SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥10 የ ዓለማችን ረዣዥም ህንፃዎች

1) Burj Khalifa =Dubai
2) Shanghai tower =China
3) abraj Al-bait clock tower =Saudi Arabia
4) ping An finance centre =China
5) Lotte world tower =south Korea
6) one world trade center =United States
7) Guangzhou CTF finance centre = China
8) Taipei 101 = Taiwan
9) Shanghai world financial center = China
10) international commerce center =China
https://t.me/ethioengineers1

 
👍14👏2❤1
📻ከ ኢንጅነር አቤሴሎም መለስ Fm addis 97.1

📜Series 2000: Site Clearance

🌟ሳይቱ ለግንባታ  clear በሚደረግበት ሰአት ክሊር የተደረገውን area አጋኖ ማቅረብ
🌟በ clearing ወቅት መፍረስ ያለበት ማንኛውም structure ካለ ስራውን አጋኖ ማቅረብ

📜Series 3000: Drainage Structure

🌟የፍሳሽ ትቦዎች ሲሰሩ ቁፏሮውን፣ ግንባታውን፣ back fill ኡንም ጭምር quality ማሳነስ ... ክፍያ ላይ ግን quantity አጋኖ ማቅረብ
🌟መንገዱን አቋርጠው የሚሄዱ ትቦዎች ( cross drainage ወይም culvert) በሚሰሩበት ጊዜ ቁፏሮ፣ backfill ፣ ግንባታውን ወዘተ quality ማሳነስና እንደነገሩ መስራት ... ክፍያ ላይ ያው የተዋዋልነው ተሰርቷል ማለት
🌟የድንጋይ ስራዎች stone pitching፣ masonry ፣ riprap ወዘተ ስራዎችን ማጋነን
🌟ለድልድይና ለትቦዎች ደህንነት የሚሰሩ ግንባታዎችን ማጋነን

📜Series 4000: Earthworks and Material Stabilisation

🌟Road bed (( ወይም የመንገዱ የመጀመሪያው ንጣፍ ማለት ይቻላል)) ሲሰራ መጀመሪያ የነበረው ጥሩ ያልሆነ አፈር (unsuitable material) ተነስቶ ሌላ ተተክቷል ይባላል ((እውነት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል)) ለዚህም ክፍያ አለው ... ቀጥሎም Road bed ለተሰራበት ይከፈላል ... የተሰራው መጠንና ካሊቲውን ፈጣሪ ያውቃል

🌟ሌላው የመንገዱ ትልቁና ዋናው ወጪ Cut  እና Fill ነው ።
🌟Cut section ሲኖር የተቆረጠውን volume አጋኖ ሪፖርት ማድረግ በተጨማሪም በቀላሉ የሚቆረጥ ወይም soft excavation ሆኖ ሳለ Hard Excavation ነው ብሎ ማስገባት ... ብሩ ይጨምራላ
🌟Fill section ሲሆን ደሞ ያው በጥራትም ይሁን በ volume ብዙ መብላት ይቻላል። በተጨማሪ ደሞ fill ሲደረግ በ Layer ነው የሚሞላው ለምሳሌ በ25 ሳንቲም thickness ትሞላለህ ከዛ ኮምፖክት ታደርጋለህ ከዛ ክፍያ ይሰጥሃል ... ሳይት ላይ ምን ሊደረግ ይችላል መሠለህ?? ... 1 ሜትር ለመሙላት ኮንትራቱ ላይ በ25 እየተሞላ ይጠቅጠቅ ካለ 4 Layer ይኖራል ማለት ነው። 4x25 cm = 1 ሜትር ...ሳይት ላይ ግን በ2 layer ብቻ ሊሞላ ይችላል። በ50 cm ውፍረት ማለት ነው። ኮንትራክተሩ አራቴ ሰርቶ ሊያገኝ የሚገባውን በሁለት ስራ ያገኛል ማለት ነው። በዛ ላይ ከሙሉ ወጪው በግማሽ ይድናል። ለ50 ብር ስራውም 100 ይከፈለዋል።

🌟Borrow area ለማግኘትም የተወሰኑ ንግግሮች ይኖራሉ በመሬቱ ባለ ይዞታዎችና በመንገዱ ባለቤት መሀል

📜Series 5000 : Sub Base, Road Base and Gravel Wearing Course

🌟እዚህም እንደላይኛው volume በማምታታት ወይም layer በመቀሸብ ... Layer ቅሸባ ከሚገመተው በላይ አዋጭ ነው

📜Series 6000 - Bituminous Surfacings and Road Base

🌟እዚህም እንደሌሎቹ volume ና layer ቅሸባ ነው።

📜Series 8000 - Structure

🌟እዚህ ስር ያሉት masonry work , bridges, box and slab culvert, cofferdam, timber structures, structural steelwork ወዘተ ናቸው። እንደሚታወቀው እነዚህን ለመስራት የሚያስፈልጉት ማቴሪያሎች ፌሮ ፣ ሲሚንቶ ፣ aggregate ፣formwork ያስፈልጋል። excavation እና backfill ስራዎች ይኖራሉ .... በሌባ አእምሮ do the maths!

