SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥ስለ መሰንጠቅ (cracking )

ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በMix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል፦  

[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ

አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።

[2] - መኮማተር (Shrinkage )
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking)   ያስከትላል ።

መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።

[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ

Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።

[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ

ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።

[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )

ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ ሊጠጣት አለበት።

[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን

በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratio ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።

[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።


https://t.me/ethioengineers1
👍24❤6👏2
🔶New Advanced Class Schedule Starting on October 16/2023

🔸Registration is active.
📲 0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
WHY EXHIBIT IN ETHIO – CON 2023?

One of Africa’s biggest International Construction Exhibition in Addis Abeba, Ethiopia.

From Oct 12 – 15, 2023 | Addis Abeba Exhibition Center.

Register TODAY;
📱 +251 912 73 46 20/
📱 +251 911 86 71 98
📧 subaevents16@gmail.com /
📧 ccae2002@gmail.com /
📧 esu_ethio@yahoo.com
🔗 www.ethiopian-construction.org
--------------------------------------------
Building Opportunities Together!
--------------------------------------------
#Ethio_Con  #Bigger #Better #Construction #CCAE #SUBA_Events #Visibility #Connection #Sales_leads #Insights  #Networking #Partnership #cooperation #AddisAbeba #Ethiopia #Africa
👍12
💥የሳን ዲያጎው የአርማታ ትዕይንት

በቺሊ ዋና ከተማ ሳን ዲያጎ ውስጥ ከጥቂት አመታት በፊት የተከናወነው መጠነ ሰፊ የኮንክሪት ሙሌት በአስገራሚነቱ የሚጠቀስ ነው።

ጠቅላላ የቦታው ስፋት 10 ሺህ ሜትር ካሬ የግንባታ ቦታ ላይ ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በተጠናቀቀው የ10 ሰዓት "ዘመቻ ኮንክሪት" 258 ከባባድ ካሚዮኖች የተሳተፉ ሲሆን፣ ለኮንክሪት ሙሌቱ በሰዓት 26 ካሚዮኖች ይገኙ ነበር። ይህ ማለት በየሁለት ደቂቃ ሃያ ሰከንዶች ውስጥ አንድ የአርማታ መሙያ ካሚዮን በቦታው ላይ ይገኝ ነበር እንደ ማለት ነው።

ይህ የኮንክሪት ሙሌት አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄዶ ቢሆን ምን ያህል ጊዜ ይወስድ ነበር የሚለውን ጥያቄ አንድ የቅይጥ ኮንክሪት አቅራቢ ኩባንያ ማናጀር ተጠይቀው፣ ዝርዝር ቴክኒካል የሆኑ ጉዳዩች ቢኖሩም አ.አ ውስጥ ሥራውን ጨርሶ ለማጠናቀቅ ቀናቶችን ይወስዳሉ ብለዋል።


https://t.me/ethioengineers1
👍15🤔2
💥አሁን አሁን የቅንጡ ሆቴሎች ዲዛይን በዚህ መልኩ እየተዘጋጀ ነው።

https://t.me/ethioengineers1
👍5
ዋትሳፕ እንደ ቴሌግራም መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል የቻናል ስርዐት አስጀምሯል፣ በዋትሳፕ መረጃ ማግኘት ለሚቀላችሁ ይህን አዲስ የከፈትኩትን ቻናል መቀላቀል ትችላላችሁ።

Follow the Ethio Construction channel on WhatsApp:👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va9LwKV3AzNPMcHPrB2D
Advanced Bridge Design With MidasCivil class contents options :
[ Evening or Weekends Schedule ]
🔸Option 1. Full Adavanced Bridge Design with Midascivil, Ms Excel & Autocad & Detail Design Code Discussion
🔸Option 2. Only Advanced MidasCivil Software
🔸Option 3. Only Basic MidasCivil Software for Begineers 
( Course Price Varies for the above 3 Options )
● Registration is active
📲 0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍2❤1
🔶Advanced Structural Design
ST CHECK LISTS
እነዚህን መመዘኛ መስፈርቶች አሟልተን ነዉ ዲዛይን አሰገብተን የምናስፈቅደው።
ለ 2 ወሩ Special Structural Design Package ስልጠና መጨረሻ ላይ እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።
[ Evening or Weekends Schedule ]
These are the checklists we will finally discuess for our 2months  special structural package course.

