SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥ሲሚንቶ በቴሌብር……

⚡️ሲሚንቶ እንደ ነዳጅ ወደ ዲጅታል ግብይት ሊገባ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።ሂደቱ ሲሚንቶ በተተመነለት ዋጋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ፣ ስርጭቱ ከፋብሪካው ጀምሮ እስከ ተጠቃሚ ድረስ ያለውን ሰንሰለት ለመከታተል፣ የዘርፉን የግብይት ሥርዓት በማዘመን የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር እና ከህገወጥ ደላሎች የፀዳ የንግድ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያግዛል ተብሏል።

https://t.me/ethioengineers1
👍18
💥በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን‼️

📲
0953138434 / +251907374856 እትዮ ኮንስትራክሽን ብለው ይደውሉ ........

https://t.me/ethioengineers1
❤10👍4
💥Slab ዲዛይን ስናደርግ ስለምንጠቀማቸው ዲዛይን ሞመንት (Md),depth(d), compresive strength of concrete (fcu) እና tensile strength of Reinforcement bar(fyk). ትንሽ እንበል።

⚡️የኮንክሪት strength እየጨመረ በመጣ ቁጥር   depth እየቀነሰ ይመጣል።
ለምሳሌ C25 ተጠቅመን depth of deflection(d) ደግሞ

d≥(0.4+0.6(fyk/400)×le/Ba ወስደን
design እያደረግን እያለ እንበልና ከanalysis ያገኘነው  moment በጣም ትልቅ ሆነ።
ይህ ማለት concrete strength constant አድርገን እየሰራን ስለሆነ depth ትልቅ ይሆንብናል ማለት ነው።
ይኼውም ከanalysis የምናገኘው depth(d)
⚡️d≥√(md/(0.8fbfcdPmaxM(1-04PmaxM))
ይኼኛው depth እና ከላይ ስንነሳ የተጠቀምነው depth of deflection(d).
  d≥(0.4+0.6(fyk/400)×le/Ba ስናወዳድራቸው ከanalysis ያገኘነው depth ትልቅ ከሆነ redesign እናደርጋለን።
አንዳንድ ጊዜ ግን ከanalysis ያገኘነው moment ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ አሻሽለንም redesign ብናደርገው እንኳን depth ትልቅ ይሆንበንና design የምናደርገው building functional use እና architectural appearance ይረብሻል።
ይህንን ለመከላከል ታዲያ ከምንጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ የconcrete እና reinforcemnet bar Grade increase ማድረግ ነው  ።
ለምሳሌ  የconcrete  C-25 እና C30 ተጠቅመን እንይ፣
C-25
fcu =25mpa
fck=0.8×fcu=0.8×25=20mp
Using concrete factor of safety =1.5
fcd=0.85fck/1.5
=0.85×20/1.5=11.3mp
ይህንን fcd ተጠቅመን ያገኘነው depth
d≥√(Md/(0.8fbfcdPmaxm(1-04Pmaxm))
እና
C30
fcu=30mpa
fck=0.8×fcu=0.8×30=24mpa
fcd=0.85fck/1.5
=0.85×24/1.5=13.6mp
ማወዳደርና ማየት ነው።
For C-25→fcd=11.33mp
For C-30→fcd=13.6mp
.      C-40→"'.      
.
.
⚡️ከላይ ከፎርሙላው እንደምናየው depth እና design moment directly proportional ናቸው።

ያ ማለት design moment በጨመረ  ቁጥር depth ይጨምራል ማለት ነው።
በአንፃሩ ደግሞ የconcrete እና የreinforcement bar grade በጨመረ ቀጥር depth እየቀነሰ ይመጣል ማለት ነው።
ከዚህ የምንረዳው high rise building's large  load እና moment experience የሚያደርጉ ቢሆንም small section የሚጠቀሙት higher grade of  concret and reinforcement bar ተጠቅመው counterbalace በማድረግ መሆኑን ነው


https://t.me/ethioengineers1
👍48👏4🙏3😍3❤2🤔2
💥Deformed_bars

⚡️ከባለ 6mm ዲያሜትር ብረት በስተቀር አብዛኛው ብረቶች ዙሪያቸውን ribs አለባቸው፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት በኮንክሪቱና በብረቱ መሃል bond እንዲኖርና ሎድ እንዲተላለፍ ነው፡፡

⚡️በተጨማሪም ስትራክቸሩ deflect በሚያደርግበት ጊዜ ብረቱ ለብቻው ተንሸራቶ እስትራክቸሩ fail እንዳያደርግ ይጠቅማል፡፡ R.C. Structure ዲዛይን ስናረግ assume ከምናደርጋቸው ውስጥ “ THE Reinforcement is Subjected To The Same Variation In The Strain As The Adjacent Concrete “ የሚለው assumption  deformed bar እና development length በመጠቀማችን የተነሳ true ይሆናል::  


https://t.me/ethioengineers1
👍22🔥4❤2😍2
*ማስታወቂያ**

ከደረጃ 1  - 3 ለምትገኙ የማኅበራችን አባላት በሙሉ!