📜Series 9000 - Ancillary Work

🌟በእዚህ ስር ያሉት gabion, mattresses, kilometer የሚያመላክቱ ኮንክሪቶች ( Kilometer Post), አስፖልቱ ላይ የሚቀቡ ቀለሞች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ guardrail ፣ ከግንባታ በኋላ አካባቢውንና borrow areaውን ወደ ተፈጥሯዊው ሁኔታ ለመመለስ የሚሰሩ ማስተካከያዎችና የእፅዋት ተከላዎች ፣ አጥሮች ፣ የእግረኛ መንገዶች ፣ ለሴፍቲ ተብለው የሚሰሩ የኮንክሪትና masonry ግድግዳዎች ወዘተ ናቸው።

📌መንገድ ስራ ላይ ማጭበርበርና ውሸት እንደ hobby ወይም ዝንባሌ ነው። ጥዋት ተነስተህ እስፖርት እንደምትሰራው ምናምን በቃ የመንገድ ስራ ሰራተኞች ወደዛ ያዘነብላሉ። በተለይም ከአዲስ አበባ የራቀ ቦታ ላይ ከሆነ ሌቦቹ እንደፈለጉ ይፈነጩብሃል። መንግስት የለም ወይ የሚያስብለኝ ከህዝቦች መሞት ይልቅ መንገድ ስራ ላይ የሚሠራውን ሳይ ነው። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩ እንደአለቃ ይሆንብሃል። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩን ብታማ እንዳንተው ተቆጣጣሪ ተብሎ የተሾመው አለቃህ ይገላምጥሀል ፣ ይነዘንዝሃል። ለምን ካልክ ብዙ ሴራዎችን እየሠሩ መሮህ እንድትሄድ ያደርጉሀል። ይሄንን ፅሁፍ የፃፍኩት ስርቆቱ በግልፅ እንዲታወቅና መፍትሄ እንዲሰጠው ነው። ነገሮቹ መዘርዘራቸውም ለእያንዳንዱ ችግር የራሳችሁን መፍትሄ እንድታስቡ ነው።

የተሻለ መፍትሄ ካላችሁ ወዲህ በሉ
...........

💫መፍትሔው ምንድነው??

1. የመንገድ ባለቤቶች የራሳቸውንም ሰራተኛ፣ ኮንሰልታንቱንም ይሁን ኮንትራክተሮችን ማመን የለባቸውም። ከዚህ ሰርክል ወጣ እያሉ ስራዎችን ቼክ ማድረግ።
2. የተለያዩ ምርምሮችን በማሰራት አዳዲስ የአሰራርና የቁጥጥር መንገዶችን መፍጠር
3. የሚያጋልጡ ግለሰቦችን ማበረታታት
4. መንገድ ስራ ላይ በአብዛኛው በሰርተፍኬት/ዲፕሎማ ነው የሚሰሩት። እነዚህም ሰዎች ስራ እናጣለን በሚል ስጋት የተባሉትን አሜን ብለው ነው የሚሰሩት። የተማረውን ማስገባት የተሻለ ነው።
5. የመንገዶች ባለቤቶች የተቆጣጣሪውንና የራሳቸውን ሰራተኞች ደሞዝ ቢጨምሩ ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ይቀንሰዋል።


https://t.me/ethioengineers1
👍27❤4👏1
✨How to select suitable type of foundations?

1. ADEQUATE DEPTH
The foundation must have an adequate depth to prevent frost damage. For such foundations as bridge piers, the depth of the foundation must be sufficient to prevent undermining by scour.

2. BEARING CAPACITY FAILURE
The foundation must be safe against a bearing capacity failure.

3. SETTLEMENT
The foundation must not settle to such an extent that it damages the structure.

4. QUALITY
The foundation must be of adequate quality so that it is not subjected to deterioration, such as fromsulfate attack.

5. ADEQUATE STRENGTH
The foundation must be designed with sufficient strength that it does not fracture or break apart under the applied superstructure loads. The foundation must also be properly constructed in conformance with the design specifications.

6. ADVERSE SOIL CHANGES
The foundation must be able to resist long-term adverse soil changes. An example is expansive soil, which could expand or shrink causing movement of the foundation and damage to the structure.

