Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
What Made Me Start? My Story, Experiences & Motivation ለምን ጀመርኩ? | የእኔ ታ...
https://youtube.com/watch?v=4_41QhKEYT8&si=pdpjPh6GbizKkYDS

YouTube
What Made Me Start? My Story, Experiences & Motivation ለምን ጀመርኩ? | የእኔ ታሪክ እና ተነሳሽነት
#Structural Design#Engineering#Software#Etabs#Sap#Safe#Detailing#Eurocode#EBCS
❤1
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
🎉 የመጀመሪያው ቪዲዮችን በይፋ ተለቋል!
ሰላም ውድ የምህንድስና ቤተሰቦች!
በገባነው ቃል መሠረት፣ የትምህርታዊ ጉዞአችን መነሻ የሆነው የመጀመሪያው ቪዲዮ አሁን በቻናላችን ላይ ይገኛል! ይህ ቪዲዮ ወደፊት አብረን ለምናከናውናቸው ትልልቅ ስራዎች መግቢያ እና መነሻ የሚሆን ነው።
ይህ የዩቲዩብ ቻናል በቀጣይነት እና በትጋት የምንቀጥልበት፣ የምህንድስና እውቀታችንን እና ልምዳችንን በተግባር የምናሳድግበት የጋራ መድረካችን ነው።
በቀጣይ በተከታታይ ምን ይጠብቃችኋል?
በጥልቀት የተዘጋጁ ተግባራዊ ቪዲዮዎች፡ በሶፍትዌሮች አሰራር ላይ የሚያተኩሩ ዝርዝር ትምህርቶች።
የቀጥታ ስርጭት ውይይቶች (Live Sessions)፡ የዲዛይን ጥያቄዎቻችሁን በቀጥታ የምንመልስበት እና የምንወያይበት መድረክ።
የባለሙያ እይታዎች እና የልምድ ፡ በተግባራዊ የሕንጻ መዋቅር ዲዛይን እና ማማከር (Structural Engineering & Consulting) ዙሪያ ያሉ የብዙ ዓመታት ተሞክሮዎች።
ተከታታይነት (Consistency)፡ ሳታቋርጡ አዳዲስና ጠቃሚ ይዘቶችን አዘውትረው ያገኛሉ።
📌 አሁኑኑ የመጀመሪያውን ቪዲዮ ይመልከቱ፣ አሳባችሁንም ኮመንት ላይ ያጋሩን!
👉 Subscribe ማድረጎን እና አዳዲስ ቪዲዮዎች ሲወጡ ወዲያውኑ እንዲደርሶት የደወል ምልክቷን ማብራታችሁን እንዳትረሱ!
ለሌሎች መሐንዲስ ጓደኞቻችሁም share በማድረግ የዚህ ጠቃሚ ጉዞ አካል አድርጓቸው። አብረን እንማራለን፣ አብረን እናድጋለን!

❤16👍1
SMH General Construction pinned «What Made Me Start? My Story, Experiences & Motivation ለምን ጀመርኩ? | የእኔ ታ... https://youtube.com/watch?v=4_41QhKEYT8&si=pdpjPh6GbizKkYDS»
🚨 አዲስ ቪዲዮ ዛሬ ይለቀቃል!
"Stop Modeling in ETABS Until You Master Eurocode 0 & 1!"
በ ETABS፣ SAP2000 እና SAFE ላይ ሞዴሊንግ ከመጀመራችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ የ Eurocode 0 & 1 መሠረታዊ ህጎች በስፋት ተዳስሰዋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
EC0: Combination factors (ψ) እና የ Design load combinations አሰራር
EC1: Superdead load፣ Live load እና Wind load calculation
📌 የላቀ የምህንድስና እውቀት እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ Subscribe ያድርጉ! የደወል ምልክቷን በመጫን አዳዲስ ትምህርቶችን የመጀመሪያው ሆነው ይከታተሉ። 👇
https://www.youtube.com/channel/UCMlfFIhWpRFUAciFvAwiMdQ