ማኅበራችን በ “Claims Management” ላይ የሚያተኩርና ተግባር ተኮር የሆነ ሥልጠና ለማዘጋጀት በማሰብ በኮንስትራክሽን ሕግ ሙያ ላይ የዳበረ ልምድና ዕውቀት ያላቸውን አቶ ዘውዱ ተፈራን በአሠልጣኝነት እንዲያገለግሉንና ሲቀጥልም ይህንኑ መስክ የተመለከተ የሥራ መመሪያ (Working Manual) እንዲያዘጋጁ አጠቃላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በቅድሚያ ግን በጉዳዩ ላይ አባላት ተገቢ የሆነ ግንዛቤ ያዳብሩ ዘንድ የሥልጠና መርኃ-ግብሩ እንዲቀድም ስለተግባባን ይህን ሥልጠና በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ለማዘጋጀትና ለመስጠት ስለታቀደ በሥልጠናው ለመካፈል ፍላጎቱ ያላችሁ አባሎቻችን በዚሁ የቴሌግራም ገፅ ላይ ፈቃደኝነታችሁን እንድታሳውቁን፣ የተሳታፊውን ሙያተኛ ስም እና የስልክ ቁጥር በማስፈርም እንድትተባበሩን እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

https://t.me/ethioengineers1
👍22❤1
በአዲስ አበባ የሲሚንቶ ዋጋን ለማረጋጋት የሚያግዙ ሁለት የሲሚንቶ ማከፋፈያ መጋዘኖች ተከፈቱ

በአዲስ አበባ የሚታየውን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋት የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ሁለት የሲሚንቶ ማከፋፈያ ዴፖ በለቡ መብራትና ጎሮ አካባቢ በመክፈት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መስከረም ባህሩ ተናገሩ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገበያውን ለማረጋጋት ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር በሚደረጉ ውይይቶች  ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች የራሳቸው ዴፖ ወይም መጋዘን እንዲኖራቸው ግፊት ሲያደረግ እንደነበር ያስታወሱት ወ/ሮ መስከረም ከዚህ ቀደም  ደርባ ሀበሻ እና ዳንጎቴ የራሳቸውን ዴፖ በመክፍት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ መሪ ስራ አስፈፃሚዋ አክለዋል፡፡

የኢስት አፍሪካ ትሬድንግ ሀውስ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አዳነ አለሙ  የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ዴፖን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት ተጠቃሚው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ያለማንም ጣልቃ ገብነት መግዛት እንዲችል የመጋዘኖቹ መከፈት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

መንግስት ባስቀመጠው የትርፍ ህዳግ መሰረት ለተጠቃሚው የሚቀርበው ሲሚንቶ 1320 ብር በኩንታል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ማንኛውም ሰው የግንባታ ፍቃዱን በማሳየት እስከ 35 ኩንታል ድረስ መግዛት የሚችል መሆኑን ምክትል ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
🤔8👍4❤1
💥የሲቪል 3D መማር ለብዙ ምክንያቶች አስፈላጊ ነው

⚡️በተለይ በሲቪል ምህንድስና ወይም ተዛማጅ መስኮች ሙያ ለመከታተል ፍላጎት ካሎት። ሲቪል 3D መማር አስፈላጊ የሆነባቸው አንዳንድ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡

1. ቀልጣፋ ንድፍ፡ ሲቪል 3D የሲቪል መሐንዲሶች ውስብስብ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በብቃት እንዲቀርጹ እና እንዲተነትኑ የሚያስችል ኃይለኛ የሶፍትዌር መሣሪያ ነው። የ3-ል ሞዴሎችን ለመፍጠር፣ መረጃን ለመተንተን እና ሪፖርቶችን ለማመንጨት  ይህም ጊዜን ይቆጥባል እና ትክክለኛነትን ያሻሽላል።

2. ትብብር፡ ሲቪል 3D ብዙ ተጠቃሚዎች በአንድ ፕሮጀክት ላይ በአንድ ጊዜ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል፣ ይህም በቡድን አባላት መካከል ትብብር እና ግንኙነትን ያሻሽላል። ይህ ሁሉም ሰው በአንድ ገጽ ላይ መሆኑን እና ፕሮጀክቱ በጊዜ እና በበጀት ውስጥ መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ይረዳል.

