።
⏺ከዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች ጋር መጣጣም
⏺ኢትዮጵያ የህንፃ ስታንዳርዶቿን ከዓለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው ኮዶች ጋር በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርዶች (Eurocodes) እና ከISO ስታንዳርዶች ጋር በማጣጣም ላይ ትገኛለች። እነዚህ የተጣጣሙ ስታንዳርዶች ብዙ ጊዜ እንደ (ES EN) በመታተም የአገሪቱን የምህንድስና ሥራ ከዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ያስማማሉ።
ይህ መጣጣም የሚያስገኘው ጥቅም፦
* የመዋቅር ደህንነትና አስተማማኝነት መሻሻል።
* በግንባታ ውስጥ የጥራት ማረጋገጫ መጠናከር።
* ከዓለም አቀፍ የምህንድስና እና የግንባታ ልምዶች ጋር የተሻለ ተኳሃኝነት መፍጠር።
* ለአካባቢያዊ እና ሴይስሚክ አደጋዎች የተሻለ መቋቋም መቻል።
https://t.me/ethioengineers1
የኢትዮጵያ የህንፃ ኮድ ስታንዳርዶች (EBCS) በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተዘጋጁ ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሕንፃዎችና የሲቪል ምህንድስና ሥራዎች ደህንነት፣ አገልግሎት ሰጪነት፣ ጤናማነት እና ጽናት እንዲኖራቸው የሚያስችሉ አጠቃላይ ደንቦች ናቸው።
እነዚህ ስታንዳርዶች የሕንፃዎችና መዋቅሮች ዕቅድ ዝግጅት፣ ዲዛይን፣ ግንባታ፣ አሠራር እና ጥገና የሚመለከቱ ዝቅተኛ መስፈርቶችን ይወስናሉ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን አካባቢያዊ፣ ጂኦሎጂካዊ፣ የአየር ንብረት እና ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባሉ።
⚡️ዋና ዋና የEBCS ተከታታይ ስታንዳርዶች
EBCS-1፡ የዲዛይን መሠረቶች እና በመዋቅሮች ላይ የሚፈጸሙ ጫናዎች የመዋቅር ዲዛይን መሠረታዊ መርሆዎችን ያቀርባል፣ እነዚህም የመጨረሻ የአቅም ሁኔታ (Limit State Design)፣ የጭነት ጥምረቶች፣ የደህንነት መጠኖች (Safety Factors)፣ የሞተ ጭነት (Dead Load)፣ የተግባር ጭነት (Imposed Load)፣ የነፋስ ጭነት (Wind Load) እና ሌሎች የአካባቢ ተጽዕኖዎችን ያካትታል።
EBCS-2፡ የሕንፃዎች ዲዛይን
የሕንፃ ዕቅድ፣ የቦታ ምርጫ፣ የአጠቃቀም ብቃት፣ ተደራሽነት እና ሥነ-ሕንፃዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አጠቃላይ መስፈርቶችን ይገልጻል።
EBCS-3 እስከ EBCS-6፡ የመዋቅር ቁሳቁስ ዲዛይን ስታንዳርዶች
* EBCS-3፡ የኮንክሪት መዋቅሮች
* EBCS-4፡ የብረት እና የተዋሃዱ (Composite) መዋቅሮች
*EBCS-5፡ የእንጨት መዋቅሮች
* EBCS-6፡ የግንበኝነት (Masonry) መዋቅሮች
እነዚህ ስታንዳርዶች ለእያንዳንዱ ቁሳቁስ የዲዛይን ዘዴዎች፣ የቁሳቁስ መግለጫዎች፣ የዝርዝር ማብራሪያ መስፈርቶች እና የግንባታ ሂደቶችን ይዘረዝራሉ።
EBCS-7፡ የጂኦቴክኒክ ዲዛይን እና መሠረቶች
የቦታ ምርመራ፣ የአፈር ምደባ፣ የአፈር ተሸካሚ አቅም ግምገማ፣ የሰፈር ትንተና (Settlement Analysis)፣ የመሠረት ዲዛይን፣ የድጋፍ ግድግዳዎች (Retaining Structures) እና የመሬት ሥራዎችን ይመለከታል።
* EBCS-8፡ የርዕደ መሬት መቋቋም የሚችሉ መዋቅሮች ዲዛይን
የሴይስሚክ ዲዛይን መስፈርቶች፣ የሴይስሚክ ዞኖች ግምት፣ የመዋቅር ትንተና ሂደቶች እና ለርዕደ መሬት መቋቋም የሚያስፈልጉ ዝርዝር መስፈርቶችን ይዟል።
* EBCS-9፡ የሕንፃዎች የፕላምቢንግ አገልግሎቶች