🙏3❤1
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
❤3
🪜 በደረጃ ኮንክሪት ስራ (Staircase Reinforcement & Formwork Preparation) ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች!
በምስሉ ላይ እንደሚታየው የህንፃ ደረጃ ኮንክሪት ከመፍሰሱ በፊት የታችኛው ሰሌዳ (Waist Slab) እና የእርምጃዎቹ (Risers & Treads) የብረት እና የእንጨት ፎርምወርክ (Shuttering) ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል።
📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት እና ለደህንነት ቁጥጥር ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
1️⃣ የፎርምወርክ እርጋታ እና ድጋፍ (Formwork & Scaffolding Support): የደረጃው የእንጨት ፎርምወርክ ከስር የተደገፈበት ፕሮፕስ/ስካፎልዲንግ የኮንክሪቱን ክብደት እና የተሰሩትን ሰራተኞች ንዝረት መቋቋም የሚችል ጠንካራ መሆኑን ማረጋገጥ።
2️⃣ የብረት አሰራር እና ማደራረብ (Waist Slab & Landing Rebar Detail): የደረጃው ዋና ብረቶች (Main Bars) እና የማቋረጫ ብረቶች (Distribution Bars) በዲዛይኑ መሠረት መታሰራቸውን፣ እንዲሁም ደረጃው ከወለሉ/ላንዲንግ (Landing) ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ ተገቢው የብረት መቆላለፍ (Development Length / Anchorage) መኖሩን ማረጋገጥ።
3️⃣ የኮንክሪት ከቨር (Concrete Cover Spacers): በብረቱ እና በፎርምወርኩ መካከል ተገቢው የኮንክሪት ከቨር (ከ 2.5cm - 3cm) እንዲኖር የስፔሰር ፓድ (Concrete Spacer Blocks) ማድረግ፤ ይህ ካልሆነ ብረቱ ከስር ክፍት ሆኖ ለዛግ ይጋለጣል።
4️⃣ የደረጃዎች እኩልነት እና ጽዳት (Step Dimensions & Cleaning): የካፕ/ራይዘር (Riser) እንጨቶች እኩል ከፍታ እና ስፋት መያዛቸውን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ኮንክሪት ከመፍሰሱ በፊት በደረጃው ውስጥ ያሉ የጥራብ/የእንጨት ፍቅፋቂዎችን እና ቆሻሻዎችን በደንብ ማጽዳት።
https://t.me/ethioengineers1

❤12👍2
Structural Design with Eurocode 2 & 8: Key Properties & Seismic Design: ...
https://youtube.com/watch?v=hXfzKZlqJLU&si=2u_xs9sqWH7xm7gY

👍6❤3
📍 VACANCY ANNOUNCEMENT: RESIDENT CIVIL ENGINEER
We are seeking qualified and experienced engineering professionals to join our team.
Position: Resident Civil Engineer
Total Openings: 8 Positions
Experience Required: Minimum 8 Years
Salary: 60,000+ ETB (Negotiable based on experience)
If you meet the requirements, send your CV on Telegram to @Belay_Ceng

👏5❤4
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
📢 VACANCY UPDATE: RESIDENT CIVIL ENGINEER
Thank you to everyone who applied! We have received an overwhelming response with over 120+ CVs submitted for the Resident Civil Engineer position.
Status: Applications are temporarily paused so our team can thoroughly filter and evaluate all submitted resumes.
Next Steps: If we do not find all required candidates from this current pool, we will share an immediate update right here.
Stay Tuned: We will be sharing more job opportunities and project updates on this channel soon. keep your notifications turned on!