3. ቪዥዋልላይዜሽን፡ ሲቪል 3D መሐንዲሶች የዲዛይናቸውን 3D ሞዴሎችን እንዲፈጥሩ የሚያስችሏቸውን የእይታ መሣሪያዎችን ያቀርባል። ይህ ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቱን በዓይነ ሕሊናዎ እንዲመለከቱት እና በገሃዱ ዓለም እንዴት እንደሚታይ እንዲገነዘቡ ይረዳል።

4. ትንተና፡- ሲቪል 3D መሐንዲሶች ግንባታ ከመጀመሩ በፊት መረጃዎችን እንዲመረምሩ እና ሊፈጠሩ የሚችሉ ጉዳዮችን እንዲለዩ የሚያስችሉ የተለያዩ የትንታኔ መሳሪያዎችን ያቀርባል። ይህ ፕሮጀክቱ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ መሆኑን ለማረጋገጥ ይረዳል።

5. የኢንዱስትሪ ደረጃ፡- ሲቪል 3D በሲቪል ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ለሲቪል ምህንድስና ዲዛይን ሶፍትዌር የኢንዱስትሪ መስፈርት ተደርጎ ይወሰዳል። ሲቪል 3D መማር በሲቪል ምህንድስና እና ተዛማጅ የስራ መደቦች ላይ የበለጠ ተወዳዳሪ እጩ ያደርግዎታል።

በአጠቃላይ ሲቪል 3D መማር በሲቪል ምህንድስና ወይም በተዛማጅ ዘርፎች ሙያ ለመከታተል ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው አስፈላጊ ነው። በስራ ገበያ ውስጥ ቅልጥፍናን፣ ትብብርን፣ ምስላዊነትን፣ ትንተናን እና ተወዳዳሪነትን ለማሻሻል ይረዳል


መማር ለምትፈልጉ @BelayChane ‼️

https://t.me/ethioengineers1
👍25❤2😍1
💥ዘመን ባንክ አዲስ ያስገነባውን ባለ 36 ወለል ህንጻ የፊታችን ቅዳሜ ሊያስመርቅ መሆኑን አስታወቀ

⚡️ባንኩ ሜክሲኮ አካባቢ ያስገነባውን የዋና መስሪያ ቤቱ ህንጻ ቅዳሜ አስመርቃለሁ ያለ ሲሆን
ህንጻው የከተማዋን ገጽታ ከማስዋቡ በተጨማሪ የኪነ-ጥበብ ውበት ጎልቶ የታየበት ነው ተብሏል።

⚡️ህንፃው እስከ 1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ግንባታው 5 ዓመታት መፍጀቱ ተገልጿል።

⚡️የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ እጅግ ውብ ተደርጎ እንደተገነባና በርካታ አገልግሎቶች እንደሚሰጥ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ኤርሚያስ እሸቱ ተናግረዋል።

⚡️የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ደረጀ ዘበነ፣ ህንጻው ለባንኩ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲሰጥና ደንበኞች የላቀ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

⚡️እስከ 5ኛ ወለል ድረስ መኪና ማቆሚያ ያለው ህንጻው ከምድር በታች 3 ወለሎችም አሉት።


https://t.me/ethioengineers1
👍6❤5
💥Haunch bar
Haunch bar purpose is wider section but I can try to simple for you in short description

1. If a haunch bar is used in the bottom of the tank and other load-bearing structure from the side,then it will provide extra strength or retain shear from on the wall because the wall work like a cantilever

2.if haunch bar is used in corner of the tank and other structure I.e retaining wall then it’s will reduce the stress developed in the corner portion and carry more shear force

⚡️Haunch bar is used for :-
1. Improve share resistance
2. Avoid leakage
3.improve load caring capacity of side
4. Decrease pressure

⚡️Application of haunch bar

.Haunch bars in water tanks
.Retaining wall
.Box culverts
.Swimming pool
.Retaining structure elements in the dam


@ethioengineers1
👍16❤3🔥2
💥Why is the bending?

This is called a #joggle in technical term.

⚡️The bent is provided to overlap the column reinforcement and to keep in alignment in its dimension (column size )..... if we don’t bend the reinforcement at overlapping then the size of the column will increase when we go up.

⚡️So the point is TO MINIMIZE LOAD IN THE TOP AND TO REDUCE THE SIZE OF COLUMN ON THE WAY


https://t.me/ethioengineers1
👍14❤2
💥የ ህንፃ ስራ ሂደቶች

1.Foundation


*ፋውንዴሽን የሕንፃው በጣም አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡
*የግንባታ እንቅስቃሴ የሚጀምረው ለመሠረት መሬትን በመቆፈር እና ከዚያ በመገንባት ነው፡፡
*እሱ የሕንፃው የታችኛው ክፍል ነው።

2. plinth


በመሬት ደረጃ እና በመሬቱ ወለል መካከል ያለው የግድግዳ ክፍል ነው፡፡
*plinth  ብዙውን ጊዜ የድንጋይ ንጣፍ ስራ ነው።
*መሠረቱም በእንጨት ላይ ከሆነ ፣ከወለል ወለል በላይ ግድግዳውን ለመደገፍ አንድ ክፈፍ ጣውላ ይጣላል።
*በፕሌይ አናት ላይ እርጥብ ማረጋገጫ ኮርስ ይሰጣል፡፡
*እሱ ብዙውን ጊዜ ከ 75 ሚ.ሜ ውፍረት ያለው የኮንክሪት ኮርስ ነው ፡፡