የውሃ አቅርቦት ሥርዓቶች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የቆሻሻ ውሃ አወጋገድ፣ የዝናብ ውሃ ፍሳሽ፣ ሴፕቲክ ታንኮች፣ ሶክአዌይ ጉድጓዶች (Soakaway Pits) እና ተያያዥ የፕላምቢንግ ሥራዎችን ያካትታል።
* EBCS-10፡ የሕንፃዎች የኤሌክትሪክ ተከላዎች
የኤሌክትሪክ ሽቦ ሥርዓቶች፣ የመከላከያ መሣሪያዎች፣ አርቲንግ (Earthing/Grounding)፣ የኤሌክትሪክ ደህንነት እና በሕንፃዎች ውስጥ የኃይል ስርጭትን ይወስናል።
* EBCS-11 እስከ EBCS-13፡ የሕንፃ አገልግሎቶች
የሕንፃ ሜካኒካል አገልግሎቶች፣ የአየር ማናፈሻ (Ventilation) ሥርዓቶች፣ የአካባቢ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የእሳት መከላከያ መስፈርቶችን ይዳስሳል።
* EBCS-14፡ በህንፃ ግንባታ ውስጥ ጤና እና ደህንነት
የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት፣ የአደጋ መለያየት፣ የደህንነት ምልክቶች፣ የግል መከላከያ መሣሪያዎች (PPE) እና ደህንነቱ የተጠበቀ የግንባታ ሥራ ሂደቶችን ይወስናል።
⏺ከዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች ጋር መጣጣም
⏺ኢትዮጵያ የህንፃ ስታንዳርዶቿን ከዓለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው ኮዶች ጋር በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርዶች (Eurocodes) እና ከISO ስታንዳርዶች ጋር በማጣጣም ላይ ትገኛለች። እነዚህ የተጣጣሙ ስታንዳርዶች ብዙ ጊዜ እንደ (ES EN) በመታተም የአገሪቱን የምህንድስና ሥራ ከዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ያስማማሉ።
ይህ መጣጣም የሚያስገኘው ጥቅም፦
* የመዋቅር ደህንነትና አስተማማኝነት መሻሻል።
* በግንባታ ውስጥ የጥራት ማረጋገጫ መጠናከር።
* ከዓለም አቀፍ የምህንድስና እና የግንባታ ልምዶች ጋር የተሻለ ተኳሃኝነት መፍጠር።
* ለአካባቢያዊ እና ሴይስሚክ አደጋዎች የተሻለ መቋቋም መቻል።
https://t.me/ethioengineers1
❤18👍6💯1
⭐️Triaxial Shear Force
⚡️ማለት አንድ የአፈር ወይም የድንጋይ ናሙና ከሦስቱም አቅጣጫዎች ጫና (Pressure) እያረፈበት ባለበት ሁኔታ፣ በውስጡ የሚፈጠረው የመንሸራተት ኃይል ነው።
በተፈጥሮ ውስጥ አፈር ከመሬት በታች ሲሆን ከሁሉም አቅጣጫ በዙሪያው ባለው አፈር ተጨኖ (Confined ሆኖ) ነው የሚኖረው። ይህንን ተፈጥሯዊ ሁኔታ በቤተ-ሙከራ (Lab) ውስጥ ለመምሰል Triaxial Test የሚባል ምርመራ ይደረጋል፦
የከበበ ጫና (Confining Pressure ) የአፈሩ ናሙና ውሃ ባለበት ሲሊንደር ውስጥ ይገባና ከሁሉም አቅጣጫ እኩል የሆነ ፈሳሽ ጫና እንዲያርፍበት ይደረጋል (ይህ አፈሩ ከመሬት በታች ያለውን ሁኔታ ይወክላል)።
ቀጥተኛ ጫና (Axial Load )
በመቀጠል ናሙናው ላይ ከላይ ብቻ ተጨማሪ ኃይል ይጫናል። ውጤቱ (Shear Failure) ከላይ የሚመጣው ጫና እየጨመረ ሲሄድ፣ አፈሩ ጫናውን መቋቋም አቅቶት በሰያፍ (በአግድም አቅጣጫ) ይንሸራተታል። ይህ እንዲንሸራተት የሚያደርገው ኃይል Triaxial Shear Force ይባላል።
⚡️ለምን ይጠቅማል? (አስፈላጊነቱ)
የሲቪል መሐንዲሶች ይህንን ምርመራ እና ኃይል የሚያጠኑት ለሚከተሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው
1,የሕንፃ መሠረት (Foundation) ጥንካሬን ለማወቅ
2,መሬቱ የተሰራበትን ሕንፃ ክብደት መሸከም ይችል እንደሆነ ወይም አፈሩ ተሸርሽሮ ሕንፃው ሊሰምጥ እንደሚችል ለማረጋገጥ