7. SEISMIC FORCES
The foundation must be able to support the structure during an earthquake without excessive settlement or lateral movement.


https://t.me/ethioengineers1
👍8❤5🙏1
⚡️በኮንስትራክሽን ሳይት ላይ የሰራተኛ ደህንነት(safety) ቅድሚያ የሚወሰድጉዳይ ነው።

ደህንነት መጠበቂያ አንዱ እና ዋነኛው በራስ ላይ የሚደረግ ቆብ
(Helmet) ይገኝበታል።

የደህንነት መከላከያ ቆብ (Helmet) እንደየ የስራ ድርሻ እና ሀላፊነታችን በቀለም ይከፋፈላል።

እያንዳነዱን ሰው በስራ ሀላፊነት ለመለየት ይጠቅማል።

💥Helmet Color Code

1. White: Managers, Engineers, Supervisors and
Foremen
*
2. Blue: Electricians, Carpenters and other technical operators apart from civil workers
*
3. Green: Safety Officers
*
4. Red: Fire Fighters
*
5. Yellow: Laborers
*
6. Brown: Welders and workers with high heat application
*
7. Grey: Site Visitors


https://t.me/ethioengineers1
👍15❤3👏1🙏1
💥የውል ቃሎችና ድንጋጌዎች አጠቃላይ ፍረጃ /General classification of Contractual provisions/

🌟የውል ቃላትና ድንጋጌዎች የስራውን ስፋት፣ መሰጠት የሚገባቸው አገልግሎቶችን፣ የአሰሪውና የሥራ ተቋራጩን መብትና ግዴታዎች ዝርዝር፣ የሥራ ተቆጣጣሪው/አማካሪው መሃንዲስ የስራ ድርሻዎች፣ ባለሞያዎች አሟልቶ ስለመስራት፣ የፕሮጀክት መሪ ባለሞያ  ተግባርና ሃላፊነቶች፣ የውል ቃላት ትርጉምና የመሳሰሉ አጠቃላይ ሁነቶችን የሚይዝ ሲሆን ከውሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ባህሪ ጋር የሚሄዱ ልዩ ሁነቶችን/Special conditions/ እና ሥራው የሚከናወንበትን ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃችን አካቶ የሚይዝ ነው፡፡

🌟የውል ድንጋጌዎች በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር /MoWUD/፣  በኢትዮጵያ መንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ /PPA/ ፣ እና በዓለም አቀፍ አማካሪ መሃንዲሶ ፌደሬሽን /FIDIC/ ሰነዶች ውስጥ የተለየ አቀራረጽና አቀማመጥ ይዘው የተዘጋጁ ቢሆንም አጠቃላይ ይዘታቸው ላይ ግን እምብዛም ልዩነት የላቸውም።

📌በመሆኑም የውል ቃላትና ድንጋጌዎችን አሁን በሃገራችን በስፋት የምንጠቀምበትን የኢትዮጵያ መንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ /PPA/ ሰነድን በመጠቀም የውል ድንጋጌዎችን በይዘታቸው በአጠቃላይ በ6 ልንፈርጃቸው እንችላለን።እነዚህም:

1.ጊዜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች/Time provisions/

2. ስለክፍያ/ቀብድ/መተማመኛ/Payment related provisions/

3.የሥራ ተቋራጩ፣ የአሰሪውና፣ የመሃንዲሱ ግዴዎችና ሃላፊነቶች/Parties Obligation/

4.ውል ስለመፈፀምና ስላለመፈፀም እና  ስለሚያስከትሉት ውጤቶች ጋር ተዛማጅ የሆኑ የውል ድንጋጌዎች /Performance and Nonperformance of contract and their effect/

5.ልዩ ልዩ ሁነቶች /Conditions /

6.ባለአማራጭ ሃሳብ ድንጋጌዎች/Alternative Provisions ናቸው።

💫በሌላ ጊዜ በምናቀርባቸው ፅሁፎች በእያንዳዱ ስር ስለሚካተቱት ድንጋጌዎች ዝርዝርና በእያንዳንዱም ላይ ማብራሪ የምንሰጥ ይሆናል።

https://t.me/ethioengineers1
👍11❤6👏2
✨Post-tension slab

⚡️Post-tension slab is a type of concrete slab that is reinforced with high-strength steel cables or tendons, which are tensioned after the concrete has been poured and cured.

🌟This process helps to increase the strength and durability of the slab by applying a compressive force to the concrete, which counteracts any tensile stress that may occur due to external loads or forces. Post-tension slabs are commonly used in large commercial and residential buildings, bridges, parking garages, and other structures that require a high level of strength and stability.