3. Walls and columns


*የ wall እና የcolumn ተግባር የመሠረቱን ጭነት ወደ ታች  ለማስተላለፍ የህንፃውን ጭነት በአቀባዊ ወደ ታች ማስተላለፍ ነው ፡፡

4. Sill እና lintels የመስኮት ክፈፍ በቀጥታ ከማሽኑ ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡

*በመሬቱ ላይ ከ 50 ሚሊ ሜትር እስከ 75 ሚ.ሜ ውፍረት ያለው ተጨባጭ ኮንክሪት ኮርስ ይቀመጣል፡፡
*ይህ ኮርስ እንደ ሰል ይባላል Lintels R.C.C. ሊሆኑ ይችላሉ።
*የበሩ ወይም የመስኮት ክፈፉ ከልክ በላይ ጫና ያልተፈጠረ መሆኑን ለማየት በበሩ እና በመስኮቱ ክፍት ቦታዎች ላይ ጭኖቹን በማስተላለፍ ላይ የተቀረጹ የድንጋይ ንጣፎች ወይም የድንጋይ ንጣፎች።
*ለምሳሌ የአንድ ቤት ርዝመት 3ሜ ሊሆን ይችላል፡የአንድ በር ቁመት 2.10 ከሆነ 90 cm ከበሩ ወደላይ lintel beam ተጠቅመን wall መሥራት እንችላለን፡፡

5. Door & windows


-የበር ተግባር በህንፃው ውስጥ የተለያዩ ክፍሎች እንዲኖሩ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተደራሽነትን መካድ ነው፡፡
*በሮች ቁጥር በተቻለ መጠን ዝቅተኛ መሆን አለበት ፡፡ የበሩን ስፋት እንደ በር ሊጠቀም የሚችል ትልቁን ነገር እንቅስቃሴ የሚያመቻች መሆን አለበት ፡፡

6. Floors

ወለሎች የሕንፃ አስፈላጊ አካል ናቸው፡፡
*ለሰራተኞቹ የሥራ / ጠቃሚ አካባቢ ይሰጣሉ የመሬቱ ወለል የተገነባው  by filling brick bats, waste stones, gravel and well compacted እና በጥሩ ሁኔታ ከላይኛው ከ 100 ሚ.ሜ የማይበልጥ የአሸዋ ንብርብር በመሙላት ነው፡፡
*የ 1: 4: 8 ፣ 100 ሚሜ ውፍረት ያለው ተጨባጭ ኮንክሪት እንደ ምሣሌ ማየት ይቻላል፡፡
*በዚህ ላይ እርጥብ ማረጋገጫ ኮርስ ሊሰጥ ይችላል ፡፡

7.Roof


*ከፍታ ለህንፃው የላይኛው ሽፋን የሚሰጥ የህንፃው ከፍተኛ ክፍል ነው፡፡
*እንደ ጣሪያ እና እንደ ኤ.ሲ.ኤል. ወረቀት ያሉ ተንሸራታች ጣራ በቀላሉ የሚፈስ ሽፋን ይሰጣል። ነገር ግን ለተጨማሪ ወለል ግንባታ ዝግጅት አይሰጡም፡፡
*የታጠፈ ጣሪያ ጥሩ የሙቀት መከላከያ ይሰጣል፡፡
*ጠፍጣፋ ጣሪያዎች ለተጨማሪ ወለሎች አቅርቦት ይሰጣሉ ፡፡*terrace የነዋሪዎችን ምቾት ይጨምራል።
*የውሃ ታንኮች በቀላሉ ጠፍጣፋ ጣሪያዎቸ ላይ በቀላሉ ሊቀመጡ ይችላሉ ፡፡

8. step,stair,lift


-ደረጃዎች ከመሬት ወለል እስከ መሬት ወለል ደረጃ ምቹ ተደራሽነት ይሰጣሉ ፡፡ በውጭው ግድግዳ ላይ በሮች ያስፈልጋሉ ፡፡ ከ 250 እስከ 300 ሚ.ሜ ስፋት እና ከ 150 ሚ.ሜ ከፍታ ለደረጃዎች በጣም ጥሩ መጠን ነው ፡፡
*በምንም ዓይነት ሁኔታ ሁለት ተከታታይ ደረጃዎች መጠኑ የተለየ አይሆንም፡፡
*የሚፈለገው የእርምጃዎች ብዛት በመሬቱ እና በመሬቱ ደረጃዎች ልዩነት ላይ የተመሠረተ ነው።

9.Finishing


-የታችኛው ንጣፍ (ጣሪያ) ፣ ግድግዳዎች እና የወለል ንጣፍ ከፕላስተር ጋር ለስላሳ ማጠናቀሪያ ያስፈልጋቸዋል፡፡

10. የግንባታ አገልግሎቶች የውሃ አቅርቦት ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና ሥራዎች ፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ሥራ እና የመጠጥ ሰሌዳዎች ግንባታ እና የማሳያ ጉዳዮች ዋና የግንባታ አገልግሎቶች ናቸው፡፡