🔹Concrete Stru(Ordinary & High rise)
🔹Steel structure
🔸Software : Etabs, Sap, Safe

● Registration is active
📲
0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
❤2👍2
💥Reasons for cause and description of type of cracks

⏺1. Diagonal Cracks

⚡️The main cause of diagonal cracks in concrete columns is

👉 Inadequate load carrying capacity of the columns;
👉 insufficient cross-section and inadequate reinforcement steel.
👉 Diagonal Cracks would influence structural soundness and hence it needs to be dealt with.

⏺2. Horizontal Cracks

👉 Horizontal crack in reinforced concrete column is observed to initiate mostly at the beam-column junction, and on column face where tensile stress is large.
👉 Columns with in adequate moment resistance capacity,
👉 Insufficient reinforcements, or disposition of installed reinforcement are prone to horizontal cracking
👉 Horizontal cracks substantially reduce the shear strength of the column leading to a greatly increased risk of failure. So, it is required to be tackled as soon as

⏺3. Splitting Cracks

👉 Splitting cracks in reinforced concrete column are short parallel vertical cracks with non-uniform width.
👉 Columns with Insufficient steel reinforcement, and low concrete quality are susceptible to experience such types of cracks.
👉 Splitting cracks in concrete columns initiated as a result of reaching its maximum load carrying capacity.

⏺4. Corrosion Cracks

👉 Corrosion cracks in concrete columns are developed along the line of reinforcements.
👉 This type of cracks is commonly uniform in width and widen as the column is ageing.

👉 Possible reinforcement corrosion and inadequate bond between concrete and steel bars are the cause of corrosion reinforcement in concrete columns.


https://t.me/ethioengineers1
👍8
#በሳይታችን(Site)የብሎኬት አጠቃቀም ስሌት?

በ አንድ ሜትር ካሬ ምን ያህል ብሎኬት እንጠቀማለን?? የሚለውን ስሌት በካ.ሜ
እንዴት መጣ ለሚለው ስሌት
የብሎኬት ስፋት =0.4ሜ 
               ቁመት =0.2ሜ
=1/(0.4*0.2)
=12.5
=~13
ስለዚህ በ አንድ ሜትር ካሬ 13 ፍሬ ብሎኬት እንጠቀማለን ማለት ነው


https://t.me/ethioengineers1
👍24❤5
💥Foundation

1) ቁፋሮ እና አፈር ሙሌት

መሰረት ሁልጊዜ የተረጋጋ መሬት ላይ ሊቀመጥ ይገባል።
ጥሩ አፈር ካልሆነ በተመረጠ እና ከሌላ ቦታ በመጣ አፈር በሚገባ
ተጠቅጥቆ እና ተደልድሎ ሊቀመጥ ይገባል።

የተመረጠው አፈር ንብርብር/layer/ በየ 25 ሴ᎐ሜ በሚገባ
ሊጠቀጠቅ ወይም ሊደለደል/compact/ ሊደረግ ይገባል።

በሚደለደልበት ወቅት በተወሰነ ረገድ እያንዳንዱን ንብርብር ለተሻለ ጥቅጠቃ እንዲያመች እርጥበት እነዲያገኝ ውሀ ማርከፍከፍ ያስፈልጋል

2) አርማታ ሙሌት እና የብረት ስራ


ቀጭን አርማታ/lean Concrete/ ከተመረጠው አፈር ሙሌት በላይ ሊደረግ ይገባል እንደ አስፈላጊነቱም እርጥበተ መከላከያ/water proof/ ሊደረግ ይችላል።

አርማታ ሙሌት ለመሰረት፣ ቢም፣ ኮለን እና ወለል ስራ የአርማታ ጥንካሬ በትንሹ C25 ሊኖረው ይገባል በተጨማሪ እንደ ስትራክቸራል ዲዛይኑ ሊለያይ ይችላል።

የቢም ብረት የላይኛው ብረት መሀል ላይ የታችኛው ደግሞ ኮለን ድጋፍ/support/ ላይ ሊሆን ይገባል እንዲሁም ማት ፋውንዴሽን ላይ የዚህ ተቃራኒ ይሆናል።