🌟They offer several benefits over traditional reinforced concrete slabs, including reduced cracking, improved load-bearing capacity, and greater flexibility in design and construction.


https://t.me/ethioengineers1
👍9❤4
ቦሌ - ራማዳ ሆቴል አካባቢ ግንባታ እንዳይካሄድ ታገደ

ቅንጡ ሠፈሮችን እያመሱ የሚገኙ ግንባታዎች ጉዳይ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ ወጥ የሆነ ደረጃ አስኪዘጋጅ ድረስ በተለይ በአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ) ራማዳ ሆቴል አካባቢ የሚካሄዱ ግንባታዎች እንዲቆሙ ዕግድ አወጣ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ትናንት ሃምሌ 12 ቀን 2015 ዓም ለቦሌ ክፍለ ከተማ በፃፈው ደብዳቤ - በወረዳ 3 በተለይም ከራማዳ ሆቴል ግራ እና ቀኝ ውስጥ ለውስጥ የተካሄዱ ግንባታዎችም ሆኑ ግንባታ ፈቃድ የወጣባቸው ፕሮጀክቶች እንዲቆሙ አዘዘ።

በነዚህ አካባቢዎች በርካታ ባለስልጣናት ፣ ባለሃብቶች እና ዲፕሎማቶች የሚኖሩበት አካባቢ ቢሆንም - ግለሰባዊ ነፃነትን የሚጋፉ ህንፃዎች በብዛት እየበቀሉ በመሆኑ ቅድሚያ ተሰጥቶት መታገዱን የወዝ ኒውስ መረጃዎች አመልክተዋል ።

ይህንን እውነታ ከግምት በማስገባት የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ስጦታው አካለ (ኢንጂነር ) ለክፍለ ከተማው ጥብቅ ትዕዛዝ በሰጡበት ደብዳቤ ፣ አካባቢው በነባሩ ፕላንና አሰፋፈር ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች የሉበት በመሆኑ ፣ በድጋሚ እስኪጠና ድረስ ከ ሃምሌ 12 ጀምሮ ምንም አይነት ግንባታ እንዳይፈቀድ ፣ የተፈቀዱ ግንባታዎችም ለጊዜው ቆመው በቀጣይ እንዲሻሻሉ መወሰኑን አመልክተዋል።

ቀደም ሲል ዘመናዊ መኖሪያ የተገነባባቸው ሠፈሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ እና ትላልቅ ህንፃዎች እየተገነቡባቸው ነው። ግንባታዎቹ የተለመደ አኗኗርን እያወኩ ነባር ነዋሪዎችን እያስለቀቁ ከመሆኑም ባሻገር ፣ የመኖሪያ ሠፈሮችን እያሳጣ የሚገኝ ያልተገራ አካሄድ በመሆኑ ቅሬታ ሲቀርበብት ቆይቷል ።


https://t.me/ethioengineers1
👍17❤1
💥አንድ የስራ ተቆጣጣሪ ባለሞያ የኮለን ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ፎርምወርክ ስራው ላይ መሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚገባው መሰረታዊ ነጥቦች

[Elements of good Column formwork finish]

1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/

⚡️የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል።

2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/

⚡️ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ሌላ አስፈላጊ ስራ ነው።

3.አቀባዊ ሊኛ/Vertical alignment/

⚡️የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ አለበት።

4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/

⚡️የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው ሆኖ መቀመጡን ማረጋገጥ አለበት።

5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/

⚡️በዲዛይኑ መሰረት የኮለኑን ወርድና ስፋት ከፎርምወርኩ አቀናንሶ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ።

6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/

⚡️ከታወቀ መነሻ በመነሳት አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ።

7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/

⚡️ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Concrete cover/


⚡️ለኮንክሪት ሽፋን ዲዛይኑ የሚጠይቀው ተገቢ መጠን፣ በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።

https://t.me/ethioengineers1
👍18❤7🙏3👏1
💥ክርስቲ

ቢሙ ካስት ሲደረግ በዋነኝነት የቢሙን ሎድ የሚሸከም በአራት አጠናዎች የተዋቀረ
ነው፡፡ ‹ ዋ › ፊደልን ይመስላል፡፡

ቢም ካስት ከማድረጋችን በፊት የምንከተላቸውን እስቴፖች ቀጥለን እንመለከታለን
፡፡

1. በመጀመሪያ ጎማ ውሃ ልክ አዙረን ቢሙ የሚያርፍበትን ቦታ
already ካስት የተደረጉ ኮለኖች ላይ ምልክት እናደርጋለን፡፡

2. በኮለኖች መሃል ምልክት የተደረገባቸውን ቦታዎች በሲባጎ እናገናኛለን - ሲባጎው የሚያርፍበት ቦታ የቢሙ ስር ወይም ቂጥ
ነው

3. በሁለት ኮለኖች መሃል - ኮለኖቹ ጥግ ላይ ሁለት ክርስቲ አቁመን ወገባቸውን እናሲዛለን

4. በሁለት ኮለኖች መሃል የሚያስፈልገውን ያህል ክርስቲ እንደረድርና በዳርኞቹ ክርስቲዎች ውስጥ ሁለት ማገሮች እናስገባለን፡፡ በመቀጠልም መሃል ላይ ያሉትን ወይም ወገባቸውን ያልያዙትን ክርስቲዎች ከማገሩ ውጪ በማድረግ ወገባቸውን
በሚስማር እናሲዛለን