❤13
SMH General Construction pinned «Structural Design with Eurocode 2 & 8: Key Properties & Seismic Design: ... https://youtube.com/watch?v=hXfzKZlqJLU&si=2u_xs9sqWH7xm7gY»
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
YouTube
Torsionally Flexible Building in Eurocode 8: How to Set q - Factor & Check Modal Mass
Once your building is classified as torsionally flexible, you cannot proceed with a standard behavior factor ($q$). In this tutorial, we cover the exact next steps under Eurocode 8 (EN 1998-1) to adjust your design parameters, evaluate structural regularity…
❤2👏1
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች! እስካሁን የተለቀቁትን 4 ጠቃሚ ቪዲዮዎች ይመልከቱ፡ Structural Design Check List ላይ መሠረት በማድረግ
🔹Eurocode 0 & 1: የዲዛይን መሠረቶች እና የጭነት (Actions) ማብራሪያ
🔹Eurocode 2 & 8: Concrete & Sesmic ዲዛይን
🔹Torsional Test: Torsion Test ሂደት
🔹Behavior Factor: የ q-factor አወሳሰን ዘዴ
በቀጣይ የሚቀርቡ፡ በ Structural Design፣ በ Quantity Surveying፣ በ Site Experience እና በሌሎች የሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፎች ላይ የላቁ ትምህርቶች ይኖሩናል።
ቻናሉን ለማሳደግ፡Subscribe፣ Like እና Share ያድርጉ፤ ጥያቄና አስተያየትዎን በ Comment ያካፍሉን! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCMlfFIhWpRFUAciFvAwiMdQ
🔹Eurocode 0 & 1: የዲዛይን መሠረቶች እና የጭነት (Actions) ማብራሪያ
🔹Eurocode 2 & 8: Concrete & Sesmic ዲዛይን
🔹Torsional Test: Torsion Test ሂደት
🔹Behavior Factor: የ q-factor አወሳሰን ዘዴ
በቀጣይ የሚቀርቡ፡ በ Structural Design፣ በ Quantity Surveying፣ በ Site Experience እና በሌሎች የሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፎች ላይ የላቁ ትምህርቶች ይኖሩናል።
ቻናሉን ለማሳደግ፡Subscribe፣ Like እና Share ያድርጉ፤ ጥያቄና አስተያየትዎን በ Comment ያካፍሉን! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCMlfFIhWpRFUAciFvAwiMdQ
👍3❤2
🎉 New Year, Advanced Content! 🚀
As part of our new year plan, we are launching in-depth, practical lessons across essential Civil Engineering disciplines,including Structural Design, Quantity Surveying, Project Planning & Contract Administration, Highway & Bridge Engineering, Practical Site Experience, and much more!
🌐 Language Update: To serve our growing community, tutorials will now also be delivered in English!
Help Us Grow: 🔔 Subscribe, Like & Share 💬 Leave your questions and suggestions in the comments below! 👇https://www.youtube.com/channel/UCMlfFIhWpRFUAciFvAwiMdQ