ብረት 4D የብረቱን ውፍረት በአራት በማባዛት የሚሰጠንን ርዝመት በመደረብ መተላለፍ ይተበቅበታል።

ዲዛይን ላይ በተቆራረጠ መስመር /hidden line የሚቀመጡ ብረቶች ሁልጊዜ የታች ብረት ሆነው ይቀመጣሉ።

የአርማታ ሽፋን/concrete cover/አብዛኛውን ግዜ 5ሴ᎐ሜ ይሆናል ከመሬት በላይ ግን በ 2᎐5ሴ.ሜ ይሰራል።

በአርማታ ወይም በብረት የሚሰራ ክፍተት መስጫ spacer/ ልንጠቀም ይገባል።


https://t.me/ethioengineers1
👍14❤3😍1
🫵እስቲ ዛሬ በነዚህ ጉዳዮች በስራ ቦታ ,በትምህርት ቤት ወይም በያላችሁበት ተወያዩ
.
🤔 አንድ የስራ ተቋራጭ ስራ አሸንፎ ውል ገባ : የሳይት ርክክብ ፈጸመ:ፕሮጀክቱ የሚሰራበት ቦታ የወሰን ማስከበር ችግር ነበረበት ፤ ነገር ግን ካሉት አራት ብሎክ ሁለቱን ሊያሰራ የሚችል ቦታ አለ ። ይህ ሁሉ ሲሰራ የስራ ተቋራጩ አድቫንስ ክፍያ አልወሰደም ፤ የስራ መርሐ ግብር አላቀረበም። የአንድቫንስ ክፊያ SCC ላይ የተገለጸውና ባሌቤትም የተዋዋለው 30% ቅድመ ክፊያ ለመክፈል ነው። ነገር ግን በውል ወቅት ቃለ ጉባኤ በመያዝ የአድቫንስ ክፍያው በphase phase በቅድሚያ  10% ፣  የመሠረት ስራ ስትጨርስ 10 %፣ 10% ሱፐር ስትራክቸር  እየሰራ ለመክፈል ተስማምተው ወደ ስራ ተገባ። አድቫንስ ለመክፈልና ስራ ለማስጀመር ያስችል ዘንድ የስራ ተቋራጩ የስራ መረሀ ግብር እንዲያቀርብ አማካሪው ደብዳቤ ጻፈ የስራ ተቋራጩም ያስገባው የስራ መርሐ ግብር unrealistic በመሆኑ አማካሪው የቀረበውን የስራመርሀግብር ተስተካክሎ እንዲቀርብ አዘዘ።
*ከሁለት ወር በሇላ የስራ ተቋራጩ የስራ መርሐ ግብሩን አስተካክሎ መለሰ። 
እንግዲህ በዚህ 2 ወር ከ15 ቀን ውስጥ የሞቢላይዜሽን ስራ ሰራ ነገር ግን የስራ መርሐ ግብር አልቀረበም ነበር ። በሞቢላይዜሽን ወቅት የሰራውን ስራ ተደምሮ በዝርዝር ቀርቦ ከመጀመሪያው ፌዝ 10%ወስጥ 1% በቃለ ጉባኤ እንዲከፈለው ተደረገ ። ከ3ወር በሇላ የስራ መርሐ ግብሩ ጸደቀ ባሌቤት በቅድሚያ እከፍላለሁ ካለው 10% ውስጥ 55% ከፈለው አጠቃላይ 56% ተከፈለው የስ/ተቋራጩ ሰበብ እንዳይፈጠር  የወሰን ማስከበር ችግር በሌለበት ቦታ ስራ እንዲሰራ ቀደም ብሎ አማካሪው በተደጋጋሚ ደብዳቤ ጽፎለታል። ነገር ግን የስራ ተቋራጩ ብሩን ከወሰደ በሇላ ከወሰደው ከ10% ውስጥ 55%አድቫንስ የወሰደ ሲሆን ነከመለስተኛ earth work and delivery of materialን ጨምሮ ስራውን የሰራው ከ10% ክፍያ የ30%  ክፍያ(ዋጋ) ብቻ ነው የሰራው። ከዚያ በቃ ከእቅዱ በታች በታች ይሰራ ጀመረ ከአራት ወር በሇላ ቀሪ 45%(10% of 45%) አድቫንስ ይለቀቅልኝ ብሎ ጠየቀ። ባሌቤትም ሲመልስ "በወሰድከው ገንዘብ መስራት ስላልቻልክ አንከፍልህም።" ጭቅጭቁ ሲበዛ ከሁለት ወር ባሌቤትም የወሰን ማስከበርም ስራ 100% ስለ ጨረሰ  ቀሪው 45% አድቫንስ ተለቀቀለት ። የውሉን 10% ሙሉ በሙሉ ወሰደ አጠቃላይ ከ10% አ.ክፍያ 5% የገንዘብ መጠን ሰርቷል። የስራ ተቋራጩ ከነዚያ አራት ህንፃ አንዱን ብቻ የመሠረተ ስራ ጨረሰ ሶስቱ አልተጀመረም። የአንዱን ህንፃ የመሠረት ስራ ስለጨረስኩ ለሰራሁበት ክፊያ ጠየቀ ተከፈለው ።
:
👉ይህ የስራ ተቋራጭ የውል ጊዜው ሊጠናቀቅ ሲል የጊዜ ማራዘሚያ ጠየቀ
1) አድቫንስ ስለዘገየብኝ ርክክብ ከፈጸምኩበት ጊዜ ጀምሮ EOT ይሰጠኝ
2) በወሰን ማስከበር ምክኒያት ስራ መስራት ያልቻልኩበት ጊዜ ይሰጠኝ
3) የተለያዩ የዲዛይን ክላሪፍኬሽን ጠይቄ መልስ ስላልተሰጠኝ መልስ ይሰጠኝ። በማለት የስ/ተቋ ጠየቀ..