5. ክርስቲዎቹ አናት ላይ በሁለቱም በኩል ማገር እንመታለን

6. ሌላ ትይዩ ቢም ካለ ከእስቴፕ 1-5 ያለውን እንሰራለትና ከዚኛው የክርስቲ ግሩፖች ጋር በማገር እናያይዛቸዋለን

7. በተወሰነ ርቀት ላይ ስላቡ የሚያርፍበትን ቋሚዎች እናቆማለን

8. ለውሃ ልክ የዘረጋነው ሲባጎና የክርስቲው አናት ልክ ከመጣልን እንደዛው እንተወዋለን - ልክ ካልመጣ ግን ‹ ኩኞ › በክርስቲውና
በሲባጎው (ፎንዶው ስር) መሃል እናስገባለን

9. ፎንዶውን የቢሙን alignment ጠብቀን እናስቀምጣለን

10. ስፖንዳ እንመታለን - እስፖንዳውን በአጠና እንደግፈዋለን

11. የቢሙን reinforcement አስገብተን ቢሙን ካስት እናደርጋለን


-ኩኞ -ቁርጥራጭ አጠና
-ፎንዶ - ቀጥታ ከቢሙ ስር የሚያርፍ ተሸካሚ ፎርም ዎርክ
-እስፖንዳ - ቢሙን ከጎን የሚይዝልን ፎርም ዎርክ


https://t.me/ethioengineers1
👍33❤4👏4
Angle እና Direction
.
*Northing = ማለት Y-Coordinate ማለት ነው ከ (0,0) ወደ Y direction ምን ያህል እንደሚሄድ የሚያሳይ ነጥብ

*Easting = X Coordinate
*Azimuth angle =Clockwise አቅጣጫ
ከ North ስንለካ የምናገኘው አንግል

*Bearing = acute angle ሲሆን clockwise ወይም counterclockwise ከ
North ወይም South ስንለካ የምናገኘው

*ከዚህ ሌላ ህንፃዎች ላይ ከ angle እና direction አለማወቅ ወይም ግዴለሽነት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡

ለምሳሌ ለፀሀይ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ ትልልቅ መስታወቶችን / መስኮቶችን ማድረግ፣ ዲዛይን ሲደረጉ ከታሰበላቸው አቅጣጫ ውጪ
የዞሩ ህንፃዎች መገንባት (በስህተት ፊታቸውን ወደ መንደር ጀርባቸውን ወደ መንገድ ያዞሩ
ሞሎች፣ መኖሪያ ቤቶች ወዘተዎች እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን) ፣ ያልሆነ ቦታ ላይ ግንባታ በመጀመር ህንፃን ያልሆነ ቦታ ላይ
ማሳረፍ ወይም የሰው ይዞታ ውስጥ እስከመግባት ፣ ስራው ከተጀመረ በኋላ አቅጣጫው ልክ እንዳልሆነ ሲያውቁ ፓዶችን
እያነሱ ቦታ ማቀያየር ካልተቻለም እንደዛው የዞረ ፎቅ ገንብቶ መጨረስ …… ሁሉም
ከአቅጣጫ አለማወቅ የተነሳ የሚፈጠሩ ችግሮች ናቸው፡፡

North, East, South, West አለማወቅ የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ አልተማሩም የምንላቸው አባቶቻችን እናቶቻችንን ሲቀጥሩ
‹‹በስተምዕራብ በኩል ያለው ዛፍ ስር ጠብቂኝ›› ሲሉ እናቶቻችንም ‹‹የከሰዓቱ ፀሀይ እንዳያስቸግረን በስተሰሜን በኩል ያለው ዛፍ
ይሻለናል›› እያሉ ሃሳብ ያቀርቡ ነበር::

እኛ ፊደል ቀመሶች ግን ለስራ ደቡብ ክልል ተልከን
ሰሜን ምስራቅ ክልል እንገኛለን፡፡

*ለማንኛውም አቅጣጫን ለማወቅ 3 መንገዶች አሉ፡፡
.
*አንደኛ ኮምፓስ መግዛት ወይም ስልክህ ላይ የኮምፓስ አፕሊኬሽኖችን መጫን፡፡

*ሁለተኛ ጠዋትና ማታ የፀሀይ መግቢያና መውጪያ ቦታዎችን እያዩ አዕምሮአችን አቅጣጫዎቹን
ሴቭ እንዲያደርግ መጣር፡፡

*ሶስተኛው ደሞ ኮምፓስ ከሌለንና ፀሀይ እስክትገባ የምንጠብቅበትም ሰዓት ከሌለን ዞር ዞር በማለት ዲሽ መፈለግ… ናይልሳት የተሰራ ዲሽ ጀርባ በመሆን LNB የምትይዘዋ ዘንግ ቀጥታ የምታሳየው 7 ዲግሪ West ነው፡፡

ስለዚህ ከዲሹ አቅጣጫ በመነሳት ሌሎቹንም
አቅጣጫዎች ማወቅ ትችላለህ፡፡  

ደሞ ዲሽ አገኘው ብለህ በአረብ ሳት አቅጣጫ
ተመርተህ ወደ ሰማይ የዞረ ፎቅ እንዳትሰራ “ናይልሳት ነው seven degree West


https://t.me/ethioengineers1
👍23❤3🤔1💯1
HOW TO CHECK SAND QUALITY IN FIELD?
.