👍2
📌 የሳይት ምልከታና የኢንጂነሪንግ ጥያቄ፦ በቅርብ ጊዜ በፒያሳ ገዳም ሰፈር አካባቢ ህንፃዎች ላይ ያየሁት የፋውንዴሽን ስህተት!
በቅርቡ በፒያሳ ገዳም ሰፈር አካባቢ በሚገነቡ ህንፃዎች ላይ የታዘብኳቸውን ሁለት ዋና ዋና የኮንስትራክሽን ስህተቶች አስመልከቶ ከወገኖቼ ለቀረበልኝ ጥያቄ ሙያዊ ምላሽ እንደሚከተለው አዘጋጅቼዋለሁ። በተለይ በከተማችን እየተስፋፉ ባሉ ግንባታዎች ላይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይደገሙ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ነጥብ ነው።
1️⃣ በአንድ ጊዜ 2 ሜትር selected material ሞልቶ ኮምፓክት ማድረግ ትክክል ነው? ወደፊትስ ህንፃው ላይ ምን ይፈጠራል?
❌ ስህተቱ፦ ይህ አሰራር ፍጹም ስህተትና የኮንስትራክሽን ስታንዳርድን የጣሰ ነው። የኮምፓክሽን መሣሪያዎች (Plate compactor ወይም Rammer) አፈርን በጥራት ማጠባበቅ የሚችሉት ቢበዛ ከ15cm እስከ 20cm (ከፍተኛው 30cm) በሚደርስ ንብርብር (layer) ብቻ ነው። በአንድ ጊዜ 2 ሜትር አፈር ተሞልቶ ከላይ ብቻ ሲረገጥ ከሥር ያለው አፈር ሳይጠብቅ ክፍተት (air voids) እንደያዘ ይቀራል።
⚠️ ወደፊት የሚፈጠረው አደጋ፦
Differential Settlement (እኩል ያልሆነ የመስመጥ አደጋ)፦ ህንፃው ተገንብቶ ሲያልቅና የክብደት ጫና ሲያርፍበት፣ ሳይጠብቅ የቀረውን 2 ሜትር አፈር እየተጫነውና እያሰመጠው ይሄዳል።
የግድግዳና የስትራክቸር ስንጣቂ፦ የመሬት ወለል (Ground Slab) መስመጥ፣ የወለል ሴራሚክስ መነሳት፣ ግድግዳዎችና Beam/Column አካባቢ Structural Cracks እንዲፈጠሩ ያደርጋል።
2️⃣ foundation ውስጥ ውሃ ሳይወጣ አፈር መሙላትና የእንጨት ትራሶች (Formwork) ሳይነሱ መቅበር ምን ችግር ያመጣል?
🌊 ውሃ ሳይወጣ አፈር መሙላት፦
አፈር ከውሃ ጋር ሲደባለቅ ወደ Mud/Slurry (ጭቃ) ይቀየራል። የውሃ መጠኑ ከፍ ስለሚል (Optimum Moisture Content ስላበቃ) ምንም ዓይነት የኮምፓክሽን ጥራት አይኖረውም።
አፈሩ የመሸከም አቅሙን (Bearing Capacity) ያጣል። ውሃው በሂደት ሲደርቅና ሲተን አፈሩ ኮላፕስ በማድረግ ከፍተኛ የመስመጥ አደጋ ያጋጥማል።
መፍትሔው፦ ውሃውን በፓምፕ (Dewatering Pump) ሙሉ በሙሉ አውጥቶ፣ የታችኛውን ጭቃ ካጸዱ በኋላ ብቻ በንብርብር መሙላት ነበረበት።
🪵 የእንጨት ግንድላ፣ ከረባትና ፎርምወርክ ሳይነሱ ከPad ዙሪያ መቀበር፦
የእንጨት መበስበስ (Wood Decay)፦ አፈር ውስጥ የቀረ እንጨት በእርጥበትና በባክቴሪያ ምክንያት ከጊዜ በኋላ ይበሰብሳል።
ትላልቅ ክፍተቶች መፈጠር (Void Creation)፦ እንጨቱ በስብሶ ሲጠፋ በPad ዙሪያ ትላልቅ ባዶ ክፍተቶች ይቀራሉ።
የፋውንዴሽን መንሸራተት፦ የፓድ ፋውንዴሽን ዙሪያውን በደንብ ከተጠጠበቀ አፈር ድጋፍ (Lateral Support) ማግኘት አለበት። እንጨቱ በስብሶ ክፍተት ሲፈጥር ፓዱ የጎንዮሽ ድጋፍ አጥቶ የመንሸራተትና የመናጋት አደጋ ያጋጥመዋል።
💡 ማጠቃለያ፦
እነዚህ አይነት የሳይት ቁጥጥር ድክመቶች (Poor Site Supervision) የህንፃውን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ጥንካሬ አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው፣ በሳይት መሃንዲሱና በሱፐርቫይዘሩ አስቸኳይ የቴክኒክ ማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።
Via tadele Dandena

❤22👍6👌1