👉 አማካሪ ሲመልስ
1)ርክክብ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ የስራ መርሐ ግብር አቅርብ ተብለህ በወቅቱ አላቀረብክም ያቀረብከውም unrealistic ስለሆነ እንድታስተካክል ተመልሶልህ ከሁለት ወር በሇላ ስላቀረብክ በለሌለ ነገር EOT አይገባህም።

አድቫንስ ዘገዬ ለተባለው በወቅቱ የስራ መርሐ ግብር ባለማቅረብህና በወቅቱ የተሰጠህን ገንዘብ ለስራ ስላላዋልክና አሁንም በጸደቀልህ የስራ መርሐ ግብር  መሠረት ባጠቃላይ የወሰድከውcን ገንዘብ ስራ ላይ ስላላዋልክ ላንተ የግዜ ማራዘሚያ አይሰጥህም የመንግስትን ገንዘብ ለግል ጥቅምህ ስላዋልክ ትከሰሳለህ ተባለ
2) ከወሰን ማስከበር ጋር ለጠየቀውም የስራ ተቋራጩ የስራ እንቅስቃሴ ደካማ ስለነበር መስራት የሚችልበትን ቦታ ላይ ስራ ተብሎ  ምንም መስራት ያልቻለ በመሆኑ ለዚህም ያቀረብከው የጊዜ ጥያቄ አይገባህም ተባለ
3) የዲዛይን clarification አማካሪው ስላዘገየበት የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

⚡️NOTE ፡ ስራዎችን በወቅቱ እንዲሰራ ደብዳቤዎች (ማስረጃዎች) አሉ

👉ምትወያዩበት ጥያቄ እና ሀሳብ👇

1. ከውል በሇላ በእለቱ ውይይት የተካሄደበት ቃለ ጉባኤ የውል አካል መሆን ይችላል?
2) የጊዜ ማራዘሚያም ይሁን የመdxጀመሪያ አድቫንስ ለመክፈል የስራ መርሐ ግብር ተገምግሞ  ከመጽደቁ በፊት የነበሩ ነገሮች ተቀባይነት አላቸው?
3) የመንግስት ገንዘብ ወስደው የፕሮጀክት የሚያዘገዩ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ በኛ ሀገርም ሆነ በውጭ ሀገር አለ?


📲 እኛን ለማግኘት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

https://t.me/ethioengineers1
👍12❤6👏1
💥የመንገድ ዓይነቶች እና የአገልግሎት ደረጃ
   
መንገዶች በሶስት ይመደባሉ

1. የፌደራል መንገዶች ፣ 2.የክልል መንገዶች 3. የከተማ መንገዶች

1.የፌዴራል መንገዶችን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሲሆን፣ የክልል እና የአካባቢ መንገዶችን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ለዚሁ ዓላማ ተብለው በየክልሉ መንግስታት የተቋቋሙ የክልል መንገድ ኤጄንሲዎች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ የከተማ መንገዶችን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት በየከተማ አስተዳደሩ ለዚሁ ዓላማ የተቋቋሙ ተቋማት ናቸው፡፡ 

በዚህም መሰረት የፍጥነት መንገዶች፤ዋና መንገዶች እና አገናኝ መንገዶች የፌዴራል መንገዶች፣ ሰብሳቢ እና መጋቢ መንገዶች የክልል መንገዶች ሲሆኑ፣ በከተማ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን የፌዴራል መንገዶች አካል ያልሆኑ መንገዶች የከተማ መንገዶች ናቸው፡፡ 