➡There are some useful tests that can be done in the field for checking
the quality of sand utilized for construction. The
following tests may
be performed to determine the characteristics of
sand.
🚩FIELD TEST OF SAND:


1. Take a glass and add some water in it.
2. Add a few amount of sand in the glass. At that
point, shake it vivaciously and permit it to settle. If there is clay present in the sand, an apparent layer will be formed at the top level of sand.
3. Mix the sand into sodium hydroxide or caustic soda solution to
distinguish the presence of organic impurities.
If organic impurities
are present in the sand, the color of the solution
will be turned into brown.
4. Now take a squeeze of sand and taste it. If it is
salty that means salt is present in the sand.
5. Take little amount of sand in the hand, and then
rub it against the
fingers. If the fingers are recolored it means sand
consists of some
earthy materials.
6. The color of sand describes the cleanness of
sand. The size and sharpness might be examined by touching and
watching visually.
7. The sand may be examined by mechanical
analysis to know its
fineness, durability, void ratio etc.


https://t.me/ethioengineers1
👍10❤1👏1🤔1
የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/

▶️ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው።

▶️የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት /resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል።

▶️ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል።

⏺እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል።

✨የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/

2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን

⏺የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን?

▶️በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ።

🚧እነዚህም

⏺1. Slump test
⏺2.Compacting factor test
⏺3.Veebee test እና
⏺4.Vibro workability test ናቸው።

🚧ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት /Slump test /Cone test/ or /Sand test/

💫የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል።

🌟ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል።

🌟ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

🌟የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች
(Factors influencing slump test result)

1- ለኮንክሪቱ  የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ።

⏺ለምሳሌ:  ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም

2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር.

3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም።

4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ

5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/

6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን

7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ

🌟Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው?

⏺ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/ :-ይህ ቅርፅ ማውጫ 30 cm
ቁመት የታችኛው ዲያሜትር 20 cm
የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው

⏺Plate/መደብ/ :- ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/

💫የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው?

1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት።

2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ።

3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት።

4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት።

5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን።

6ኛ. በርጋታ  ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት።

7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።

🌟ማስታወሻ

⏺ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን።

⏺ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች /Results to be/

🚧True Slump

🏷ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው።

⏹ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው።

🚧Zero Slump

🏷ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና
ሲሚንቶ /water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል።

🚧Collapsed Slump:

🏷ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል እንዲሁም የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል።

🚧Shear Slump

🏷ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።


https://t.me/ethioengineers1
👍17❤4💯2
🌟ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ /Soil Compaction/ በጥቂቱ

☄Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።

✨እንዴት?

✨አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ/density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው።

💥ይህም በመሆኑ:

*የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን።

*በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን።

*ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/

⚡️የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/

⚡️የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው።

⚡️በሰው ሰራሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ /Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል።

🤞ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው።

✨የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/

⚡️በዋናነት በሁለት ይመደባሉ።

-በሳይት ላይ የሚተገበሩ /Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው።

-በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test... 

ለዛሬ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን።

⚡️Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/

ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው።

* *የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/

የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር

መቆፈሪያ፣ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/

ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/:

ንፁህ አሸዋ

ወንፊት

ሚዛን/Balance/

ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ

* *የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/

1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ።

2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት።

3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።

ማስታወሻ:- የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን።ምስል 5 ን ይመልከቱ

4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ።

5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

6ኛ. የተሰበሰበው ዳታ በመጠቀም. የሳይት ላይ እፍግታውን/Bulk density/ ማወቅ እንችላለን። በቀጣይ ጽሁፍ የሚወጣውን ምሳሌ መመልከት ይቻለል።

7ኛ. ከፍተኛው የደረቅ እፍግታ ልኩን/MDD/ በቤተ ሙከራ ለመስራት ከሰሃኑ ላይ ለናሙና 1/3ኛ ያህሉን በንፁህና ደረቅ ላስቲክ በማድረግ ማዘጋጀት።

ማስታወሻ:-የተወሰደው ናሙና ባእድ ነገር እንዳገባበትና ከሌላ ናሙና ጋር ለመለየት እንዲያስችለረ በጥንቃቄ መታሸግና እላዩ ላይ መለያ ኮድ መጻፍ ይገባል።

