SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
ስለ ኮንስትራክሽን ላያውቋቸው የሚችሉ አምስት ነገሮችን እነኾ፦

1. የዓለማችን ረዥሙ ክሬን 53.3 ሜትር ድረስ ከፍ ማለት ይችላል።  ብራንዱም Liebherr type HC-L ነው።

2. በ2018 በመላው ዓለም ለኮንስትራክሽን የወጣው ገንዘብ 11.4 ትራሊየን ዶላር ሲኾን በ2030 17.5 ትሪሊየን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል።

3. በኤምፓየር ስቴት ሕንጻ ላይ 10 ሚሊየን ጡቦች ይገኛሉ።

4. ከግንባታ ዕቃዎች መካከል በቀዳሚነት ጥቅም ላይ የሚውለው ኮንክሪት ነው።

5. በዓለም ዙሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ ሰዎች ቁጥር 180 ሚሊየን ይገመታል
።

https://t.me/ethioengineers1
👍18❤3
👍3❤1
የግንባታ ወጪን ለመቀነሰ የሚረዱ አማራጭ ዘዴዎች

ለህንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ እንደ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ብሎኬት፣ ጠጠር ያሉ ጥሬ ዕቃዎች ዋጋ እ.ኤ.አ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ1000 ፐርሰንት በበለጠ ዋጋ እየጨመረ የመሄዱ ጉዳይ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

ለዚህ መንስኤ በዋነኝነት የሚጠቀሱት የማምረቻ፣ የሠራተኛ ጉልበት፣ የትራንፖርት ዋጋ መጨመር እና ተያያዥነት ያለው የዋጋ ግሽበት ናቸው፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ልዩ ባህሪ ደግሞ ጥሬ ዕቃዎችን በመግዛት እና በመደባለቅ፣ ጠንካራ ረጅም ዕድሜ የሚኖረው እና ውብ የሆኑ ህንፃዎችን መገንባት ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት የኮንስትራክሽን ኤክስፐርቶች የጥሬ ዋጋ ንረትን በመቋቋም ወጪን ለመቀነስ ያስችላሉ ብለው በቀዳሚነት ያስቀመጧቸውን አሠራሮች መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ጠንካራ የዕቅድ ፕላን መዘርጋት

እንደ ማንኛውም የንግድ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የመጨረሻ ልብ ማትረፍ ነው፡፡ ይህንን ትርፍ ለማግኘት ለግንባታው የሚያስፈልገውን በጀት እና ዝርዝር የግንባታ ሂደቶች የተመለከተ ጠንካር ያለ የዕቅድ ፕላን መቀየር ነው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉ ጠንካር ያሉ የዕቅድ ፕላኖች ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን ካለው  ነባራዊ ሁኔታ በመመርመር ቀደም ብሎ ማከማቸት በእያንዳንዱ የግንባታ ሂደት የሚያስፈልጉ ግብዕቶችን ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ናቸው፡፡

2. መደበኛ የሆነ እና የሚደጋገም ዲዛይን

አንድ ህንፃ ከመሬት ተነስቶ እያደገ በሄደ ቁጥር፣ የሚይዛቸው የክፍል ገፅታዎች መደበኛ የሆነ ስፋት እና ገፅታ የተለበሱ እንደሆኑ ማድረግ ዋጋን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ህንፃው ባደገ ቁጥር የውስጥ ገፅታ ዲዛይን የሚለዋወጥ ከሆነ፣ የጥሬ ቁስ ብክነት ያስከትላል፡፡ ለተለዋጭ ዲዛይን የሚሆን ሌላ ጥሩ ቁስ መግዛትን ይጠይቃል፡፡

እስከ ዘለቄታው ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን ቀደም ብሎ ማከማቸት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች በየጊዜው እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ የሥራ ፍጥነት እና ሂደትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጋሬጣ ይፈጥራል፡፡