@ethioengineers1
👍37❤6👏2
1. How is a reinforcement bar in hardened concrete structure exposed to corrosion??
ሙሉ በሙሉ ጥንካሬውን ያገኘ የ ኮንክሪት ስትራክቸር ውስጥ ያለ ወይም የተሰራበት reinforcement bar እንዴት ሊዝግ ይችላል? በምን ምክንያቶችስ ሊሆን ይችላል?
⬇️
🚧3 መሰረታዊ የሆኑ ሁኔታዎች reinforcement ባራችንን በበቂ ሁኔታ ጥንካሬውን ባገኝ የ አርማታ ስትራክቸር ውስጥ ባለበት ሊያዝጉት ይችላሉ (corrosion እንዲፈጠር ሊያደርጉት ይችላሉ)

1,የመጀመሪያው carbonation ይባላል

:- እንደሚታወቀው concrete strongly alkaline nature አለው። ይህም የሆነበት ምክንያት Ca(OH)2 ስላለው። pH value ደግሞ about 13 ነው። 
:- due to this high alkalinity nature ኮንክሪቱ reinforcement ባሩን ከ corrosion ለመከላከል a thin passivating layer በባሩ ዙሪያ በመፍጠር ብረቱን ከዝገት ይከላከላል። ይህም process passivation በመባል ይታወቃል።
:- as we know CO2 በራሱ reactive አይደለም። ግን in the pressence of moisture( እርጥበት) ወደ dilute carbonic acid ይቀየራል። ከዛም concrete form ያደረገውን passivating layer መብላት ወይም ማፈራረስ ይጀምራል። በመጨረሻም PH value ን  ወደ 8.3 - 9 ያደርሰዋል። ልክ PH value ከ 11 ማነስ ሲጀምር ብረቱ በቀላሉ መዛግ ይጀምራል።

2,ሁለተኛው ደግሞ chloride attack ነው

:- በተመሳሳይ መንገድ ልክ carbonation passivating layer ን ማፈራረስ እንደሚችል chloride attack ም ያንን በበለጠ ማድረግ ይችላል።
:- chloride attack is more serious reason than any other
:- in the presence of water and oxygen, chloride can destroy the passivating layer and leads to corrosion.
:- chloride በቀላሉ ወደ ኮንክሪቱ ሊገባ ይችላል። ለምሳሌ በ cement,water,aggregate and sometimes from admixtures or from environment by diffusion.

3,ሶስተኛው በ electrochemical process ነው

:- ይሄኛው ደግሞ when there is a difference in electrical potential along the steel reinforcement in concrete.
:- ብረቱ ውስጥ አንደኛው part anode ሌላኛው part ደግሞ cathode ሲሆን ነው።

★ በስተመጨረሻም corrosion of reinforcement ለመከላከል ምን አይነት measurement መውሰድ እንዳለብን እንድትወያዩበት እጋብዛለው።

https://t.me/ethioengineers1
👍29🤔2❤1😍1
💥ADVANCE PAYMENT

⚡️በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል

1) ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
2)በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
3) ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።


@ethioengineers1
👍38❤5🙏3👏2
💥የሁለቱ ህንጻዎች ወግ
2.2ቢሊዮን Vs 1.7ቢሊዮን


⚡️የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የቢሮ ዕድሳት የፈጀው 2.2 ቢሊዮን ብር ሲሆን በዚህ ሳምንት ተጠናቆ የተመረቀው የዘመን ባንክ ባለ 37 ፎቅ ዘመናዊ ህንጻ ሙሉ ለሙሉ ተሰርቶ ለማጠናቀቅ አጠቃላይ የፈጀው 1.7 ቢሊዮን ብር ነው።

https://t.me/ethioengineers1
🤔82👍11❤4🙏2
💥በኮንስትራክሽን ውል አሰሪው የተቋራጩን ክፍያ አዘግይቶ መክፈል ጉዳይ/Delay payment/ 
    