3,የመሬት መንሸራተትን (Slope Stability) ለመከላከል
4, በተራራማ ቦታዎች ላይ መንገድ ሲሰራ ወይም ግድብ ሲገነባ የመሬት መንሸራተት አደጋ እንዳይከሰት
5,የግድቦች (Dams) እና የመንገዶች ደህንነት ግድቡ የያዘውን ከፍተኛ የውሃ ግፊት አፈሩ መቋቋም መቻሉን ለማረጋገጥ።

❤7👍3👌1
⭐️Differential Settlement
ይህንን ታሪክ በሳይት ላይ ብዙ ጊዜ ታየዋለህ። ሕንፃው ይጠናቀቃል፣ ርክክብ ይደረጋል፣ ባለቤቱም ይገባበታል። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ግን በር መዝጋት ይከብዳል፤ ከግድግዳው ጥግም ቀጭን ስንጥቅ ይታያል። ብዙዎች ይህንን የ finishing ችግር አድርገው ያልፉታል፤ አንተም እንደዚያ ልታስብ ትችላለህ። እውነተኛው መንስኤ ግን ከመሬት በታች፣ ከ footingህ ሥር ተደብቋል።
ታዲያ ከመሬት ሥር ምን ይሆናል? የመዋቅርህ ጭነት ከመሬቱ የመሸከም አቅም ጋር ሲገናኝ አፈሩ በጊዜ ሂደት መጨመቁ አይቀርም። Settlement ማለት ሕንፃህ subgrade ላይ ሲያርፍ የሚከሰት ቋሚ ወደ ታች የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ይህ እንቅስቃሴ በአንድ ጊዜ አይጠናቀቅም፤ እንደ ሦስት ተከታታይ ምዕራፎች በጊዜ ሂደት ይገለጣል።
መጀመሪያ የሚመጣው immediate settlement ነው። ጭነቱን እንደጫንክ፣ የእርጥበት ለውጥ ሳይኖር ወዲያውኑ ይፈጠራል። ይህ የሚሆነው በግንባታው ወቅት ነው፤ ብዙ ጊዜም ሳይታወቅ ያልፋል።
ከዚያ በኋላ ግን እንቅስቃሴው አያቆምም። በውኃ በተሞላ fine-grained clay ውስጥ ጭነቱ ወደ pore water ይተላለፋል፤ ውኃው ቀስ በቀስ እየወጣ excess pore-water pressure ሲቀንስ አፈሩ ይጨመቃል። ይህ primary consolidation ነው፤ ለወራት አንዳንዴም ለዓመታት ይቀጥላል። ሕንፃህ ተጠናቆ ሰው ከገባበት በኋላ እንኳ መንቀሳቀሱን የሚቀጥለው በዚህ ምክንያት ነው።
በመጨረሻም consolidation ሲጠናቀቅ እንኳ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አይቆምም። Effective stress ሳይለወጥ፣ የአፈሩ አጽም (soil skeleton) ቀስ በቀስ እየተስተካከለ የሚፈጥረው secondary compression (creep) ይቀጥላል።
እነዚህ ሦስቱ ምዕራፎች በሕንፃህ footprint ሁሉ ላይ በእኩል ቢከሰቱ፣ መዋቅርህ ከፍተኛ ውስጣዊ ጭንቀት ሳይደርስበት እንቅስቃሴውን ሊቋቋም ይችላል። አደጋው የሚጀምረው differential settlement ሲከሰት ነው። የ subgrade አለመመጣጠን ወይም የጭነት ስርጭት ልዩነት አንዱን የሕንፃህ ክፍል ከሌላው ቀድሞ ወይም ይበልጥ ጥልቀት እንዲሰምጥ ሲያደርግ፣ የመዋቅርህ grid ከባድ angular distortion ይደርስበታል።
ከዚያ በኋላ ያለው ሂደት ዝም ብሎ የሚሄድ ነው። ይህ distortion በ beams እና columns ላይ ያልታሰቡ secondary bending moments ይፈጥራል፤ በ masonry infill እና partition walls ላይ ደግሞ አደገኛ diagonal shear cracks ያስከትላል። ግንባታው ካለቀ ከዓመታት በኋላም elevator shafts ያጣምማል፣ በሮችን ያጨናንቃል፣ ጠንካራና የማይታጠፉ utility connections ይበጥሳል።
ከዚህ ሁሉ የባሰው ደግሞ ጉዳቱ ከተከሰተ በኋላ መጠገኑ ነው። ስንጥቅን በ plaster መለጠፍ ምልክቱን ይሸፍናል እንጂ መንስኤውን አያስወግድም፤ ከሥር ያለው መሬት መንቀሳቀሱን እስካላቆመ ድረስ ስንጥቁ ተመልሶ ይከፈታል። ስለዚህ እውነተኛው መፍትሄ ከመጀመሪያው ይጀምራል፤ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት ባለው የ geotechnical investigation ላይ።