3.አማራጭ ቁሶችን መጠቀም

በህንፃ ግንባታ ህንፃው ለወደፊት የሚሰጠውን አገልግሎት ከግምት በማስገባት ረሳይክልድ የሆኑ ብረቶችን ከጂፕሰም እና ከጣውላ የሚዘጋጀ የውስጥ ማከፋፈያ ግርግዳዎችን መጠቀም፣ ተገጣማሚ ብሎኬቶች እና ግርግዳዎችን መጠቀም የህንፃው የግንባታ ዋጋ እንዲቀነስ ያደርጋሉ::

4. የግንባታ ባለሙያዎች ወጪን መቀነስ

የግንባታ ሂደትን በጊዜ ሰሌዳ ሸንሽኖ አስፈላጊውን ቁስ ቀደም ብሎ በማሟላት፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ባለሙያ በጊዜው በመቅጠር ግንባታ የሚያስፈልግ የጉልበት (የሙያ) ክፍያ ወጪን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ ይረዳል::

5. ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ

ለግንባታ የሚያስፈልጉ እና ሥራን የሚያቀላጥፉ እንደ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ፓሌት (የብረት ምንጣፍ) የኮንክሪት ምንጣፍ ተሻካሚ፣ ተገጣጣሚ ብረቶችን፣ ግንባታው ሳይቋረጥ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያው የሚቀርቡበትን ቀደም ያለ ዝግጅት ማድረግ ለግንባታ የሚያስፈልግ ጊዜ በመቆጠብ፣ በፍጥነት ወደሚፈለገው ትርፋማ ጉዞ ለማምራት በተዛማጅነትም ወጪን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ብርሃን የሚያስገቡ መስታወቶችን እና የፀሀይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ የሚለውጡ ግርግዳዎችን ማካተት፣ ህንፃው ከተጠናቀቀ በኃላ ዘላቂ የኃይል ፍጆታ (ገንዘብ) እንዲቆጠብ ያደርጋል
፡፡

https://t.me/ethioengineers1
👍24❤5
ይህንን ያውቃሉ?

የዓለማችን ቁመታሙ ድልድይ

ዱግ ድልድይ የሚገኘው በቻይና ሲኾን የጉይዡና ዩናን ግዛቶች መካከል ቤይፒን ወንዝ ላይ የተሠራ ነው።

ከወንዙ በላይ ያለው ከፍታ 565 ሜትር ያህል ሲኾን ይህም ከዓለማችን ድልድዮች በከፍታ አንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል።

ይህ ከፍታ በህንጻ ይመሰል ቢባል ከባለ 200 ወለል ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ጋር መሳ ለመሳ ይኾናል።

ምስራቃዊ የድልድዩ ተሸካሚ ማማም 269 ሜትር ከፍታ በመያዝ ከዓለም ከቀዳሚዎች ተርታ የተመዘገበ ኾኗል።

የድልድዩ ርዝመት 1341 ሜትር ሲኾን ይህም ከተንጠልጣይ ድልድዮች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል። ግንባታው በ2012 ተጀምሮ በ2016 ነው የተጠናቀቀው።


https://t.me/ethioengineers1
👍15❤5🙏1
✨ለሁሉ ነገር መላ አለው እኛ ሀገርም እስት ለማፍረስ አትቸኩሉ ትንሽም ብሆን ለማሰብ ሞክሩ

🤔ምህንድስና ማለት ደግሞ መፍትሔ ፈጣሪ ማለት ነው።

https://t.me/ethioengineers1
👍26
3D PRINTING in Construction

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታው

ስሪዲ ፕሪንቲንግ ለሕንፃ ግንባታ የሚውሉ የኮንክሪት ምንጣፎችን፣ ብሎኬቶችን በተፈለገው ቅርፅ፣ መጠን እና ስፋት በ3 አውታር (3 dimension) እያተመ የሚያወጣ ከመሆኑም በላይ፣ ቴክኖሎጂው ትላልቅ ሕንፃዎችን፣ መኖሪያ ቤቶችን፣ ቢሮዎችን፣ ድልድዮችን ወዘተ የመሳሰሉ ግንባታዎችን በፍጥነት ለመገንባት የሚያስችል ዘመን አመጣሽ መሳሪያ ወይም ማሽን ነው፡፡