ጉባዔ አሰፋ(Legal practitioner 09-75-576924) በናሽናል ኮንስትራክሽን መጋዚን የኮንስትራክሽን ህግ አምደኛ

# የኮንስትራክሽ ውል መሰረታዊ ባህሪው ሲታይ በዋናነት አሰሪና ተቋራጭን በተዋዋይነት የሚይዝ ሲሆን ጉልህ የሆነው ግዴታቸው ሲታይ ደግሞ ተቋራጩ በውሉና ዲዛይኑ/ስፔስፊኬሽኑ መሰረት ግንባታውን የማከናወን ሀላፊነት የሚኖርበት ሲሆን ክፍያ የመክፈል ጉዳይ ደግሞ ለአሰሪው ዋናውና ትልቁ ግዴታው ነው፡፡የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610፣3019እና 3020 እንዲሁም 3244 ተገናዝቦ ሲታይ ይሄን ሁኔታ ያስገነዝባል፡፡
# የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ "ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም" በሚል የተደነገገው በኮንስትራክሽን ውል ለተቋራጩ የሚከፈለው ክፍያ ጉዳይ የውሉ መሰረታዊ ነጥብ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ስለክፍያ አይነቶች የህጉን ጉዳይ ወደፊት በሌላ ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡
# አሰሪው ለተቋራጩ ክፍያ የመክፈሉን ሁኔታ ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት አይችልም፡፡
# አማካሪ መሀንዲሱ በተለይ ከተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ የማረጋገጥና የማጽደቁን ስራ በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(d) 
# አሰሪው መስሪያ ቤት ደግሞ በአማካሪ መሀንዲሱ የጸደቀ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(e) 
# አማካሪ መሀንዲሱ በተቋራጩ የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሰባት ቀናት ውስጥ የማረጋገጥና የማጽደቅ ስራ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*በዚህ ረገድ የመመሪያው አንቀጽ አንቀጽ 28.5(f) ግልጽ ምላሽ አስቀምጧል፡፡
*ይሄውም ተቋራጩ በዚህ ምክንያት ከአሰሪው ላይ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ የጠየቀ እንደሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ይህን ተጨማሪ ክፍያ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
*ሆኖም ግን አማካሪ መሀንዲሱ ለሚሰጠው አገልግሎት ከሚከፈለው ክፍያ በላይ የሆነ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነት አይኖርበትም፡፡
*በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636 የአማካሪ መሀንዲሱን የእውቀት ስራ ውል ግዴታ ይደነግጋል፡፡ይሄውም አማካሪው "የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሰሪው በኩል ስራ ተቋራጩን ሀላፊነት አይነካውም" በሚል ተቀምጧል፡፡(2636(2)) እንደዚሁም አማካሪው ሳይሰራ ከመቅረቱ የተነሳ ወይም በአሰሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ስራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል እንደሚችል የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636(3) ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ አማካሪው ክፍያ የማረጋገጥ እና የማጽደቅ ስራውን በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባለማከናወኑ አሰሪው ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል በተቋራጩ የተጠየቀ እንደሆነ አማካሪው አጥፊ ነው ሊባል ያስችለዋል ማለት ነው፡፡   
#አሰሪው በአማካሪው የጸደቀው የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14 ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*አሰሪው ያለበቂ ምክንያት ክፍያ ያዘገየ እንደሆነ ለተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ ለመክፈል ሀላፊነት እንደሚኖርበት የፌዴራል የግዥ መመሪያ/Federal public procurement directive/ አንቀጽ 28.5(g) ይደነግጋል፡፡
*ተጨማሪ ክፍያ ሲባልስ ምንን ያጠቃልላል? የሚለው ሲታይ በዋናነት ወለድ የመክፈል ሀላፊነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3268 ተቋራጩ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብት ይሰጠዋል፡፡የወለዱ መጠንም በውል ያልተወሰነ የሆነ እንደሆነ በአንቀጽ 1751 መሰረት ህጋዊ ወለድ በአመት 9(ዘጠኝ) በመቶ ሆኖ የሚሰላ ይሆናል፡፡
*ሌላው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ክፍያን ማዘግየት የሚኖረውን ውጤት አስመልክቶ የቅጣት ስምምነት/penality clause/ ያካተቱ ከሆነ የፍትሀብሄር ህጉ አንቀጽ 1889 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ እውቅና ስለሚሰጠው እና በአንቀጽ 1731 መሰረት ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ስለሚቆጠር ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
*አንዳንድ ክልሎችም በዚህ ረገድ በግዥ መመሪያቸው ላይ ዝርዝር ውጤቱን ያስቀምጣሉ፡፡
*አሰሪው ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ከወለድ ባለፈ ሌላም ጉዳት የደረሰበት ተቋራጭስ ከጉዳቱ ጋር እኩል የሆነ ኪሳራ ሊከፈለው አይገባም ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡ምክንያቱም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2091 እና 1790(2) ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ መሆኑ በህግ የታወቀ ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሳ ሀላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት በሚል በግልጽ ይደነግጋል፡፡    
#በአጠቃላይ አሰሪው በማናቸውም ምክንያት የተቋራጩን ክፍያ በሚያዘገይበት ጊዜ ተቋራጩን ለውድቀት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ምክንያቱም በሀገራችን አብዛኛው ተቋራጭ ድርጅት የፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስርአት የለውም፡፡ተቋራጮቻችን የገንዘብ አቅማቸውም ደካማ ነው፡፡አብዛኛው ተቋራጭ ለአንዱ ፕሮጀክት የሚወስደውን የቅድሚያ ክፍያ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ይጠቀምበታል፡፡በዚህ ምክንያት አንድ ተቋራጭ ሲከስር ብዙ ሰራተኛ እንደሚበተን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ በአሰሪዎች በኩል ተቋራጮች የሰሩበትን ክፍያ በወቅቱ እና በተሰራው ስራ ልክ አንዲከፈላቸው ለማድረግ እና በህጉ የተቀመጠው የክፍያ የጊዜ ገደብ እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም ወስዶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ 
                              