ኢ መ አ የፌደራል መንገዶች ማለትም የፍጥነት፣ አውራ፣ ዋና መዳረሻ መንገዶችን የማልማትና የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ የፍጥነት መንገዶች እና አውራ መንገዶች  አዲስ አበባን ከጐረቤት ሀገራት እና ወደቦች ጋር የሚያገናኙ እና አዲስ አበባን ከክልል ዋና ከተሞች እና ከሌሎች ከፍተኛና መካከለኛ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ናቸው፡፡

ዋና መዳረሻ መንገዶች ለልማት ሊውል የሚችል ሰፊ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ከሚገኝባቸውና ከአቅራቢያቸው በሚገኙ ወንዞች በመስኖ ሊለሙ ከሚችሉ አከባቢዎች ፣ ከፍተኛ ትርፍ የምግብ ሰብል (Cash Crops) ከሚመረትባቸው አከባቢዎች፣ እምቅ የማዕድን ሃብት ከሚገኙባው ቦታዎች እንዲሁም ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ከሚገኝባቸው የገጠር አካባቢዎች ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ናቸው፡፡

የክልል እና የአካባቢ መንገዶችን የማልማትና የማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጣቸው የክልል መንገድ ኤጄንሲዎች በዋናነት የወረዳ ከተሞችን ከዞን ዋና ከተሞች ጋር የሚያገናኙ፣ የወረዳ ዋና ከተሞች ከወረዳ መለስተኛ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ እንዲሁም የወረዳ ዋና ከተሞች ከወረዳ የልማት ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን የማልማትና የማስተዳደር ሥራዎችን ያከናውናሉ፡፡ በቀጣይም የክልል መንገድ ኤጀንሲዎች ያላቸውን ኃላፊነት የሚያሻሽል/የሚያሳድግ ጥናት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ለመንግስት ቀርቦ ሲጸድቅ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡ 

በተመሳሳይ የከተሞች መንገድ ኤጄንሲዎች በከተማ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን የፌዴራል መንገዶች አካል ያልሆኑ መንገዶችን የመገንባት፣ የመጠገንና የማስተዳደር ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዋና መዳረሻ መንገዶች እንደየሚገነቡበት ዓላማ እየታየ የፌዴራል፤ የክልል ወይም የከተማ መንገዶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር  የማናቸውንም የፌዴራል መንገዶች የመንገድ ክልል ስፋት ይወስናል፡፡

በተመሳሳይ የክልል የመንገድ ተቋም የማናቸውንም የክልል መንገዶች የመንገድ ክልል ስፋት የሚወስን ሲሆን፣  የከተማ የመንገድ ተቋም የማናቸውንም የከተማ መንገዶች የመንገድ ክልል ስፋት ይወስናል፡፡

(ኢመአ)
👍13👏4❤2🙏1
ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በሙሉ!

17ኛው “ኢትዮ-ኮን” ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን ከጥቅምት 1 – 4 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡

በዚሁ ወቅት ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በኤግዚቢሽን ማዕከል ቁጥር 2 አዳራሽ ውስጥ አዲስ በሥራ ላይ ለመዋል በሂደት ላይ የሚገኘውን የተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ ዕድሳት ጉዳይን በማስመልከት ከከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የሚመጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በዚሁ መመሪያ ላይ መግለጫ ለመስጠትና ከእናንተ ከሥራ ተቋራጮች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በመድረኩ ስለሚገኙ በዕለቱና በሰዓቱ በሥፍራው ተገኝታችሁ በዚሁ ወቅታዊና አንገብጋቢ በሆነ ጉዳይ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ሐሙስ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ  በ7፡00 ሰዓት ላይ በመክፈቻው ላይ እንድትገኙልን እና ከዚሁ ጎን ለጎንም ኤግዚቢሽኑን እንድትጎበኙ በታላቅ አክብሮትና ትህትና ተጋብዛችኋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር
👍19
BeGet Engineering PLC.

🔸ላለፉት 8 አመታት ዲዛይንና ስልጠና ላይ ያዳበርነውን ልምድ በመጠቀም ለ2016 ዓ.ም ስልጠናዎችንና የዲዛይን ስራዎችን በጥራትና በተደራጀና መልኩ  አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።እያንዳንዳቸው ለ2 ወር የሚቆዩ በፓኬጅ የተዘጋጁ ስልጠናዎች አሉን ።

Advanced Level Training Package (2months)

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
8) Graphic Design

🔸Registration is active!

📲 0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
❤1🤔1