እንደስራው ደረጃና የሳይቱ ስፋት መጠን ከላይ የተጠቀሰውን አካሄድ ቢያን ሶስትና ከዚያ በላይ በመሃንዲሱ በተመረጡ ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል።

⚡️የአፈር ጥቅጠቃ ስራ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

የአፈሩ ዓይነት/soil type/

ለምሳሌ: ኮረታማ/ጠጠርማ/Gravel/Granular/ አፈር ለመጠቅጠቅ ምቹና በጣም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሲሆን፣በተቃራኒ ጥቁርና ብስባሽ ያለው አፈር ደግሞ ለመጠቅጠቅ የማይሆንና የማይች በመሆኑ ለማንኛውም ስትራክቸራል ሙሊት ስራ የማይመረጥ ነው ይሆናል ማለት ነው።ከታች በምስል 4 ላይ የተቀመጠውን ይመልከቱ።

⚡️የአፈሩ ውሃ ይዘት/soil water content/:

⚡️አፈሩ በጣም ውሃ ያዠ ወይም ከልክ በላይ የደረቀ መሆን የምንፈልገውን እፍግታ ማግኘት እንዳንችል ያደርጋል ማለት ነው።

⚡️የጥቅጠቃ ሃይል/Compaction Effort/


https://t.me/ethioengineers1
👍16❤4👏1🙏1
Dear Readers,

In this special issue, Ketema traveled 500 kilometers across the country zooming out of the bustling metropolitan city to a serene and picturesque site nestled within the hills and mountains of Dawro zone.

Halala Kella lodge, named after the fortified rocks of the Dawro kingdom is a testament to a new specimen of hospitality architecture in Ethiopia that was designed respecting the topography, natural environment, indigenous culture and history of the great Halala wall.

Check it out! 👇
https://ketemajournal.com/v-20/
https://ketemajournal.com/v-20-flipbook/

MAY • JUNE • 2023

Printed versions available at:
Abrehot Library
Tomoca Coffee (all branches)
The Urban Center
Gelani Coffee, Dumerso Coffee
Kebena House, Zoma Museum
And more destinations
👍5❤3
👋የስሚንቶ ሽያጭ በቅርቡ ወደ ዲጂታል ግብይት ስርአት እንደሚቀየር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

⚡️የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተለይም ለአራዳ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እየፈተነው የሚገኘውን የስሚንቶ ግብይት ሙሉ በመሉ ወደ ዲጅታል ለመቀየር እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

⚡️የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ በላይነሽ እረጋሳ እንዳሉት ስሚንቶን ወደ ዲጂታል ግብይት ለማስገባት ከቴሌና ከስሚንቶ አምራች ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተደርሷል፡፡

⚡️የዲጂታል ግብይቱ ሲጀመር ጣልቃ የሚገቡ የስሚንቶ ደላሎችን መሉ በሙሉ ማስቀረት እንደሚችል ታምኖበታል ሲሉ የኮሚዩኒኬሽን አስፈፃሚዋ ገልፃዋል፡፡

⚡️የስሚንቶ አምራች ኩባንያዎችም ወኪሎቻቸው ምንያህል መጠን ስሚንቶ ይፈልጋሉ እንዲሁም ሽጠው ጨርሰዋል ወይ የሚሉትን ከዲጂታል መተግበሪያው ላይ ማወቅም መቆጣጠርም ያስችላቸዋል ነው ያሉት፡፡

🫵ይህም በ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የራሱ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Via -  Arada FM


https://t.me/ethioengineers1
👍15🤔4👏1
🚧How can this be eleminate?🙄
📩
@Ethiocon143bot

https://t.me/ethioengineers1
🤔5👍1
👉ሞሪስ ካልካ

👌ቀራፂ፣ነዳፊ፣ከታሚ | 1913 - 1991 ዓ.ም

🫵አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ከብሔራዊ ቲያትር አጠገብ ያለውንና በዓለም የታወቀዉን ባለ 10 ሜትር ቁመት የአንበሳ (የይሁዳ አንበሳ) ሥነ-ቅርፅ በ1948 ዓ.ም በአፄ ሃይለ-ሥላሴ ትዕዛዝ ከቲያትሩ የሥነ-ኪነ-ሕንፃ ነዳፊዎች ሄነሪ ሾሜና አንቶይን ላጌት ንድፍ ጋር በማናበብ የነደፈና በግሩም መልኩ የቀረፀ ስመ ጥር ፈረንሳዊ (ፖላንዳዊ ተብሎም ይጠቀሳል) የሥነ-ቅርፅና ንድፍ ባለሙያ ነበር።