@ethioengineers1
👍25❤4👌1
💥ትኩረት

መገናኛ ከቦሌ ወደ ዲያስፖራ የሚያሸጋግረው መንገድ ላይ ያለው ድልድይ ያልታሰበ አደጋ ከማስከተሉ በፊት ጥገናና እና ወቅታዊ ክትትል ሊደረግለት ይገባል እንላለን።

Driving in addis

https://t.me/ethioengineers1
👍49👏3🙏1
💥የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/
                
 ⚡️የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡አንድ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡

⚡️ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡

⚡️ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡

⚡️ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤትስ?(Announcing the successful bidder)

⚡️ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡፡ የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የጨረታ ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡
    
ጉባኤ አሰፋ(የህግ አማካሪ, 09-75-576924
)

https://t.me/ethioengineers1
👍18❤2🔥1🙏1
💥ተቋራጮችን ከመንግስት ግዢ አቅራቢዎች ዝርዝር ማገድ [Suspension from Suppliers List]


⚡️በመንግስት ግዢ ወቅት በሚፈፀሙ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች ምክንያት ጥቅሜ ተነክቶብኛል የሚል አቅራቢ ወይም ተጫራች  ለግዢ ፈፃሚው የመንግስት አካል ወይም ለአቤቱታ አጣሪው ቦርድ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለው የአዋጁ አንቀፅ 70(1) እንዲሁም የመመሪያው አንቀፅ 43 ይገልፃሉ፡፡ ነገር ግን አቤቱታ የማይቀርብባቸው ጉዳዮችም እንዳሉ አንቀፅ 70(2) እና 44 በዝርዝር ያስቀምጣሉ፡፡   

⚡️ነገር ግን የዚህ ፅሁፍ አላማ በግዢ ፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለኤጀንሲው በሚያቀርቡት አቤቱታ ላይ ተመሰረቶ ኤጀንሲው ተቋራጮችን ከተጫራቾች ወይም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ሊያግድ ስለሚችልበት ሁኔታዎች ለመወያየት ስለሆነ ተጫራቾች ስለሚያቀርቡት አቤቱታ እና ስለአፈታት ስርዓቱ በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለው፡፡

⚡️የግዢ ፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤት በተጫራቾች ወይም በአቅራቢዎች ሕገ-ወጥ ተግባር ወይም ሕጋዊ ጥቅሜን የሚነካ ተግባር ተፈፅሞብኛል ብሎ ሲያምን በአዋጁ አነቀፅ 12 መሰረት ለተቋቋመው የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቤቱታውን ማቅረብ እንደሚችል አንቀፅ 76(1) እንዲሁም የመመሪያው አንቀፅ 48(1) ይደነግጋሉ፡፡ አንቀፅ 15(7) በዕጩ ተወዳዳሪዎችና በአውራቢዎች ላይ የመ/ቤቶች የሚያቀርቡትን አቤቱታዎች መርምሮ ውሳኔ መስጠት የኤጀንሲው አንዱ ተግባር መሆኑን ይገልፃል፡፡

⚡️በዚህም መሰረት ኢጀንሲው አቤቱታ ሲቀርብለት አቤቱታ ለቀረበበት ወይም ለተከሳሽ ዕጩ ተወዳዳሪ ወይም አቅራቢ አቤቱታ መቅረቡንና የአቤቱታዉን ይዘት የሚገልፅ ማስጠንቀቂያ በመላክ ያሳውቃል፡፡ ይህም የተከሳሽ በአስተዳደር ዉሳኔ አሰጣጥ ላይ የመሰማት መብቱን እነዲጠበቅ ይረዳል፡፡

⚡️ይህ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ‹ተከሳሽም› በ5 የስራቀናት ውስጥ የፅሁፍ መልሱንና የሰነድ ማስረጃዎችን ለኤጀንሲው ማስገባት እንዳለበት ከመመሪያው አንቀፅ 48.3 ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡

⚡️ኤጀንሲውም አቤቱታውን በተቀበለ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ መርምሮ ውሳኔ በመስጠት ለተከራካሪዎቹ በፅሁፍ ማሳወቅ እንዳለበት የአዋጁ አንቀፅ 76(4) ከመመሪያው አንቀፅ 48.4 ጋር ይገልፃሉ፡፡ ለአቤቱታውም ሊሰጡ የሚችሉት ዉሳኔዎች አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ፤ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት፤ ወይም ዕጩ ተወዳዳሪውን ወይም አቅራቢውን በመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፍ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ከተወዳዳሪነት ወይም ከአቅራቢነት ማገድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

⚡️ስለዚህ ተቋራጮች በቀረበባቸው አቤቱተታ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ በማንኛውም የመንግስት ጨረታ ላይ እንዳይወዳደሩ ሊታገዱ ይችላሉ ማለት ነው፡፡
ተጫራቾች ከማንኛውም የጨረታ ውድድር ሲታገዱ በተለምዶ በጥቁር መዝገብ ወይም “Black List” ውስጥ ገቡ ይባላል፡፡