በአሁን ወቅት በአለም ላይ ያለውን የመኖሪያ ችግር ከመቅረፍ ባለፈ የስሪዲ ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ ከፈጠራቸው ዕድሎች ዋና ዋና የተባሉት ጠቀሜታዎች የሚከተሉት አምስቱ በቀዳሚነት ይቀመጣሉ፡፡

፩
አካባቢን የሚበክሉ ፕላስቲኮችን እና በየቆሻሻ ገንዳ የሚገኙ ውድቅዳቂዎችን ታዳሽ ወደሆነ የኮንክሪት ምንጣፍ በመለወጥ ለግንባታ እንዲውሉ በማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

፪
በጣም ግዙፍ የሆኑ የስሪዲ ፕሪንቲንግ ኢንደስትሪን በማቋቋም በጣም ርካሽ የሆኑ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ሥር የሰደደውን የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ አይነተኛ መፍትሔ ነው፡፡

፫
በስሪዲ ፕሪንቲንግ በሚዘጋጁ የግንባታ ቁሳቁሶች የሚገነቡ ቤቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቁ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ፣ በተለይ ከተፈጥሮ አደጋዎች ጋር በተያያዘ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በገዳይ አውሎ ንፋስ የሚወድሙ መኖሪያ ቤቶችን በፍጥነት በመገንባት የተጎጂዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር የመቅረፍ ጠቀሜታው ለማመን የሚያዳግት ነው፡፡

፬
የስሪዲ ቴክኖሎጂ፣ በተለመደው የግንባታ ዘዴ ለመገንባት አስቸጋሪ የሆኑ ውስብስብ ቅርጽ ያላቸው ዲዛይኖችን በቀላሉ ለማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂን የተላበሰ በመሆኑ፣ የአስገንቢዎችንም ሆነ የገንቢዎችን ፍላጎት የመጠበቅ ድርሻው ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡

፭
በቴክኖሎጂው የሚመረቱ የግንባታ አካላቶች ከፍተኛ ጥንካሬ ተላብሰው በቀላል ክብደት የሚዘጋጁ በመሆናቸው፣ በጨረቃ ወይም በማርስ ላይ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ዕድል ሊፈጥሩ የሚያስችሉ ናቸው ተብለው እንደ ናሳ ባሉ የአሜሪካ ምርምር ተቋማት በቴክኖሎጂው ላይ ቀልብ ተጥሎበታል፡፡

ለዚህም ዋናው ምክንያቱ፣ ብዙ ልምድ በሌላቸው ሰዎች በቀላሉ የሚገጣጠም በመሆኑ ግንባታን ያለችግር የማካሄድ ዕድል ሊፈጥር ይችላል ተብሎ በመታመኑ ነው፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍12❤1🔥1👌1
የግንባታ የጊዜ ቀመርን
ለማዘጋጀት የሚረዱ ሳይንሳዊ
አማራጮች


የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች አብዛኛውን ጊዜ ስሜትን የሚተናኮሉ፣ አስፈሪ ህልም እና ቅዠት ውስጥ የሚከቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለዚህ ዋናው መንስኤ ከእውነታ ጋር የተዛመደ የግንባታ ጊዜ ቀመር (Construction timeline) ግንባታውን የሚመራበት ሥርዓት ካለማዘጋጀት ጋር በይበልጥ የተዛመደ ነው፡፡

የዕቃ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ ውጣ ውረዶችን ከግምት በማስገባት፣ ከእውነታ ጋር የተዛመደ የግንባታ የጊዜ ቀመር በማዘጋጀት ከተጠቀሰው አላስፈላጊ ህልም እና ቅዠት ለመከላከል ከሚረዱ ዘዴዎች የሚከተሉት በቀዳሚነት ይቀመጣሉ፡፡