🌟ሞሪስ ከመኪና ፣ ከሥነ-ሥቅለት ቅርፅ ፣ ከጠረጴዛ ፣ ከወንበር ፣ ከተለያዩ የሠዉና የእንሠሳት ገፅታዎችና ሁለንተናዊ የሥነ-ቅርፅ ስራዎቹ በተጨማሪ ግሩም የመጠንና (Scale) የምጣኔ (Proportion) ዕሳቤዎቹን ጨምሮ ለቅርፅ ከሚጠቀማቸው ቁሶችም አንፃር ልዩና ጥበባዊ የሥነ-ቅርፅ አገላለፅን የተካነ ባለሙያ ነበር።

🌟ከ50 በላይ የሚሆኑ ስራዎቹ በሙሉ በሁለቱ እጅጉን ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈ ሲሆን በከተማችን ከእነ ውበቱና ሞገሱ እስካሁን ዓይንን በቀላሉ በሚይዝ ቅርፃዊ ምስሉ (Silhouette) እየታየ የሚገኘው የአንበሳ ሥነ-ቅርፅ ዋነኛው ነው። ሞሪስ ሁሉንም ሊባል በሚችል መልኩ የሥነ-ቅርፅ ሥራዎቹን በፓሪስ ከተማ ሩ ራፌት በሚገኘው የስራ ቦታው (Studio) የተገበረ ሲሆን 15 የተገነቡ የከተማ ቦታና የሥነ-ኪነ ሕንፃ ሥራዎችም ላይ በተባባሪነት ተሳትፏል።

Via NArc Home Architecture

#Architecture
https://t.me/ethioengineers1
👍6❤1
SMH General Construction
🌧ከ ክረምት ጋር በተያያዘ የውሃ ስርገትና ርጥበትን እንዴት ልከላከል /Damp Prevention/ 💧የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ ሌሎች የተለመዱ መንገዶች/Typical Membrane Damp-proofing Agents/ ⭐️1ኛ. የኮንክሪት ግግር መደብ/Application thin Concrete layer(s) / ⚡️አነስተኛ ርጥበት የሚፈጥር የውሃ ስርገት መኖሩ ሲገመት ማለትም የውሃ ፍሰቱ/እዠት…
💥የፍሳሽ ስርገትና ርጥበትን መከላከል/Damp Prevention/
☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️☔️

🌟ከ ባለፈው የቀጠለ

⚡️አንድ ህንጻ የታሰበለትን የተሟላ አገልግሎት እንዲያስገኝ ከሚያስፈልጉ ፍላጎቶች አንዱ ህንጻው ከማንኛውም በግድግዳ፣በጣሪያና ከመሬት በላይ ወይም ከመሬት ስር በሚኖረው ወለል ከሚመጣ ፍሳሽ ከሚፈጠር ርጥበት/hygroscopic moisture/ የጸዳና ደረቅ መሆኑ ነው።


💧ለርጥበት መከሰት ምክንያቶች/Sources of Dampness/:

1.ከመሬት ውስጥ ወደላይ የሚወጣ ውሃ/Moisture Rising up the wall from Ground/:

2.ግድግዳን ሰርጎ ውስጥ ለውስጥ ወደታች የሚወርድ የዝናብ ውሃ/Rain Travel from wall Tops/

3.በግድግዳ ሰርጎ ግድግዳውን የሚያለዝብ የዝናብ ውሃ/Rain beating against External wall/

4.ጥዘት/Condensation/

5.ሌሎች ምክንያቶች

-ደካማ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት

-የህንጻ አቀማመጥ አቅጣጫ ልክ ያለመሆን/imperfect orientation/

-በቂ ያልሆነ የጣራ ተዳፋት/imperfect Roof slope/

-የግንባታ ጥራት ችግር........

💧የርጥበት መከሰት የሚያስከትካቸው ችግሮች/Effects of Dampness/

1.ንጽህናው ያልተጠበቀና ጤናን የሚጎዳ ሁኔታን ይፈጥራል፣

2.ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ  ምክንያት ይሆናል።

3.ለተጠቃሚዎች ምቾትን የሚነሳ አካባቢ እንዲፈጠር ያደርጋል።

4.የልስን ስራ ላይ መሳሳትና መፈርፈር ምክንያት ይሆናል።

5.እንደቀለምና የቤት ማስዋቢያ ስራዎች ላይ ብልሽት ያስከትላል።

6.የወለልና ግድግዳ ማጠናቀቂ ስራዎች/Damages on floor & wall coverings/

7.ከብረት የተሰሩ የተለያዩ የግድግዳ፣ወለልና ጣሪያ ስራዎች ላይ ዝገት እንዲፈጠር ያደርጋል።

8.እንደ ኤሌክትሪክ ስራዎችና

⏺በአጠቃላይ የህንጻ ደህንነት ላይ አደገኛ ደረጃ ጉዳት እስከማድረስ ችግር ሊፈጥር ይችላል ማለት ነው።

💧የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ መንገዶች/Methods of Dampness prevention and water proofing works/


https://t.me/ethioengineers1
👍12❤5🙏2