⚡️ዋናው ነገር ደግሞ ምን ምን ዓይነት ጥፋቶች ናቸው ተጫራቾችን በጥቁር መዝገብ እንዲገቡ የሚያደርጓቸው? የሚለው ነው፡፡ እነዚህም ነጥቦች በመመሪያው አንቀፅ 48.5.1 እና 48.5.2 ላይ በዝርዝር ተቀምተጠዋል፡፡

⚡️በአንቀፅ 48.5.1 እንደተዘረዘሩትም የጨረታ ግምገማውን ውጤት ለማበላሸት ወይም ለመለወጥ አስበው  ለግዢ ሰራተኞች ሙስና መስጠት፤ የውሸት ወይም ተቀባይነት የሌላቸውን መረጃዎች በማቅረብ ማጭበርበር፤ የኤጀንሲው እግድ እያለባቸው በግዢ ላይ መሳተፍ/መወዳደር እንዲሁም ተጫራቾች ወይም አቀራቢዎች በዉሉ ከተገለፀው ጥራት የወረደ ዕቃ፤ ስራ፤ ወይም አገልግሎት በማጭበርበር ወይም ከገዢ ሰራተኞች/ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ያቀረቡ እንደሆነ ኤጀነሲው ከሁለት ዓመት ጀምሮ እስካልተወሰነ ጊዜ ድረስ በማንኛውም የመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፉ ሊያግዳቸው ይችላል፡:
ከእነዚህም ምክንያቶች በተጨማሪ ተጫራቾች ፍትሃዊ የዋጋ ወድድር ጥቅምን ለማሳጣት ከተወሰኑ ተጫራቾች ጋር በመመሳጠር የዋጋ ተመን ካወጡ/ከጣሉ፤ የግዢ ባለሙያዎች ወይም የግዢ ፈፃሚ መንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ላይ የአካል ጉዳት ለማድረስ የዛተ/ያስፈራራ ወይም ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በኤጀነሲው  የተጣለበት እግድ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመታት ዉስጥ ሌላ ማንኛውም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ሊያሳግድ የሚችል ጥፋት የፈፀመ እንደሆነ በተመሳሳይ ከሁለት ዓመት ጀምሮ እስካልተወሰነ ጊዜ ድረስ ሊታገድ ይችላል ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ሙስና፣ ማጭበርበር፣ መመሳጠር፣ ወይም ዕግድን ጥሶ በጨረታ ላይ መወዳደር ተጫራቾችን/አቅራቢዎችን ከአቅራቢነት ዝርዝር ሊያሳግዳቸው ይችላል ማለት ነው፡፡
በሌላ በኩለ ደግሞ አንቀፅ 48.5.2 ላይ እንደተገለፁት ከመንግስት ጋር የግዢ ውል የተዋዋለው አቅራቢ በዉሉ የተገለፁትን ዕቃዎች፡ ስራዎች ወይም አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ባለማቅረቡ ምክንያት የግዢ ፈፃሚው መ/ቤት ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ጉዳት [Direct or Consequential Loss] ያጋጠመው እንደሆነ ወይም የመ/ቤቱን ስራ ያጓተተ ወይም ያፋለሰ እንደሆነ አቅራቢው ከአቀራቢዎች መዝገብ ላይ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ሊታገድ ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጨረታ ውድድር እንዳሸነፈ በመ/ቤቱ የተገለፀለት አቅራቢ ውሉን ለመዋዋል ባለመቻሉ ወይም እምቢተኛ በመሆኑ ምክንያት መ/ቤቱ በዉሉ የተገለፀውን ዕቃ፣ ስራ ወይም አገልግሎት ከሌላ አቅራቢዎች ለመግዛት ሲል ጉዳት ያጋጠመዉ ወይም ስራዉን ያጓተተ ወይም ያፋለሰ እንደሆነ እነዲሁም የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው አቀራቢ በሶስት ዓመት ውስጥ ሌላ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሊያስጥ የሚችል ጥፋት ፈፅሞ ከተገኘ ኤጀንሲው አቅራቢውን ከአቀራቢዎች መዝገብ ላይ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ሊያግደው ይችላል፡፡

⚡️ከአቀራቢዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ መታገድ ውጤቱም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ወይም አቅራቢው በማንኛውም የመንግስት ግዢ ላይ መወዳደር አይችልም፡፡ እነዚህ በኤጀንሲው የሚጣሉት የዕግድም ይሁን የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ቅጣቶች ግዢ ፈፃሚውን የመንግስት መ/ቤት በአቅራቢው ወይም በተጫራቹ ምክንያት የደረሰበትን የገንዘብ ኪሳራ ከመጠየቅ አያግደውም፡፡
      


https://t.me/ethioengineers1
👍10❤2🤔1💯1