መሬቱን ከአንድ ነጥብ ብቻ ሳይሆን ከሕንፃህ footprint ተለያዩ ቦታዎች አጥና፤ ምክንያቱም በአንድ ቦታ ላይ ያለው ጠንካራ አፈር ከጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ያለውን ለስላሳ clay አይወክልም። ከዚያም ጭነቱ በ footings መካከል በተቻለ መጠን ተመጣጥኖ እንዲሰራጭ አድርግ። አፈሩ ከቦታ ቦታ የሚለያይ ከሆነ ደግሞ ሁሉንም footings አንድ ዓይነት አድርጎ መድገም ሳይሆን፣ እንደ ሁኔታው ሌሎች አማራጮችን (ለምሳሌ foundation ዓይነትን መቀየር ወይም ክፍሎቹን በ settlement joint መለየት) ከስትሩክቸራል መሐንዲስህ ጋር ተወያይተህ መመዘን ይኖርብሃል።
ሕንፃ ሲሰምጥ የሚጎዳው የሚታየው ክፍል ነው፤ መንስኤው ግን ሁልጊዜ ከሥር ይጀምራል። ስለዚህ ከመሬት በታች ያለውን ከመሬት በላይ ከሚታየው በፊት አጥና።
https://t.me/ethioengineers1
⚡️ሕንፃህ በጠቅላላ በእኩል ቢሰምጥ መዋቅርህ ሊተርፍ ይችላል።
ችግሩ የሚጀምረው አንድ ማዕዘን ብቻ ከሌሎቹ ቀድሞ መስመጥ ሲጀምር ነው። በዚያች ቅጽበት የኮንክሪት ፍሬምህ ላይ angular distortion ይፈጠራል፤ በ masonry ግድግዳዎችህና በ beams ላይም diagonal shear cracks መታየት ይጀምራሉ።
ሕንፃህ በጠቅላላው ምን ያህል እንደሰመጠ ብዙ ጊዜ ዋናው ጉዳይ አይደለም፤ ሕንፃን የሚገነጣጥለው በክፍሎቹ መካከል ያለው የመስመጥ ልዩነት ነው፤ እሱም differential movement/settlement ይባላል!ይህንን ታሪክ በሳይት ላይ ብዙ ጊዜ ታየዋለህ። ሕንፃው ይጠናቀቃል፣ ርክክብ ይደረጋል፣ ባለቤቱም ይገባበታል። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ግን በር መዝጋት ይከብዳል፤ ከግድግዳው ጥግም ቀጭን ስንጥቅ ይታያል። ብዙዎች ይህንን የ finishing ችግር አድርገው ያልፉታል፤ አንተም እንደዚያ ልታስብ ትችላለህ። እውነተኛው መንስኤ ግን ከመሬት በታች፣ ከ footingህ ሥር ተደብቋል።
ታዲያ ከመሬት ሥር ምን ይሆናል? የመዋቅርህ ጭነት ከመሬቱ የመሸከም አቅም ጋር ሲገናኝ አፈሩ በጊዜ ሂደት መጨመቁ አይቀርም። Settlement ማለት ሕንፃህ subgrade ላይ ሲያርፍ የሚከሰት ቋሚ ወደ ታች የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ይህ እንቅስቃሴ በአንድ ጊዜ አይጠናቀቅም፤ እንደ ሦስት ተከታታይ ምዕራፎች በጊዜ ሂደት ይገለጣል።
መጀመሪያ የሚመጣው immediate settlement ነው። ጭነቱን እንደጫንክ፣ የእርጥበት ለውጥ ሳይኖር ወዲያውኑ ይፈጠራል። ይህ የሚሆነው በግንባታው ወቅት ነው፤ ብዙ ጊዜም ሳይታወቅ ያልፋል።
ከዚያ በኋላ ግን እንቅስቃሴው አያቆምም። በውኃ በተሞላ fine-grained clay ውስጥ ጭነቱ ወደ pore water ይተላለፋል፤ ውኃው ቀስ በቀስ እየወጣ excess pore-water pressure ሲቀንስ አፈሩ ይጨመቃል። ይህ primary consolidation ነው፤ ለወራት አንዳንዴም ለዓመታት ይቀጥላል። ሕንፃህ ተጠናቆ ሰው ከገባበት በኋላ እንኳ መንቀሳቀሱን የሚቀጥለው በዚህ ምክንያት ነው።
በመጨረሻም consolidation ሲጠናቀቅ እንኳ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አይቆምም። Effective stress ሳይለወጥ፣ የአፈሩ አጽም (soil skeleton) ቀስ በቀስ እየተስተካከለ የሚፈጥረው secondary compression (creep) ይቀጥላል።