🚧 በቂ ልምድ ካለው ኮንትራክተር ጋር መዋዋል

የኮንስትራክሽን ሥራ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ባልተናነሰ መጠን ተግባራዊ ልምድ እና ተሞክሮን የሚጠይቅ ነው፡፡ አንድ ኮንትራክተር በአካዳሚው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ ብቻ በአዳዲስ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ ተሰማርቶ ውጤታማ የመሆኑ ዕድሉ አነስተኛ ነው።

ይሁን እንጂ፣ አብዛኛዎቹ ባለሀብቶች የሚቀጥሩት ተቋራጭ ወይም መሃንዲስ፣ የአካዳሚ ብቃት ወይም ውጤትን መነሻ በማድረግ ሲሆን፣ ልምድ ያለው ኮንትራክተር ቢቀጥሩ ከሚከፍሉት ወጪ የሚያተርፉትን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ሰነዶችን በመመልከት ብቻ ሥራዎችን ለኮንትራክተሮች ይሰጣሉ፡፡

በዚህ ሁኔታ በመጨረሻ ሥራው እየተጓተተ ለበለጠ ኪሣራ መዳረግ ይመጣል፡፡ ስለዚህ ከተቋራጮች ጋር የግንባታ ውል ሲፈራረሙ፣ ባለሙያው ከአካዳሚ ዕውቀት በተጨማሪ፣ በቂ የሥራ ልምድ ያለው እና የግንባታ የጊዜ ቀመሩን አዘጋጅቶ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡

🚧 የግንባታ የጊዜ ቀመሩን በጋራ ማዘጋጀት

የግንባታ ቀመርን ከተለያዩ የግንባታ ቡድኖች ማለትም ከዕቃ አቅራቢዎች እና ተረካቢዎች፣ ከተለያዩ የግንባታ ባለሙያዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ሰብ ኮንትራክተሮች፣ ጋር እና ከዋናው ኮንትራክተር ጋር በጋራ እየተነጋገሩ ማዘጋጀት እና በጊዜ ቀመሩ ላይ በሂደት ሊገጥሙ የሚችሉ የማይታዩ ችግሮችን ከግምት በማስገባት ተጨማሪ ጊዜ መመደብ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው፡፡

🚧 ፍላጎት እና አቅርቦትን በተገቢው መንገድ ማደራጀት

የግንባታ የጊዜ ቀመር ሲዘጋጅ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገባቸው ጉዳዮች አንዱ፣ የግንባታው ሂደት ሳይቋረጥ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በተገቢው ጊዜ መቅረብ የሚችሉበትን አሠራር መዘርጋት ነው፡፡ ዕቃዎቹ ከውጭ ተገዝተው የሚገቡ ከሆኑ ከገንዘብ እና ከሂሳብ ተቋማት ጋር በሚኖረው ግንኙነት በመርከብ ጉዞ ከወደብ በማስገባት ሂደት ሊፈጠር የሚችል መስተጓጎልን ቀድሞ በመረዳት ቀደም ያለ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

🚧 አስፈላጊ ፍላጎትን በሚገባ ማጤን

አንድ ኮንስትራክሽን በተያዘበት የጊዜ ገደብ እና በጀት ሥራው ከተጀመረ በኋላ ባለሀብቱንም ሆነ ኮንትራክተሩ ቀደም ብለው ካስቀመጡት መስፈርት እንዲያፈነግጡ የሚያደርጉ በርካታ አማራጮች መከሰታቸው አይቀሬ ነው፡፡

አንዳንዶቹ አማራጮች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሲሆኑ፣ የተቀሩት ደግሞ የፕሮጀክቱን ብቃት እና ጥራት የበለጠ የሚያሳድጉ ናቸው፡፡ እነዚህ አማራጮች በመጡ እና ተግባር ላይ በዋሉ ቁጥር የፕሮጀክቱ ወጪ ይጨምራል፡፡
ከዚህ የተነሳ፣ የግንባታው የጊዜ ቀመርም ይዛባል፡፡

ከዚህ በመነሳት ባለሀብቱም ሆነ ኮንትራክተሩ እነዚህን አዳዲስ አማራጮች ከመጠቀማቸው በፊት ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ በተያዘለት መስፈርት ቢገነባ እና ቢጠናቀቅ የሚያስገኘውን ትርፍ አስፈላጊነቱን እና ፍላጎትን በማመጣጠን በተረጋጋ መንፈስ እና ጥናት ከውሳኔ ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍18❤2👏1
ለአዲስ አበባ ከተማ የጠጠር መንገዶች ይመጥኗታል?

ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተገኘው መረጃ፦ "በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች እየተገነቡ ነው" ይላል።

እስከ አሁን ድረስ የከተማው መንገዶች ባለስልጣን በርካታ የአስፋልት መንገዶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የሚታወቅ ነው። ከዚያም አለፍ ሲል በስፋት የኮብልስቶን ግንባታ ሲካሃድ ቆይቷል።

በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በከተማ ውስጥ  መገንባት አዋጪነቱ የሚያጠያይቅ ነው። ከአቅም ማነስና ከበጀት እጥረት ጋር የተያያዙ ጉዳይች እንኳን ካሉ ከጠጠር መንገድ ይልቅ የኮብልስትን መንገዶችን መገንባት አዋጪ ነው።

ይሁን እንጂ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ መሰረተ-ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ ናቸው።

አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመረጃው፦ የከተማዋን የመንገድ ኔትወርክ ይበልጥ በማስተሳሰር ደህንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል ከሚያካሂደው መጠነ ሰፊ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታና ጥገና ሥራ ጎን ለጎን፤ የመንገድ መሠረተ ልማትን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ መንደሮች በተገነቡባቸው አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ መሆኑን ይገልፃል።

አሁን ላይ በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገድ እየተገነባባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከናሆም አደባባይ - ገልማ አባገዳ  ፣ ከናሆም አደባባይ -  ሃና ማርያም መውጫ፣ ላምበረት አካባቢ እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ - የተባበሩት አካባቢ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።


https://t.me/ethioengineers1
👍8👏1
💥በምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና ውስጥ የሚገኘው ታዋቂው UNIVERSITY OF ACCRA ከአየር ላይ በድሮን ካሜራ የተነሳ ፎቶ ነው።

https://t.me/ethioengineers1
👍14❤4👏1
ለሊዮኔል ሜሲ በማያሚ ሊገነባለት የታሰበው ቅንጡ መኖሪያ ቤት

የግንባታው ወጪ ከ50 ሚሊየን ዶላር በላይ ይሆናል

ከሰሞኑ በኪነ ህንፃ ባለሙያው ጆርጌ ሊዊስ ቬሊዝ ይፋ የተደረገው ለሊዮኔል ሜሲ ታስቦ ዲዛይን የተደረገው መኖሪያ ቤት በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል።

ይህ አነጋጋሪ መኖሪያ ቤት በማያሚ የሚገነባ ሲሆን ከላይ ሲታይ የሊዮኔል ሜሲ መለያ የሆነውን የ "M" ፊደል ቅርፅ የያዘ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።

መኖሪያ ቤቱ በሦስት ደረጃዎች የተዋቀረ ሲሆን፣ የመርከብ ቅርፅ ያለው ነፃነት የሚሰጥ ደሴት ነውም ተብሏል።

ይህ መኖሪያ ቤት በውስጡ ከ20 በላይ መኪናዎችን መያዝ የሚችል ትልቅ የመኪና ጋራዥ፣ ከቤተሰብ እና ጓደኞች ጋር ጊዜ ማሳለፊያ የቲያትር ቤት፣ ጌም መጫወቻ ክፍል እና አምስት የመዋኛ ገንዳዎች አሉት።

ከዚህ በተጨማሪም የልምምድ እግርኳስ ሜዳ፣ የቴኒስ ሜዳ እና ሦስት የሄሊኮፕተር ማረፊያ ይኖሩታልም ተብሏል።

መኖሪያ ቤቱንም ሠርቶ ለማጠናቀቅ 50 ሚሊየን ዶላር ወጪ እንደሚያስወጣ ተገምቷል
።

https://t.me/ethioengineers1
👍13🤔6❤2