እነዚህ ሦስቱ ምዕራፎች በሕንፃህ footprint ሁሉ ላይ በእኩል ቢከሰቱ፣ መዋቅርህ ከፍተኛ ውስጣዊ ጭንቀት ሳይደርስበት እንቅስቃሴውን ሊቋቋም ይችላል። አደጋው የሚጀምረው differential settlement ሲከሰት ነው። የ subgrade አለመመጣጠን ወይም የጭነት ስርጭት ልዩነት አንዱን የሕንፃህ ክፍል ከሌላው ቀድሞ ወይም ይበልጥ ጥልቀት እንዲሰምጥ ሲያደርግ፣ የመዋቅርህ grid ከባድ angular distortion ይደርስበታል።
ከዚያ በኋላ ያለው ሂደት ዝም ብሎ የሚሄድ ነው። ይህ distortion በ beams እና columns ላይ ያልታሰቡ secondary bending moments ይፈጥራል፤ በ masonry infill እና partition walls ላይ ደግሞ አደገኛ diagonal shear cracks ያስከትላል። ግንባታው ካለቀ ከዓመታት በኋላም elevator shafts ያጣምማል፣ በሮችን ያጨናንቃል፣ ጠንካራና የማይታጠፉ utility connections ይበጥሳል።
ከዚህ ሁሉ የባሰው ደግሞ ጉዳቱ ከተከሰተ በኋላ መጠገኑ ነው። ስንጥቅን በ plaster መለጠፍ ምልክቱን ይሸፍናል እንጂ መንስኤውን አያስወግድም፤ ከሥር ያለው መሬት መንቀሳቀሱን እስካላቆመ ድረስ ስንጥቁ ተመልሶ ይከፈታል። ስለዚህ እውነተኛው መፍትሄ ከመጀመሪያው ይጀምራል፤ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት ባለው የ geotechnical investigation ላይ።
መሬቱን ከአንድ ነጥብ ብቻ ሳይሆን ከሕንፃህ footprint ተለያዩ ቦታዎች አጥና፤ ምክንያቱም በአንድ ቦታ ላይ ያለው ጠንካራ አፈር ከጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ያለውን ለስላሳ clay አይወክልም። ከዚያም ጭነቱ በ footings መካከል በተቻለ መጠን ተመጣጥኖ እንዲሰራጭ አድርግ። አፈሩ ከቦታ ቦታ የሚለያይ ከሆነ ደግሞ ሁሉንም footings አንድ ዓይነት አድርጎ መድገም ሳይሆን፣ እንደ ሁኔታው ሌሎች አማራጮችን (ለምሳሌ foundation ዓይነትን መቀየር ወይም ክፍሎቹን በ settlement joint መለየት) ከስትሩክቸራል መሐንዲስህ ጋር ተወያይተህ መመዘን ይኖርብሃል።
ሕንፃ ሲሰምጥ የሚጎዳው የሚታየው ክፍል ነው፤ መንስኤው ግን ሁልጊዜ ከሥር ይጀምራል። ስለዚህ ከመሬት በታች ያለውን ከመሬት በላይ ከሚታየው በፊት አጥና።
https://t.me/ethioengineers1
👍8❤5
Vacancy Announcement
1. Junior Structural Engineer (Civil Engineering)
Vacancies: 2
Qualification: BSc Degree in Civil Engineering — Fresh Graduates.
Key Requirements:
Fundamental knowledge of structural design and engineering principles.
Basic practical/academic experience with ETABS and SAFE modeling software.
2. Junior Office / Site Engineer (COTM)
Vacancies: 2
Qualification: BSc Degree in Construction Technology & Management (COTM) — Fresh Graduates.
Key Requirements:
Strong foundation in Quantity Surveying (Take-offs & BOQ preparation).
Good understanding of project documentation and site management principles.
Application Details:
Deadline: November 8/2026
How to Apply: Send your CV, cover letter, and temporary degree/documents to [Telegram Link].@Belay_Ceng

❤5